News Detail
Nov 11, 2025
33 views
ከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ለታቀዱ የሪፎርም ተግባራት መሳካት ሁሉም አካላት የሚጠበቅባቸውን መወጣት እንዳለባቸው ተገለጸ፤
የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በ34ኛው የትምህርት ጉባኤ ላይ እንደገለጹት በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ለታቀዱ የሪፎርም ተግባራት መሳካት ሁሉም አካላት የሚጠበቅባቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በዚህም የኢንዱስትሪዎችና የትምህርት ተቋማት ትብብር መሥራት ሁለቱንም አካላት የሚጠቅም ተግባር መሆኑን አስገንዝበዋል።
አያይዘውም የዩኒቨርስቲዎች በመማር ማስተማር እና በማህበረሰብ አገልግሎት ስራ ላይ ማተኮር እንዳለባቸው ገልጸው ከየዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ምገባ ጋር በተያያዘ ኃላፊነት ወስዶ የሚከታተል ተቋም ለማቋቋም እቅድ መኖሩንም ተናግረዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም የዩኒቨርስቲዎች የትኩረት መስክ ልየታ በሂደት እየተሳካ የሚሄድ መሆኑን ገልጸው በዚህ ሂደት የሚፈጠሩ የመምህራንን እጥረትና ከምችት ለማሰተካከል አዘዋውሮ የማሰራት አቅጣጫ መኖሩንም ጠቁመዋል።
የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በትኩረት ለመደገፍ የተለየ የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ መሆኑንም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ጨምረው አብራርተዋል።