News Detail
Aug 02, 2025
54 views
ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአዋጅ የተሰጡ ተግባርና ኃላፊነቶች ውጤታማ እንዲሆኑ በተደራጀና በተቀናጀ አግባብ መምራት እንደሚባ ተመላከተ፤ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስራ አመራር ቦርድ የአሰራር ማኑዋልና የአፈጻጸም ግምገማ ዙሪያ ከተቋማቱ የስራ አመራር ቦርድ አመራሮች ጋር ምክክር ተደርጓል ፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በምክክሩ ወቅት እንደገለጹት ለፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአዋጅ የተሰጡ ተግባርና ኃላፊነቶች በውጤታማነት እንዲፈጸሙ በተደራጀና በተቀባጀ አግባብ መምራት እንደሚባ አመላክተዋል፡፡
የዩኒቨርስቲ የስራ አመራር ቦርድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ተግባርና ኃላፊነቶቻቸውን ብሎም የሚተገብሯቸውን የሪፎርም ስራዎች በውጤታማነት መፈጸምና ማከናወን እንዲችሉ የስራ አመራር ቦርድ የአሰራር ማኑዋለል መዘጋጀቱን ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ጠቅሰዋል፡፡
ይህም ተቋማቱ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በአግባቡ እንዲወጡ እንደሚያስችላቸውና ተጨማሪ አቅምና አደረጃጀት የሚፈጥርላቸው መሆኑንም ክቡር አቶ ኮራ አስረድተዋል፡፡
የአስተዳደርና መሠረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) በበኩላቸው የስራ አመራር ማኑዋሉም ሆነ የአፈጻጸም ግምገማ መስፈርቶቹ የተፈጻሚነት ወሰን ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስራ አመራር ቦርድ የሚያገለግል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በቀጣይ ተቋማቱን በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ ለመደገፍ የስራ አመራር ቦርዱ ሰብሳቢውን ጨምሮ እስከ አስራ አንድ የሚደርሱ አባላት እንዲኖሩት መታሰቡን ጨምረው ገልጸዋል፡፡
በምክክር መድረኩም ላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ምክትል ስራ አመራር የቦርድ አባላት፣የከፍተኛ ትምሀርት ተቋማት ፕሬዚዳንቶች ፣ የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡