News Detail

National News
Nov 11, 2025 18 views

የትምህርት ስርዓቱን ከዓለም የአየር ንብረት ፣ የቴክኖሎጂ፣ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ለውጥ ጋር በሚጣጣም መልኩ መቃኘት እንደሚገባ ተመላከተ። ‎ ‎34ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ባለ 12 ነጥብ አቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት የትምህርቱን ሥራ ከአየር ንብረት ፣ ቴክኖሎጂና ከዓለም የፖለቲካና የኢኮኖሚ ለውጥ ጋር በሚጣጣም መልኩ መቃኘትና መተግበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
‎ይህ ጊዜ ለውጦችን በመቋቋም ወደ እድል የሚቀይሩ ፣ አገራቸውን የሚወዱና ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ ዜጎችን ለማፍራት በትጋት የምንሰራበት ወቅት መሆኑንም ፕሮፌሰር ብርሃኑ ተናግረዋል።
በመሆኑም‎ በየደረጃው ያሉ መምምህራን በሚያስተምሩበት ትምህርት አይነት የበቁ ሆነው በመገኘት ሙያቸውን ሊያሳድጉና ሊያስከብሩ እንደሚገባ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።
በተጨማሪም ‎የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተቋቋሙበት አላማ ቅድሚያ በመስጠት ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
‎የአካል ጉዳተኞችን የመማር ማስተማር ከባቢ ምቹ ለማድረግ አገሪቱ ባላት አቅም ድጋፍ እንደሚደረግም አመልክተዋል።
‎በበኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፍትሃዊና “ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም” በሚል መሪቃል የተካሄደው 34ኛው የትምህርት ጉባኤ ባለ 12 ነጥብ አቋም መግለጫ በማውጣትም ተጠናቋል።
Recent News
Follow Us