News Detail

National News
Nov 11, 2025 10 views

ብዝሃነትና አካታችነትን በማረጋገጥ የዜጎችን እኩል ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተመላከተ ‎በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ Diversity & Inclusion በሚል ርዕስ ትምህርታዊ ውይይት ተካሂዷል።

የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሽኔ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት በከፍተኛ ትምህርት ዘርፉ ብዝሃነትና አካታችነትን ለማረጋገጥ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
‎ብዝሃነትና አካታችነትን በማረጋገጥ በዘርፉ ያሉ እድሎችን እኩል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ቢሆንም ከሚጠበቀው አንጻር ብዙ መስራት እንደሚገባም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ጠቅሰዋል።
‎አካታችነትና ብዝሃነት የአመለካከት ጉዳይ መሆኑን የጠቆሙት ክቡር አቶ ኮራ ተግባራዊነቱን ለማረጋገጥና ለማስፋት ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
‎በከፍተኛ ትምህርት በውጤት ተኮር የትምህርት አሰጣጥና በብዝሓነትና አካታችነት ላይ ያተኮረውን ትምህርታዊ ገለጻ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአካቶ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር አለማየሁ ተክለ ማርያም ሰጥተዋል።
‎በከፍተኛ ትምህርት ብዝሃነት አካታችነትና ውጤት ተኮር የትምህርት አሰጣጥ ጥራቱን ለጠበቀ ትምህርት ወሳኝ መሆኑንም ፕሮፌሰር አለማየሁ ጨምረው ተናግረዋል።
በትምህርታዊ ገለጻው /Public Lecture / የተሳተፉ የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች በእለቱ ያገኙትን እውቀትና መረጃ በተጨባጭ ለሚያከናውኑት ስራ ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥርላቸው ጠቁመዋል።
‎የመምህራንና የተማሪዎች ልማት ዴስክ ኃላፊ አቶ በየነ ተዘራ በበኩላቸው በቁልፍ የአፈጻጸም አመላካቾች/KPI/ ዕቅድ መሠረት በየሳምንቱ በተጋባዥ እንግዳ ትምህርታዊ የግንዛቤ ማስጨበጫና የእውቀት ሽግግር መድረክ እንደሚካሄድ ገልጸዋል።
Recent News
Follow Us