News Detail

National News
May 03, 2025 37 views

የያቤሎ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ተጀመረ።

ትምህርት ሚኒስቴር ለማስገንባት ካቀዳቸው 50 ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የያቤሎ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ በዛሬው እለት ተጀምሯል።
ይህ በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ያቤሎ ከተማ የሚገነባውን ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና ኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች አስጀምረውታል።
በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ይህ ሞዴል ትምህርት ቤት አርብቶ አደር በሆነ አካባቢ የሚገነባ መሆኑን ጠቅሰው ይህ ለሁሉም ዜጎች ጥራት ያለው ትምህርትን በፍትሃዊነት ለማዳረስ የምናደርገውን ጥረት ያሳያል ብለዋል።
እንደ ሀገር ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥኑ በአለም ላይ ተወዳዳሪ የሆኑ፤ ብቃትና ክህሎት ያላቸው የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጎችን ለማፍራት እንደዚህ ያሉ መሠረተ ልማት የተሟላላቸው ትምህርት ቤቶች ያስፈልጋሉ፤ ለዚህም አቅደን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።
ከኛ የተሻለ ማሰብ የሚችሉ፣ ሀገር የሚመሩ ተተኪ ትውልዶች ከመንደርና አካባቢ ወጥተው ስለ ሀገር ማሰብ የሚችሉ ዜጎችን ለማፍራት የበለጠ መረባረብ አለብን ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የትምህርት ቤቱ ግንባታ ሙሉ ወጪ በትምህርት ሚኒስቴር የሚሸፈን ሲሆን 500 ሚሊየን ብር ይፈጃል ተብሏል።
ትምህርት ቤቱ ግንባታም በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ የመማር ማስተማር ሥራ እንደሚጀምር የተገለፀ ሲሆን ግንባታው በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግም ተጠይቋል።
Recent News
Follow Us