News Detail

National News
Dec 20, 2025 18 views

በኢትዮጵያና ህንድ መካከል በትምህርት ዘርፍ ያለው ትብብር እየተጠናከረ መምጣቱን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ አስታወቁ። ‎የሦስተኛ ዲግሪ ነጻ የትምህርት እድል ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ይፋ ሆኗል።

የከፍተኛ የትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ መርሃ ግብሩን ሲከፍቱ እንደገለጹት በሁለቱ አገራት መካከል በትምህርት ዘርፍ ያለው ወዳጅነትና ትብብር እየተጠናከረ በመሄድ ላይ ነው።
‎ይፋ የሆነው የድህረ ምረቃ ትምህርትና ምርምር መርሃ ግብርም የድህረ ምረቃ ትምህርት አቅም በመገንባት በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ትልቅ ሽግግር ለማድረግ እንደሚያግዝ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል።
ከህንድ የቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር በትብብር የሚሰጠው የትምህርት እድል፣ የምርምር፣ ቴክኖሎጅና ፈጠራን በማሳደግ ብቁ የሰው ሀይል በጥራት ማቅረብ እንደሚያስችል ጠቅሰዋል።
‎የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) በበኩላቸው የመርሃ ግብሩ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በኢንጂነሪንግና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያለውን የሦስተኛ ዲግሪ እጥረት እንደሚያቃልል ተናግረዋል።
‎በህንድ ካሉ 8 የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች ጋር በተደረሰው ስምምነት መሠረት በየዓመት 250 በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ደግሞ 1,250 ተማሪዎች ነጻ የዶክተሬት ትምህርት እድል እንደሚያገኙ ዶክተር ኤባ ጠቅሰዋል።
‎የመምህራንና የተማሪዎች ልማት ዴስክ ኃላፊ አቶ በየነ ተዘራ በበኩላቸው የፕሮግራም አስተዳደርና አፈጻጸምን በተመለከተ በቀጣይ ከሚመለከታቸው የከፍተኛ ተቋማት ጋር ምክክርና የመረጃ ልውውጥ እንደሚደረግ ተናግረዋል።
‎በፕሮግራሙ ላይ በበይነ መረብ የተሳተፉት ስምንት (😎 የህንድ ቴክኖሎጂ ተቋማት ስለተቋሞቻቸውና በሦስተኛ ዲግሪ መርሃ ግብር ስልጠና ስለ የሚሰጡባቸው ፕሮግራሞች አስመልክተው ገለጻ አድርገዋል።
‎በፕሮግራሙ ላይ ከሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ ፕሬዚዳንቶችና ምክትል ፕሬዚዳንቶች ተገኝተዋል።
Recent News
Follow Us