News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Jul 11, 2025 55 views

ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርቱ ዘርፍ ያላትን ትብብር አጠናክራ መቀጠል እንደምትፈልግ ተገለጸ። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር Mr.Monday የተመራ የልዑካን ቡድንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በዚሁ ጊዜ ክቡር ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን ጋር የቆየ ግንኙነት በተለይም በትምህርቱ ዘርፉ ጠንካራ ትብብር እንደነበራት ጠቅሰው አሁን ኢትዮጵያ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ትኩረት በመስጠት እየወሰደቻቸው ያሉ የሪፎርም እርምጃዎችን አብራርተዋል።

የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር Mr.Monday በበኩላቸው ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ረጅም ጊዜ የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት እንደነበራት አንስተው ይህንን ታሪካዊ ግንኙነት ሀገራቸው የበለጠ አጠናክረው መቀጠል እንደምትፈልግ ገልጸዋል።

አክለውም በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ነጻ የትምህርት እድል አግኝተው ከተመረቁ ተማሪዎች መካከል 200 የሚሆኑት በሀገራቸው መንግስት በተለያዩ ቦታዎች ተቀጥረው አገልግሎት እየሰጡ በመሆኑ ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

ሁለቱ አካላት በነበራቸው ውይይት ኢትዮጵያ ነጻ የትምህርት እድል የምትሰጣቸው ደቡብ ሱዳናውያንን በሚመለከት፣ ዩኒቨርሲቲ ለዩኒቨርስቲ የሚደረግ ትብብር፣ በጋራ የሚሰሩ ጥናትና ምርምር ሥራዎች እንዲሁም ለደቡብ ሱዳን የትምህርት ሚኒስቴር እና ለከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የአቅም ግንባታ ሥልጠናና ድጋፍ በሚደረግባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በመድረኩም በኢትዮጵያ ነጻ የትምህርት እድል ያገኙ ደቡብ ሱዳናውያን ከመኝታ፣ ከምግብ  እንዲሁም ከኢሚግሬሽን ጋር ተያይዞ ያሉ ወጪዎች በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈነው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተጠቅሷል።

በመጨረሻም ክቡር ሚኒስትሩ በደቡብ ሱዳን ተገኝተው ጉብኝት እንዲያደርጉ የደቡብ/ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋብዘዋቸዋል።

የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በተመለከተ ለተማሪዎችና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን

Recent News
Follow Us