News Detail
Feb 12, 2026
11 views
ትምህርት ሚኒስቴር ያሳተማቸው የቅድመ አንደኛ እና የአንደኛ ደረጃ ትምህርት መጽሐፍት ከጅቡቲ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት መጀመራቸው ተገለጸ።
የትምህርት ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ባገኘው ድጋፍ ያሳተማቸው የቅድመ አንደኛ እና የአንደኛ ደረጃ መጽሃፍት በገላን የመጽሃፍት ክዘና ማዕከል እየተራገፉ ይገኛል።
የትምህርት ሚኒስቴር የአንደኛ ደረጃ ትምህርት መጽሃፍትን አንድ ለአንድ ለማድረስ ከአጋር አካላት ባገኘው ድጋፍ ከ23.9 ሚሊየን በላይ መጽሃፍትን በማሳተም ከጅቡቲ ወደ ሃገር ውስጥ ማጓጓዝ መጀመሩን የሥርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ ተጠባባቂ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዛፉ አብርሃ ገልጸዋል።
በዚህም ከ30 ኮንቴነር በላይ መጽሃፍት በገላን የክዘና ማዕከል መድረሳቸውን የገለጹት ሥራ አስተፈጻሚዋ አሁን የደረሱትን መጽሐፍት ክልሎች እንዲረከቡ ከስር ከስር የማሰራጨት ሥራ ይሰራል ብለዋል። በትክክል ለተማሪዎች መሰራጨታቸውን የማረጋገጥ ሃላፊነት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
መጽሐፍቶቹም ሲታተሙ በሁሉም ክልል እና ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ዞኖች የሚያሳይ መለያ ኪውአር ኮድ (QR CODE) የተካተተ በመሆኑ የሁሉንም ዞኖች መጽሐፍቶች በመለያ ኮዳቸው መከታተል የሚቻልበት አሰራር መኖሩንም አብራርተዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መጽሐፍትን አንድ ለአንድ ያደረሰ ሲሆን የቅድመ አንደኛ እና የአንደኛ ደረጃ መጽሃፍትን አንድ ለአንድ ለማድረስ እንዲቻል ለክልሎች ድጋፍ በማድረግ ረገድ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።
Recent News
የአማሮ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።
Feb 27, 2026
አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርስቲ አመራሮች ኃላፊነታቸውን በትክክል እንዲወጡ ተጠየቀ ።
Feb 13, 2026