News Detail

National News
Jul 31, 2025 45 views

ተባብረን በመትከል ለልጆቻችን አረንጓዴ ሀገር እናስረክባለን፤ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

ትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች 700 ሚሊየን የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ የግንፍሌ ወንዝ ዳር ፕሮጀክት አስቀምጠዋል።
በምርሃ ግብሩ ተገኝተው አሻራቸውን ያስቀመጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተባብረን በመትከል ለልጆቻችን አረንጓዴ ሀገር እናስረክባለን ያሉ ሲሆን የጎዳናትን ፕላኔት ጥሩ ስራ ሰርተን ምቹ የሰው ልጆች መኖሪያ ለማድረግ መትጋት አለብን ብለዋል።
የአጠቃላይ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በበኩላቸው በሀገር አቀፍ ደረጃ 700 ሚሊዮች ችግኝ በአንድ ጀንበር የሚለው መርሃ ግብር ተሳታፊ መሆናቸው ደስታ እንደፈጠረባቸው ጠቁመው የሚተከሉት ችግኞች ጸድቀው ጥቅም እንዲሰጡ አስፈላጊው እንክብካቤ እንደሚደረግ ተናግረዋል።
የተተከሉት ችግኞች የአየር ሚዛንን በመጠበቅ፣ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ እንደሚሆንም አክለዋል።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ የሚተከሉት ችግኞች ለአካባቢውን ውበት እንደሚጨምሩ ገልጸው በዚህ ታሪካዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተሳታፊ መሆናቸው ደስ እንዳሰኛቸው ተናግረዋል።
 
 
 
 
 
 
 
Recent News
Follow Us