ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ በታች ባለው ክፍት የሥራ መደብ ላይ ባለሙያዎችን አወዳድሮ በኮንትራት መቅጠር ይፈልጋል።

 

 1. የስራ መደቡ መጠሪያ ፦የልዩ ድጋፍ ባለሙያ
 2. ተፈላጊ ችሎታ፦    ከታወቀ ዩኒቨርስቲ  በትምህርት እቅድናሥራ አመራር/በትምህርት አስተዳደር  በትምህርት ፖሊሲና ሥራ አመራር እና በስነ -ትምህርት/ፔዳጎጂ/የመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ ያለው/ላት
 3. የስራ ልምድ፦     ለመጀመሪ ዲግሪ 8 ዓመት#ለ2ኛ ዲግሪ 6 ዓመት ያለው /ያላት
 4. በአርብቶ አደር ክልሎች በትምህርት ልማት ዘርፍ የሰራ/ች ቢሆን ይመረጣል
 5. የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ ማህበራዊና ባህላዊ እሴቶች ላይ በቂ እውቀት ያለው/ላት
 6. በአራቱ ታዳጊ ክልሎች ተዘዋውሮ ለመስራትና የረጅም ጊዜ የመስክ ስራን ለማከናወን ፈቃደኛ የሆነ/ች
 7. በእንግሊዝኛ ቋንቋ ዕቅድና ሪፖርት የማዘጋጀት ችሎታ ያለው/ላት
 8. መሠረታዊ የኮምፒውተር ክህሎት ያለው/ላት
 9. በትምህርት ፖሊሲ እና ስትራቴጂ እንዲሁም በአምስተኛው የትምህርት ዘርፍ ልማት እቅድ በቂ ግንዛቤ ያለው/ት
 10. ብዛት   ፦   1/አንድ/
 11. ደመወዝ ፦ 9000.00/ዘጠኝ ሺህ ብር/
 12. ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ።

 

የመመዝገቢያ ቀንና ቦታ፦ ማስታወቂያው ከወጣበት ከጥር 16 ቀን 2009 ጀምሮ ባሉት/ሰባት / ተከታታይ  የሥራ ቀናት ቢሮ  ቁጥር 28

 

ማሳሰቢያ

 • ከተጠቀሰው የትምህርት ደረጃና የሥራ ልምድ በላይ አግባብነት ያለው ማስረጃ የሚያቀርቡ ሊወዳደሩ ይችላሉ።
 • የሚቀርበው የሥራ ልምድ ማስረጃ  ይከፈለው የነበረውን የደመወዝ መጠን መግለጽ አለበት።
 • የሚቀርበው የሥራ ልምድ ማስረጃ ከግል ድርጅት ከሆነ የሥራ ግብር ስለመከፈሉ ማረጋገጥ ይኖርበታል።
 • ተመዝጋቢዎች በምዝገባ ወቅት ደመወዛቸውን የሚገልጽ አግባብ ያለው የሥራ ልምድና የትምህርት ማስረጃ ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
 • ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ በውስጥ ማስታወቂያ ይገለጻል።

 

አድራሻ፦ አራት ኪሎ

ስልክ ቁጥር 011-155-31-33 EX. 411

ፖስታ ሣጥን ቁጥር 1367

ትምህርት ሚኒስቴር