News Detail
Nov 11, 2025
5 views
ብዝሃነትና አካታችነትን በማረጋገጥ የዜጎችን እኩል ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተመላከተ በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ Diversity & Inclusion በሚል ርዕስ ትምህርታዊ ውይይት ተካሂዷል።
የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሽኔ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት በከፍተኛ ትምህርት ዘርፉ ብዝሃነትና አካታችነትን ለማረጋገጥ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
ብዝሃነትና አካታችነትን በማረጋገጥ በዘርፉ ያሉ እድሎችን እኩል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ቢሆንም ከሚጠበቀው አንጻር ብዙ መስራት እንደሚገባም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ጠቅሰዋል።
አካታችነትና ብዝሃነት የአመለካከት ጉዳይ መሆኑን የጠቆሙት ክቡር አቶ ኮራ ተግባራዊነቱን ለማረጋገጥና ለማስፋት ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በከፍተኛ ትምህርት በውጤት ተኮር የትምህርት አሰጣጥና በብዝሓነትና አካታችነት ላይ ያተኮረውን ትምህርታዊ ገለጻ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአካቶ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር አለማየሁ ተክለ ማርያም ሰጥተዋል።
በከፍተኛ ትምህርት ብዝሃነት አካታችነትና ውጤት ተኮር የትምህርት አሰጣጥ ጥራቱን ለጠበቀ ትምህርት ወሳኝ መሆኑንም ፕሮፌሰር አለማየሁ ጨምረው ተናግረዋል።
በትምህርታዊ ገለጻው /Public Lecture / የተሳተፉ የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች በእለቱ ያገኙትን እውቀትና መረጃ በተጨባጭ ለሚያከናውኑት ስራ ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥርላቸው ጠቁመዋል።
የመምህራንና የተማሪዎች ልማት ዴስክ ኃላፊ አቶ በየነ ተዘራ በበኩላቸው በቁልፍ የአፈጻጸም አመላካቾች/KPI/ ዕቅድ መሠረት በየሳምንቱ በተጋባዥ እንግዳ ትምህርታዊ የግንዛቤ ማስጨበጫና የእውቀት ሽግግር መድረክ እንደሚካሄድ ገልጸዋል።
Recent News
የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተደረገላቸው አቀባበል
Dec 20, 2025
Dec 15, 2025
Nov 18, 2025