News Detail
Dec 13, 2021
786 views
የትምህርት ሚኒስትሩ ማህበራዊ አገልግሎት ሲሰጡ ለነበሩ ተማሪዎች እና መምህራን ምስጋና አቀረቡ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ለአንድ ሳምንት በቆየው ማህበራዊ አገልግሎት ለተሳተፉ ተማሪዎች እና መምህራን ምስጋና አቅርበዋል።
ለሀገራዊ ዘመቻው ውጤታማነት ለአንድ ሳምንት መደበኛ ትምህርት ተዘግቶ ሲሰጥ የነበረው ማህበራዊ አገልግሎት ዛሬ ተጠናቋል።
ለአንድ ሳምንት በቆየው የማህበራዊ አገልግሎትም በመላው ሀገራችን ተማሪዎች እና መምህራን የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብስብ፣ደም በመለገስ፣ ድጋፍ በማሰባሰብ እና ስንቅ በማዘጋጀት ተሳትፈዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) ተማሪዎች እና መምህራን ሀገራዊ ጥሪውን በመቀበል ያደረጉት ንቁ ተሳትፎ የሚደነቅ ነው ብለዋል።ተማሪዎች እና መምህራን ላደረጉት ተሳትፎም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ዘመቻው ለሀገሩ እና ወገኑ የሚችለውን ለማድረግ የማይሰስት እና ኢትዮጵያን ወደፊት ለማሻገር ዝግጁ የሆነ ትውልድ መኖሩን ያሳየ ነው ሲሉም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
በቀጣዩም ለሀገራችን ዘላቂ ሰላምና እድገት ትምህርት ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ በትምህርት ገብታው ተመሳሳይ በሆነ ሀገራዊ ስሜትና ቁርጠኝነት ተግታችሁ እንደምትሰሩ ሙሉ እምነት አለኝ ብለዋል።
ተማሪዎችም ከ ዛሬ ጀምሮ መደበኛ ትምህርታቸውን ጀምረዋል።
Recent News
Sep 02, 2025
Aug 29, 2025
Aug 28, 2025
Aug 23, 2025