News Detail
Nov 29, 2021
1.4K views
በጦርነቱ ምክኒያት ከአንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን የሚበልጡ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር ) በጥፋት ኃይሉ በፈጸመው ወረራ ከአንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን የሚበልጡ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ከወር በፊት በነበረው መረጃ ከአንደኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚያስተምሩ ከ1ሺህ 600 በላይ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱንና 300 ያህሉ ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ሚኒስትር ደኤታው አስታውቀዋል፡፡
የጥፋት ቡድኑ በከፈተው ጦርነት ትግራይ ያሉ አራት ዩኒቨርስቲዎችን ጨምሮ የወልዲያ ዩኒቨርስቲ ስራ ማቆማቸው ይታወቃል፡፡
በእነዚህ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ያሉ ተማሪዎችንና መምህራንን ወደሌሎች ዩኒቨርስቲዎች የመመደብ ስራ እንደተሰራ ገልፃዋል፡፡
የጥፋት ቡድኑ የከፈተውን ጦርነት በአጭር ጊዜ በመቀልበስ በቀጣይ የትምህርት ስርዓት ላይ በማተኮር መስራት እንደሚያስፈልግም ሚኒስትር ዴኤታው አስረድተዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴርም በጦርነቱ የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ወደ ቀድሞ ይዞታቸው ለመመለስ እንሚሰራም ተናግረዋል፡፡
Recent News
Aug 28, 2025
Aug 23, 2025
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
Aug 21, 2025
Aug 13, 2025
Aug 08, 2025