የጽ/ቤቱ ግብ፣ አላማዎች

የጽ/ቤቱ ግብ፣ አላማዎች
  1. ዋና ዋና ግቦች
    • የተገልጋይ እርካታ ማሣደግ
    • የሀብት አጠቃቀም ውጤታማነትን ማሻሻል
    • የውስጥ አሠራር ማሻሻል /የሥራ ግንኙነትን ማሻሻል/
    • የአገልግሎት አሠጣጥ ቅልጥፍናና ውጤታማነትን ማሻሻል
    • የክትትል ግምገማና ድጋፍ አሠራር ማጐልበት
    • ተቋማዊ የትምህርት ልማት ሠራዊት አቅም ማሣደግ
    • የተቋሙን የአሠራር ስርዓት ማሻሻል
    • ዓላማዎች /አጠቃላይ - አላማዎች/
    • ሠራተኛውን በፀረ ሙስና ትምህርቶች በስራ ዲስፒሊን፣ በሙያ-ሰነ ምግባር፣ በህዝብ አገልጋይነት ስሜት በማነፅ የነቃና ሙስናን ሊሸከም የማይችል ሰራተኛ እንዲፈጠር ጥረት የማድረግ
    • መስሪያ ቤቱ የሙስና ወንጀልና ብልሹ አሠራርን የመከላከል
    • የሙስና ወንጀል ብልሹ አሠራር እንዲጋለጥና እንዲመረመር አጥፊዎች ላይ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ ጥረት ማድረግ
  2. እስትራቴጂ
    • ከተቋሙ ወደ ስነ-ምግባር መከተታያና ቅሬታ ማስተናገጃ ጽ/ቤት የወረዱ ግቦችን ማሣካት፣
    • ደንቦች፣መመሪያዎች የአሠራር ስርአቶችን በአግባቡ ስራ ላይ መዋላቸው መከታተል፣
    • በየደረጃው የቅሬታ አፈታት ስርዓት የተጠናከረ መሆኑን መከታተል፣
    • የለውጥ ስራዎችን መደገፍ የፈፃሚውን አመለካከትና ክህሎት ማሣደግ፣
    • የመ/ቤቱን አገልግሎት ለሚፈልጉ ሁሉ በቀልጣፋ ሁኔታ ውጤታማ አገልግሎት መስጠት፣
    • የተቋሙ ሰራተኞች በመልካም ዲሲፒሊን ሥነ-ምግባር ታንፀው የዕለት ተግባራቸውን እንዲያከናውኑና የሰነ ምግባር ብልሸነትና ኪራይ ለሰብሣቢነትን
    • ለዩኒቨርሲቲዎች የስነ-ምግባር መከታተያና ፀረ- ሙስና ዳይሬክትሬቶች ሙያዊ ድጋፍ ማድረግ፣
    • የህዝብ ክንፍን በተደራጀ አግባብ ከተቋሙ ጋር የስራ ግንኙነት እንዲፈጠር ማስቻል፣
    • /ሙስናን/ እንዲታገሉ በማድረግ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ፡፡
  3. የሚያከናውናቸው ተግባራት
    • አብዛኛው ተገልጋይ እርካታ ያጣበትን አገልግሎት አካባቢ መለየትና መፍትሄ ማፈላለግ
    • የሀብት አጠቃቀም ውጤታማነትን ማሻሻል
    • ከተለያዩ ተቋማት ጋር ግንኙነት በመፍጠር ምርጥ ተሞክሮ መቀመርና ማስፋፋት
    • የሃብት ማሣወቅና ምዝገባ ሥርዓትን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማደረግ
    • ከሥራ ክፍሎች ጋር በመሆን አገልግሎት አሠጣጥ ዳሰሳ ጥናት ማካሄድ
    • በደንበኞች ግብረ መልስ ላይ የተመሠረተ ክትትል ግምገማና ድጋፍ መስጠት
    • የፈፃሚዎችን የክህሎትና የአመለካከት ክፍተት በመለየት በየደረጃው ሥልጠና የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት
    • የወጡ ደንቦችና ስታንዳርዶችን በመፈተሸ ተግባራዊነታቸውን ማረጋገጥ
    • የክፍሉን እቅድ ሪፖርት ማዘጋጀት የሚከለሰውንም በወቅቱ እቅዱን መከለስ፣ ማሻሻል
  4. ከተመሠረቱ እስካሁን ድረስ የተገኙ ውጤቶች /በ2007 ዋና ዋናዎቹን/
    • ተገልጋዮች በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያጋጠማቸውን ጠንካራም ሆነ መስተካከል የሚገባቸውን ነጥቦች በነፃነት እንዲገልፁ አግዟል
    • የሀብት አጠቃቀም ላይ ግልፀኝነትና ተጠያቂነትን መኖሩን በመገንዘብ ያለአግባበብ የመስሪያ ቤቱ የሀብት ብክነት እንዳይኖር ግንዛቤ ፈጥሮአል
    • አዳዲስ ተቀጥረው ለሚመጡ የመስሪያቤቱ ሠራተኞች በየግዜው በሰነ- ምግባር መመሪያዎች፣ህጐች በማስተማር ከጽ/ቤቱ ጐን በመሆን የፀረ-ኪራይ ሰብሰቢነት ትግል ስልት በማዳበር እና ራሳቸው ከኪራይ ሠብሣቢነት ፅዱ መሆን እንዳለባቸው ግንዛቤ ጨብጠዋል
    • በአገልግሎት አሰጣጣችን ሊገጥሙ የሚችሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፈተሽ በአፋጣኝ በማረም የተገልጋዩ እርካታ እንዲጨምር አግዟል
    • በተደረገው ክትትልና ግምገማ ግብረመልስ መሠረት በ2007ዓ.ም 82 የተለያዩ ቅሬታዎችና ጥቆማዎችን በአካል ወርዶ በማጣራትና በመረጃ በማስደገፍ ሁሉንም ተገቢ ምላሽ እንዲሰጥ ተደርጐል
    • የመስሪያቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና ስራቸው ከመንግስት ሃብት ጋር ቀጥታ ትስስር ያላቸውን ፈፃሚዎች ጨምር በቁጥር 26 እድሳት የሚመለከታቸው ነባር ሰራተኞችና ኃላፊዎች እንዲሁም 14 አዲስ ወደ መ/ቤቱ የመጡ ሃብታቸውን ማሣወቅና ማስመዝገብ የሚመለከታቸው ለፌዴራል ፀረ ሙስና ስነ ምግባር ኮሚሽን ጋር በመሆን እንዲያስመዘግቡ ተደርጐአል፡፡
  5. በሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ የተቀመጡ
    • 5.1 ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች
    • አብዛኛው ተገልጋይ እርካታ ያጣበትን የአገልግሎት አካባቢ መለየትና መፍትሄ ማፈላለግ
    • ውጤታማ የሃብት አጠቃቀም
    • 5.2 በ2008ዓ.ም የታቀዱ ውጤቶች
    • ተገልጋዮች ቅሬታቸውን የሚያቀርቡበት ሥርዓት እንዲያውቁ ምቹ ሁኔታዎች ይፈጠርላቸዋል፤ ቀልጣፋ አገልግሎት በማግኘት የተገልጋይ እርካታ ከፍ ይላል፣
    • የቅሬታ ምንጮችን በመለየት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን መፍትሄ ለማፈላለግ ያስችላል፣
    • የጽ/ቤቱ አድራሻ በመታወቁ ቅሬታ ለማቅረብና ጥቆማ ለመስጠት ለተገልጋዮች ምቹ ሁኔታይፈጥራል፣
    • ውጤታማ የሃብት አጠቃቀም

Directorates and Departments Directorates and Departments