News Detail
Aug 22, 2025
46 views
እንደ ሀገር ፕሮጀክቶች ጀምሮ በፍጥነት ማጠናቀቅ በትምህርት ቤቶችም ባህል እየሆነ መምጣቱ ተገለፀ።
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የምክክር መድረክ ተሳታፊዎች በሲዳማ ክልል ያለውን የትምህርት እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በዚሁ ጊዜ የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በትምህርት ቤቶቹ ተገኝተው ባዩት ነገር መደሰታቸውን ገልፀው የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ለማሻሻል ከፍተኛ ጥረት መደረጉን ገልፀዋል።
በተለይም በወንዶ ገነት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተገነባው የመማሪያ ህንፃ በ8 ወር ውስጥ ተጠናቆ አገልግሎት እየሠጠ መሆኑን ተመልክተዋል።
ይህም እንደ ሀገር ፕሮጀክቶችን ጀምሮ በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ የሚለው ባህል እየሆነ መምጣቱን ያሳያል ያሉ ሲሆን ሌሎች ክልሎችም ከዚህ ልምድ ሊወስዱ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የሲዳማ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድርና ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በየነ በራሳ በበኩላቸው በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ የሲዳማ ተሃድሶ በሚል የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ለማሻሻል የተሠሩ ሥራዎችን አብራርተዋል።
በተለይም እንደ ክልል ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ልዩ ትኩረት በመስጠት ተመሳሳይ ስታንዳርድ ያላቸው 78 ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በአዲስ መገንባት መቻሉን ገልፀዋል።
የጉብኝቱ ዓላማም በክልሎች መካከል ልምድ መለዋወጥ መሆኑም ተገልጿል።
Recent News
Aug 23, 2025
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
Aug 21, 2025
Aug 13, 2025
Aug 08, 2025