News Detail
        
            Mar 14, 2025
        
        
            
            851 views
        
    
    
    
    የትምህርት ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ጋር ተወያዩ፤
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ጋር በትምህርት ዘርፉ በትብብር ሊሰሩ በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓትን ለማስተካከል የቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተሰሩ ያሉ የሪፎርም ሥራዎችን ለአምባሳደሩ አብራርተውላቸዋል፡፡
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ በበኩላቸው በኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓቱን ለመቀየር እየተወሰዱ ያሉ ሪፎርሞችና የተያዙ ራዕዮችን እንገነዘባለን ያሉ ሲሆን በቀጣይ የትምህርት ዘርፉን ለመደገፍ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
ሁለቱ አካላት በነበራቸው ውይይቶች ለትምህርት ዘርፉ የሚደረጉ ድጋፎች ለታለመላቸው አላማ ይውሉ ዘንድ ከመተግበራቸው አስቀድሞ መወያየት እንደሚያስፈልግም ተስማምተዋል፡፡