News Detail

National News
Dec 25, 2025 58 views

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመረጃ አያያዛቸውንና አስተዳደራቸውን በማሻሻል ትክክለኛ መረጃ የመስጠት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት መረጃ አያያዝና አስተዳደር ሥርዓት ለማሻሻል በትምህርት ዘርፉ እየተከናወኑ ባሉ የሪፎርም ሥራዎች ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የግንዛቤ ማስጨበጫ መደረክ አካሂዷል።
በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዴስክ ኃላፊ እዮብ አየነው (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልዕክት የመንግስትም ይሁን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መረጃ አያያዛቸውንና አስተዳደራቸውን በማሻሻል ትክክለኛ፣ ወቅታዊና ተዓማኒነት ያለው መረጃ ለሚመለከታቸው አካላት የመስጠት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
አያይዘውም ይህ መድረክ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በትምህርት ዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ የሪፎርም ተግባራትን እንዲያውቁ በተለይም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመረጃ አያያዝ፣ አስተዳደደርና ግልጽነት ላይ ተመጣጣኝ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የትምህርት መረጃ አመራርና አይሲቲ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰብስብ ለማ በበኩላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚፈለጉ መረጃዎችን ትምህርት ሚኒስቴር ወደ አበለጸገው የከፍተኛ ትምህርት መረጃ አስተዳደር ሥርዓት (HEMIS) በወቅቱ ካላስገቡ የተተነተነ ሀገራዊ መረጃ ለሀገራዊ ተልዕኮም ሆነ ለባለድርሻ አካላት ማቅረብ የማይቻል መሆኑ ጠቅሰዋል። አቶ ሰብስብ አያይዘውም መረጃን በወቅቱ ካለማስገባት ጋር ተያይዞ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዘንድ ሰፊ ክፍተት መኖሩን ጠቁመዋል፡፡
በመሆኑም በመረጃ ምዝገባ፣አያያዝና አላላክ ሂደት የተፈጠሩ ችግሮችን መፍታት እና ወደ በለጸገው የከፍተኛ ትምህርት መረጃ አስተዳደር ሥርዓት (HEMIS) ያልገቡ ተቋማትን ወደ ሥርዓቱ ማስገባት ከግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ የሚጠበቅ ሌላው ውጤት መሆኑንም በማንሳት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዚህ ረገድ የሚታየውን ክፍተት በማረም ትክክለኛ፣ ወቅታዊና ተዓማኒነት ያለው መረጃ በመስጠት ሀገራዊ ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።
Recent News
Follow Us