ዜና

የአራዳ ክፍለ ከተማ በሰሜን ወሎ የወደመ አንድ ትምህርት ቤትን መልሶ እንደሚገነባ አስታወቀ፡፡

በሰሜን ወሎ ዞን በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የወደመ አንድ ትምህርት ቤት መልሶ ለመገንባት ሃላፊነቱን እንደሚወስድ የአራዳ ክፍለ ከተማ አስታወቀ፡፡

የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አባወይ ዮሐንስ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ወረራ በፈጸመባቸው የአማራ እና የአፋር ክልል አካባቢዎች ንጹሃንን ከመግደል ባለፈ ሕዝብ የሚገለገልባቸውን ተቋማት መዝረፉንና ማውደሙን አስረድተዋል፡፡ 

የወደሙ ተቋማትን  መልሶ  የመገንባትና አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ የሁሉንም ርብርብ ይጠይቃልም ብለዋል።

 ስለዚህም  ሥራ አስፈጻሚው በሰሜን ወሎ ዞን የወደመ አንድ ትምህርት ቤት መልሶ በመገንባትም  ክፈለ ከተማው ኀላፊነቱን እንደሚወጣ ገልፀዋል፡፡

ምንጭ-አሚኮ