News Detail
        
            Aug 16, 2022
        
        
            
            2.6K views
        
    
    
    
    በጦርነት እና ግጭቶች ለወደሙ ትምህርት ቤቶች መልሶ ግንባታ ሁሉም አሻራውን እንዲያሣርፍ ተጠየቀ።
                    በጦርነት እና በተለያዪ ግጭቶች በአፋር ፣ አማራ፣ ቤንሻንጉል ፣ ኦሮሚያ እና ደቡብ ክልሎች የወደሙ ከ1ሺሕ 300 በላይ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት  ከ80 ቢሊዬን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ የትምህርት ሚንስትሩ  ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ   አፋር ክልል ጭፍራ ላይ ከመገናኛ ብዙሃን  ጋር በነበራቸው ቆይታ 
            አብራርተዋል።
ሚንስትሩ በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በጦርነቱ ውድመት የደረሠበትን የጭፍራ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በአዲሱ የኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች ድዛይን መልሶ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።
ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት የተለያዩ አጋር ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ መቅረቡን አስታውሠው መንግስት ባለው አቅም የመልሶ ግንባታውን እውን ለማድረግ ይተጋል ብለዋል።
ይህንን ትምህርት ቤት የሚሰራውን ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ያመሰገኑ ሲሆን ሁሉም የበኩሉን በመወጣት አሻራውን እንዲያሣርፍ ጥሪ አድርገዋል።
የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኤለማ አቡበከር መንግስት ህብረተሠቡ የደሰሠበትን ጉዳትና የከፈለውን ዋጋ ከግምት በማስገባት ት/ቤቶችን በተሻለ መልኩ ለመገንባት በመወሠንና ተግባራዊ ለማድረግ እየሄደበት ያለውን ርቀት አስመልክቶ ምስጋና አቅርበዋል።
ሠዎች ለሠዎች የተባለ ግብረ ሠናይ ድርጅት በመላው ኢትዮጵያ ተጠሪ አቶ ይልማ ታዬ መንግስት ባቀረበው ዲዛይን መሠረት ጭፍራ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤትን ጨምሮ በክልሉ 8 ትምህርት ቤቶችን ሙሉ በሙሉ አስገንብቶ በተቀመጠለት ጊዜ ለማስረከብ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።