News Detail

National News
Feb 08, 2026 33 views

ባለፉት የለውጥ አመታት በትምህርቱ ዘርፍ በተከናወኑ የሪፎርም ስራዎች ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መመዝገባቸው ተገለጸ።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በትምህርት ዘርፉ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተተገበሩ የሪፎርም ተግባራትና የተመዘገቡ ውጤቶች በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል።
በዚህም በትምህርቱ ዘርፍ ባለፉት የለውጥ አመታት በተከናወኑ የሪፎርም ስራዎች ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።
እነዚህ የሪፎርም ስራዎች በዋናነት የትምህርቱን ስርዓት ከወቅታዊው የዓለም ሁኔታ ጋር ለማጣጣምና የዜጎችን የዕውቀት አድማስ ለማስፋት ያለሙ መሆናቸውንም አመላክተዋል።
ከእነዚህ ስኬቶች መካከል በሀገር አቀፍ ደረጃ በትምህርት ለትውልድ ፣በትምህርት ቤት ምገባ በስርዓተ ትምህርት ለውጥ፣የመምህራንና የትምህርት ቤት ምገባ፣በማጠናከሪያ ትምህርት እንዲሁም የትምህርትጥራትና ተደራሽነትን ከማስፋት አንጻር የተመዘገቡ ስኬቶች ተስፋ ሠጪ መሆናቸውን አብራርተዋል።
በአጠቃላይ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡት ስኬቶች የትምህርትን ጥራትና ተደራሽነት ከማስፋት ባሻገር ብቁና ተወዳዳሪ ትውልድ ለመፍጠር ጠንካራ መሰረት የጣሉ ስለመሆናቸው ተናግረዋል።
በቀጣይም የተገኙ ስኬቶችን በማጠናከርና የታዩ ጉድለቶችን በማረም የትምህርት ሪፎርሙ የተቀመጠለትን ግብ እንዲመታ በትኩረት እንደሚሰራ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
Recent News
Follow Us