News Detail
Jan 01, 2022
580 views
በትምህርት ብርሃን ምዘና ከ540 ሺ በላይ ለሚሆኑ ጎልማሶች የዕውቅና ሰርተፊኬት መሰጠቱ ተገለፀ፡፡
“የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ለህብረ-ብሔራዊ አንድነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት” በሚል ርዕስ ሀገር-አቀፍ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በሲምፖዚየሙ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ባለድርሻ ከሆኑ ፌዴራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤት፤ ከክልል ትምህርት ቢሮ፣ከማህበረሰብ የመማሪያ ማዕከላት የተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ዳይሬክተር ጀነራል ታምራት ይገዙ(ዶ/ር) ጎልማሶችና መደበኛ ያለሆነ ትምህርት ስርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ ባለፉት ዓመታት በርካታ ተግባራት ቢከናወኑም ከውጤት አንፃር አጥጋቢ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡
አሁንም 6 ሚሊየን ህፃናት ከመደበኛ ትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑበት እንዲሁም ከ30 ሚሊየን በላይ ዜጎች ማንበብ፣መፃፍና ማስላት የማይችሉ መኖራቸውን መረጃ ያሳያል ብለዋል፡፡
በትምህርት ብርሃን ምዘና እስካሁን ተመዝነው አጥጋቢ ውጤት ላመጡ ከ540ሺ በላይ ጎልማሶች የዕውቅና ሰርተፊኬት የተሰጣቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ሀገር-አቀፍ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ስኬቶችና ተግዳሮቶችን በተመለከተ የመነሻ ሰነድ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል፡፡
በሲምፖዚየሙ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ለሀገርና ለዜጎች የተፋጠነ እድገት የሚያበረክተውን አስተዋፆ በመረዳት ውጤታማ ውይይት በማድረግ ቀጣይ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
Recent News
Sep 02, 2025
Aug 29, 2025
Aug 28, 2025
Aug 23, 2025