News Detail

National News
Jul 15, 2025 146 views

የ2017 ትምህርት ዘመንየ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ሀገር አቀፍ ፈተና ተጠናቀቀ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ በወረቀትና በበይነ-መረብ ሲሰጥ የቆየው የ2017 ትምህርት ዘመን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና መጠናቀቁን ተገልጿል።
ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8/ 2017 ዓ.ም በመላ አገሪቱ በወረቀትና በበይነ-መረብ ሲሰጥ የቆየው የ2017 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ዛሬ ተጠናቋል፡፡
ከዝግጅት ጀምሮ በፈተናው ወቅት በየደረጃው የሚገኙ በፈተናው ስራ የተሳተፉ ባለሙያዎች ፣ አመራሮችና ባለድርሻዎች በፈተናው ሂደት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረጋቸው ፈተናው በሰላም ተጠናቋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር የፈተናው ስራ እንዲሳካ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለተወጡ ኃላፊዎች፣ አስተባባሪዎች፣ ፈታኞች፣ የጸጥታ አስከባሪዎችና ሌሎችም ባለድርሻዎች ላበረከቱት አስዋጽኦ ምስጋና ያቀርባል፡፡
ተፈታኞችም ፈተናው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ላሳዩት በጎ ስነ- ምግባር አያመሰገነ መልካም እድል እንዲገጥማቸው ትምህርት ሚኒስቴር ምኞቱን ይገልጻል፡፡
የ2017 ትምህርት ዘመን ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና ከሰኔ 23/2017 ዓ.ም ጀምሮ በወረቀትና በበይነ መረብ በመላ ሀገሪቱ ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል።
Recent News
Follow Us