News Detail
Jul 29, 2025
41 views
ኢትዮጵያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው 2ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሥርዓተ ምግብ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ በትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ያላትን ልምድ አካፈለች።
በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው 2ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሥርዓተ ምግብ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ በትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም አተገባበር ያላትን ልምድና የመንግስትን ቁርጠኝነት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አቅርበዋል።
የሀገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባ ፖሊሲ ፍሬም ዎርክ በማውጣት ሀገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ተግባራዊ በማድረግ የአካባቢ ልማትና ግብርናን ለማሳደግ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎችን አብራርተዋል።
በዚህ የሀገር በቀል የት/ቤት ምገባ ፕሮግራም መንግስት 6.3 ቢሊየን ብርመመደቡንና የማህበረሰቡ ድጋፍ ደግሞ 9.8 ቢሊየን ብር መድረሱን ገልጸው የአጋር ድርጅቶች ድጋፍ ደግሞ 1.3 ቢሊየን መሆኑን አብራርተዋል።
ይህም በኢትዮጵያ ለት/ቤት ምገባ 90 በመቶ የሚደርሰው በጀት በመንግስትና በማህበረሰቡ ተሳትፎ የሚሸፈን መሆኑን ገልጸው ተግባሩ የመንግስትንና የማህበረሰቡን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል።
የምገባ ፕሮግራሙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህፃናት ትምህርታቸው ላይ ትኩረት አድረገው እንዲማሩ ከማድረጉ ባለፈ፤ ጤንነታቸው ተጠብቆ ትምህርታቸው ሳይቋረጥ እንዲማሩ ማድረግ ያስቻለ ተግባር ስለመሆኑም ገልጸዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ ከጉባኤው ጎን ለጎንም ከአለም የትምህርት ቤት ምግብ ጥምረት (School Meal Coalition) እና ከአለም የምግብ ፕሮግራም ኤክስኩዩቲቭ ዳይሬክተር ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።