News Detail
Aug 22, 2025
93 views
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በውጭ ሀገር ካሉ አቻ ተቋማት ጋር የሚያደርጓቸውን ስምምነቶች አፈጻጸም አጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠየቀ፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ አስተባባሪነት ኢንሃ ከተሰኘ የኮሪያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ
በስምምነት ፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የትብብር ስምምነቱ በአቬሽን ሳይንስ፣ ኤሮስፔስ ኢንጂነሪንግ እና ስማርት ሲቲ ትምህርት ፕሮግራሞችን በማጠናከር እንደሆነም ተገልጿል።
ዩኒቨርሲቲው በሀገራችን የአቬሽን ሳይንስ እና ኤሮስፔስ ኢንጂነሪንግ ትምህርት ፕሮግራሞችን ለማጠናከር ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ሰነዱን የተፈራረመ ሲሆን ኢንሃ ዩኒቨርሲቲን በመወከል ፕሮፌሰር ሂቸንግ ኮህ እና ጅማ ዩኒቨርሲቲን በመወከል ደግሞ አቶ ኤፍሬም ዋቅጅራ ተፈራርመዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በሀገራችን የስማርት ሲቲ ትምህርት ፕሮግራምን ለማጠናከር ከአዲሰ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር የመግባቢያ ሰነዱን የተፈራረመ ሲሆን አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲን በመወከል የዩኒቨርስቲው አካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ከማል ኢብራሂም ተፈራርመዋል፡፡
የመግባቢያ ሰነዶቹ የሚያተኩሩባቸው ቁልፍ ጉዳዮች የአቅም ግንባታ ሥልጠና፣ ምርምር እና የተማሪዎችና መምህራን ልውውጥ ከትብብር ማዕቀፎቹ መካከል ዋና ዋናዎቹ እንደሚሆኑም ተገልጿል።
የማፈራረም ሂደቱን የመሩት በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ የትብብር ማዕቀፎቹ በሶስቱም የትምህርት ፕሮግራሞች ሀገራችን ብቁ ባለሙያዎችን እንድታፈራ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ መሆናቸውን ጠቁመው ተቋማቱ በስምምነቱ መሰረት ለውጥ ለማምጣት ጠንክረው መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል።
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም ሶስቱም ተቋማት ተቋሞቻቸውን በመወከል የወሰዱትን የጋራ ሀላፊነትና አደራ በሚገባ እንደሚወጡ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
Recent News
Aug 28, 2025
Aug 23, 2025
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
Aug 21, 2025
Aug 13, 2025
Aug 08, 2025