News Detail
Aug 05, 2025
72 views
ዩኒቨርሲቲዎች ዓለም ያለችበትን ሁኔታ የተገነዘቡ፤ ሀገርን ከችግር ሊያወጡ የሚችሉ ጥናትና ምርምሮች በማድረግ እውነትና እውቀትን መሠረት ያደረገ ሀሳብ የሚፈልቅባቸው ተቋማት ሊሆኑ ይገባል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
የትምህርት ሚኒስትሩ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የለውጥ ምክር ቤት ማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው በስተላለፉት መልዕክት አሁን ካለንበት የትምህርት ጥራት ችግር ለመውጣት ትልቅ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ሪፎርሞች ተቀርፀው በትምህርት ሴክተሩ እየተተገበሩ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በተለይም ዩኒቨርሲቲዎች ዓለም ያለችበትን ሁኔታ የተገነዘቡ፤ ሀገርን ከችግር ሊያወጡ የሚችሉ ጥናትና ምርምሮች በማድረግ እውነትና እውቀትን መሠረት ያደረገ ነፃ ሀሳብ የሚፈልቅባቸው ተቋማት ሊሆኑ ይገባል ነው ያሉት።
እንደ ህብረተሰብ እንዳንጠፋ ከፈለግን ይህንን የሚቋቋም ትውልድ ለመፍጠር በመሰረታዊነት በመናበብ ከላይ እስከ ታች እነዚህን ሪፎርሞች መተግበር ይገባናል ብለዋል።
በዚህም በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥራት ያለው ትምህርት እንዲኖረን እንፈልጋለን ያሉት ሚኒስትሩ ከዚህ በኋላ በዩኒቨርሲቲዎች መካከል የሚኖር ውድድር በሚሰጡት የትምህርት ጥራት እና በሚሰሯቸው ጥናትና ምርምሮች ብቻ መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል።
አክለውም ብቃት ያላቸው ተማሪዎች በጋራ ተሰብስበው ብቃት ባላቸው መምህራን የሚማሩበት ከባቢ በዩኒቨርስቲዎች እንዲፈጠር እንፈልጋለንም ብለዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ በበኩላቸው ይህ የለውጥ ምክር ቤት ጉባኤ የከፍተኛ ትምህርት ዘርፉ ወዴት እየሄደ ነው፤ እንዴት ሪፎርሙ መተግበር እንችላለን የሚለውን ማየት የተቻለበት ነው ብለዋል።
የቁልፍ ተግባራት አፈፃፀምም ዩኒቨርሲቲዎችን ደረጃ ለማውጣት ሳይሆን ዩኒቨርሲቲዎቹ ምን ደረጀ ላይ ናቸው የሚለውን ያየንበት ነበር ያሉ ሲሆን
በአጠቃላይ ለሁለት ቀናት የቆየው ጉባኤ በትምህርት ስርዓቱ ላይ እየተደረገ ስላለው ለውጥ የጋራ መግባባት ላይ የተደረሰበት እንደሆነም ተናግረዋል።
''የከፍተኛ ትምህርት ለላቀ ተፅዕኖ" በሚል በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የነበረው የኢትዮጵያን የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የለውጥ ምክር ቤት ጉባኤም ተጠናቋል።