News Detail
Aug 21, 2025
113 views
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
የዘርፉ መሪ ተዋንያኖችን ያሰባሰበው የምክክር መድረክ የ2017 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም የሚገመገምበትና የ2018 ዓ.ም እቅድ ላይ በመምከር የለውጥ ስራዎችን በላቀ ትጋት ለማስቀጠል ስምምነት የሚፈጸምበት መሆኑ ተመላክቷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት ትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ባስተላለፉት መልዕክት ትምህርትን ለዜጎች ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለማድረስ የሚደረገውን ጥረት አጠናክሮ በማስቀጠል ረገድ ያሉ ጅምር ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ አስገነዝበዋል።
ሚንስትሩ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በመንግስት ብቻ በሚደረጉ ድጋፍና ጥረቶች የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ የማይቻል በመሆኑ በማህበረሰቡንና በሌሎች ባለድርሻ አካላት በትምህርት ለትውልድ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር እንዳለባቸው አሰገንዝበው በዚህ ረገድ የክልልና ከተማ አስተዳድር ትምህርት ቢሮዎች በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በበኩላቸው መንግሥት ለሁሉም ዜጐች የምትመች፣ ሰላምና መረጋጋት የሰፈነባት፣ የልማትና የብልጽግና ተስፋ የሚታይባት ኢትዮጵያን ለመገንባት የተለያዩ የለውጥ መርሃ ግብሮችን በመንደፍ በርካታ ሥራዎች እያከናወኑ መሆናቸውን ያብራሩ ሲሆን ከእነዚህ የለውጥ መርሃ ግብሮች አንዱ የትምህርት ዘርፉ የለውጥ መርሃ ግብር መሆኑን ገልጸው በዚህም በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን አንስተዋል።
ክብርት ሚንስትር ዴኤታዋ ከዚሁ ጋር አያይዘው የአምስት አመት የልማት መርሃ ግብር እንዲሁም የስድስተኛውን የትምህርት ልማት መርሃ ግብር የሚጠናቀቅበት ወቅት በመሆኑ የ2018 ዓ.ም እቅዶቻችንን ስኬታማ ለማድረግ መንደርደሪያ መሆኑን አብራርተዋል
ክቡር አቶ በየነ በራሶ የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ም/ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ ለተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በክልሉ ውስጥ በመንግስትና በማህበረሰብ ተሳትፎ የተከናወኑ ዋና ዋና የትምህርት ልማት ስራዎችን አብራርተዋል።
መድረኩ የተገኙ ስኬቶች ይበልጥ ለማዳበር ፣ ያጋጠሙ ችግሮችና ተግዳሮቶችን በልምድ ልውውጥና ሌሎች ስልቶችን በመንደፍ ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑም ጭምር ተገልጿል።
Recent News
Aug 23, 2025
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
Aug 21, 2025
Aug 13, 2025
Aug 08, 2025