News Detail

National News
Mar 18, 2026 13 views

ሴቶችን በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፓለቲካዊ ዘርፎች ተጠቃሚ ለማድረግ እንደ ሀገር በመከናወን ላይ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆናቸው ተገለጸ።

የትምህርት ሚኒስቴር ሠራተኞችና አመራሮች "50ኛ ዓመት የሴቶች ድምጽ ለእኩልነትና ለበለጸገች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በድምቀት ከክብረዋል።
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት ቁልፍ መልዕክት ጥራቱን የጠበቀና ፍትሃዊ የትምህርት ተደራሽነትን በማረጋገጥ ሴቶችን በኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ እና ፓለቲካዊ ዘርፎች ተጠቃሚ ለማድረግ እንደ ሀገር በመከናወን ላይ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል።
አያይዘውም የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና እኩልነት ማረጋገጥ በልማትና ዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ውስጥ አይተኬ ሚና ያለው መሆኑን በማንሳት እድሎችን አሟጦ መጠቀም እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለውም መንግስት የሴቶችን ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚ ተሳትፎ ለማሳደግ በወሰዳቸው ቁርጠኛ እርምጃዎች ውጤቶች መታየት መጀመራቸውን ጠቁመው በተለይም ሴቶች በከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ እንዲመደቡና የራሳቸውን እንዲሁም የሀገራቸውን ዕጣ ፈንታ እንዲወስኑ ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ መሆኑን አብራርተዋል።
በትምህርት ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ምህረተክርስቶስ ታምሩ በበኩላቸው ባደረጉት ገለፃ የሴቶች እኩልነት ጉዳይ የአንድ ወቅት ተግባር ሳይሆን ዘላቂ ትኩረት የሚሻ የሰብዓዊ መብትና የልማት ጥያቄ መሆኑን አንስተዋል።
በመጨረሻም በሁሉም የትምህርት እርከኖች የሚገኙ ሴት ተማሪዎችና በስራ ዓለም ያሉ ሴቶች ያላቸውን አቅም ተጠቅመው ለሀገር ብልጽግና የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።
Recent News
Follow Us