News Detail
ከአምናው በእጥፍ የሚበልጡ ተማሪዎች የዛሬውን ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደዋል።
በመግለጫቸው ሚኒስትሩ የዛሬውን ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከተመዘገቡት 91.5% የሚሆኑ ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን ገልፀዋል።
ዛሬ መሰጠት የጀመረው ሀገር አቀፍ ፈተናም በሁሉም ቦታ በሰላም ሲሰጥ መዋሉንም ተናግረዋል።
ፕሮፌሰር ብርሀኑ ፈተና ከመሰረቅ ጋር በተያያዘም ምንም አይነት ችግር እንዳልገጠመም ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ በዘንድሮው አመት የ2013ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተናን አምና ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች እጥፍ ፈተናውን መውሰዳቸውንም ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ በየደረጃው ፈተናው በሰላም እንዲካሄድ ላደረጉ አካላትም ምስገና አቅርበው በቀጣይ ቀናትም የተጠናከረ ክትትል እና ቁጥጥር በማድረግ ፈተናው በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ እንደሚደረግ ተናግረዋል።
በዛሬው እለት በጠዋት መርሀ ግብር እንግሊዘኛ እንዲሁም በ ከሰዓት መርሀግብር የሂሳብ ፈተና ተሰጥቷል።
ዛሬ ጠዋት የፈተናውን ሂደት በተመለከተ ሚኒስትሩ እና የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በጋራ በአዲስ አበባ በሚገኙ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች በመገኘት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አሰጣጥን መመልከታቸው ይታወሳል።
Recent News
Aug 28, 2025
Aug 23, 2025
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
Aug 21, 2025
Aug 13, 2025
Aug 08, 2025