News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Dec 26, 2025 31 views

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች የወሊሶ ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ ተዘዋውረው ተመለከቱ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታው ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት የወሊሶ ፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ የደረሰበት ደረጃ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
አመራሮቹ የትምህርት ቤቱን የመማሪያ ክፍል፣ የተማሪዎች ዶርም፣ የመመገቢያ አዳራሽ ፣ የአስተዳደር ህንፃና ሌሎች ግንባታዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በምልከታቸውም ግንባታው በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን የተመለከቱ ሲሆን ቀሪ ሥራዎችን በማጠናቀቅ ተማሪዎችን ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ የማዛወር ሥራ ይሰራል ብለዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር የወሊሶ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ እስኪደርስ ድረስ ተማሪዎች በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሀጫሉ ካምፓስ በመቀበል በዛሬው እለት የመማር ማስተማር ሥራ ማስጀመሩ ይታወሳል።
Recent News
Follow Us