የአፍ መፍቻ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማት ዳይሬክቶሬት

 1. ዳራ

የአፍ መፍቻ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማት በትምህርትና ስልጠና ፖሊሲው ውስጥ ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው የትምህርት ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነው። ከዚህ አንጻር ብሔር-ብሔረሰቦችን በራሳቸው ቋንቋ እንዲማሩ ማድረግ፣እንዲሁም ለጋራ ግንኙነት እንዲረዳ አንድ አገር አቀፍና አንድ ዓለም አቀፍ ቋንቋ ማስተማር የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲው ግብ ሀኖ ተቀምጧል። ይህን ግብ ለማሳካት ስምንት ስትራቴጅዎች በግልጽ የተቀመጡ ሲሆን የአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት ልማትን በተመለከተ በአፍ መፍቻ ቋንቋ መማር ትምህርታዊ/ፔዳጎጂካዊ ጠቀሜታ ስላለውና ብሔር-ብሔረሰቦች በራሳቸው ቋንቋ የመጠቀም መብታቸውን ስለሚያረጋግጥ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትና ተመጣጣኝ ሥልጠናዎች በብሔር-ብሔረሰብ ቋንቋ እንደሚሰጡ በግልጽ ተቀምጧል።

ከዚህ አኳያ ብሔር-ብሔረሰቦች አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረጉ በራሳቸው ቋንቋ ወይም በብሔራዊ ክልላዊና በሀገር አቀፍ ሥርጭታቸውና በተናጋሪ ብዛታቸው መሠረት በሚመርጡት ቋንቋ ሊማሩ እንደሚችሉ፤ በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚደረገው ግንኙነት የአማርኛ ቋንቋ በትምህርትነት እንደሚሰጥና ለአፀደ ህጻናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት መምህራን ሥልጠና በአካባቢው ት/ቤቶች ለማስተማሪያነት የተመረጠው ቋንቋ የማሰልጠኛ ቋንቋ እንደሚሆን በትምህርትና ስልጠና ፖሊሲው ውስጥ ትኩረት ተሰጥቷቸዋል።

የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማትን በተመለከተም ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት እንደሚሰጥና ለሁለተኛ ደረጃና ለከፍተኛ ትምህትርት መስጫ ቋንቋ ሆኖ እንደሚያገለግል ፖሊሲው በግልጽ አስቀምጧል። የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲው የዜጎችን ብዝኀ-ልሣን መሆን በሚገባ ትኩረት የሰጠ ከመሆኑ አኳያ ባህላዊና ዓለም አቀፋዊ  ግንኙነቶችን ለማሳደግ እንዲያግዝ ተማሪዎች ከብሔር-ብሔረሰብ ቋንቋቸውና ከውጭ ቋንቋዎች መካከል እንደ ፍላጎታቸው ቢያንስ አንድ የሀገር ውስጥ ቋንቋና አንድ የውጭ ቋንቋ መርጠው በተጨማሪ መማር የሚችሉበት ሁኔታ ሊመቻች እንደሚገባ ይደነግጋል። በመሆኑም የቋንቋ ትምህርት ልማት በጥራትና በተጠናከረ ሁኔታ እንዲተገበር በሁሉም ደረጃ ተገቢ ጥረት ማድረግ  እንደሚገባ ፖሊሲው በግልጽ አስቀምጧል።

ባለፉት ሁለት አሰርት ዓመታት የዜጎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የመማር መብታቸው በመረጋገጡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ተሳትፎአቸው አድጓል።የእንግሊዝኛ ቋንቋም ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት እየተሰጠ ይገኛል። ከአፍ መፍቻ ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት መስጫነት የሚደረገው ሽግግር እንደየክልሎች ተጨባጭ ሁኔታ ከተለያዩ የክፍል ደረጃዎች ይጀምራል። ከዘጠነኛ ክፍል ጀምሮ የአጠቃላይ እና የመሰናዶ ሁለተኛ ደረጃ እና የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት በወጥነት በእንግሊዝኛ ቋንቋ እየተሰጠ ይገኛል።

ከዚህ አንጻር የቋንቋ ትምህርት ልማትን በፖሊሲው በተቀመጠው መሰረት በባለቤትነት ለመምራትና ለማሳለጥ ሲባል የአፍ መፍቻና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማት ዳይሬክቶሬት ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ተፈቅዶ በ2007 በጀት ዓመት ስራ ጀምሯል።

 1. የአፍ መፍቻና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማት ዳይሬክቶሬት አደረጃጀት

የአፍ መፍቻና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማት ዳይሬክቶሬት በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ከሚገኙ አደረጃጀቶች አንዱ ሲሆን በሦስት የአንድ ለአምስት ቡድኖች የተደራጀ ነው። እነርሱም የአፍ መፍቻ ቋንቋ፣ የእንግሊዝኛ ቋንቋ እና የድጋፍ ሰጭ ሠራተኞች የአንድ ለአምስት ቡድኖች ናቸው። የአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት ልማት የአንድ ለአምስት ቡድን አምስት የአፍ መፍቻ ቋንቋ ከፍተኛ ባለሙያዎችን ፤ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማት የአንድ ለአምስት ቡድን ደግሞ አንድ ረዳት ፀሐፊ እና አምስት ከፍተኛ ባለሙያዎች በጥቅሉ ስድስት ሠራተኞችን ያካትታል። የድጋፍ ሰጭ ቡድኑ ሁለት ፀሐፊዎችና አንድ የመልዕክት ሠራተኛ በድምሩ ሦስት ሠራተኞች አሉት። የሥራ ክፍሉ  ዳይሬክተሩን ጨምሮ በአጠቃላይ አስራ አምስት ሠራተኞችን በመያዝ የተሰጠውን የቋንቋ ትምህርት ልማት የማሳለጥ ተልዕኮ ለመወጣት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

 1. ዓላማ

የአፍ መፍቻ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማት መርሀ ግብርን  በውጤታማነት በመተግበር የመምህራንን የቋንቋ ክህሎትና የማስተማር ሥነ-ዘዴ ማሻሻልና በተማሪዎች የቋንቋ ክህሎትና የትምህርት ውጤታማነት ላይ ጉልህ ድርሻ እንዲኖረው ማድረግ   

 1. የአፍ መፍቻና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማት ዋና ዋና ግቦች
  • ተጨባጭ ሁኔታዎችንና መረጃዎችን መሰረት ባደረገ መልኩ የተነደፉ ሀገራዊ የቋንቋ ትምህርት ልማት ግቦች
  • የቋንቋ ትምህርት ልማትን በፍትሐዊነት ለማፋጠን የተቀመጠ  ሀገራዊ አቅጣጫ
  • የቋንቋ ትምህርት ልማትን ለማሳለጥ የተዘረጋ ሥርዓት
  • የቋንቋ ትምህርት ልማትን በውጤታማነት ለመተግበር የተፈላለገና የተመደበ ሀብት
  • የቋንቋ ትምህርት ልማት ውጤታማነትን ለመፈተሽ የተዘረጋ የድጋፍ፣ የክትትል፣ የግምገማና የግብረ-መልስ ሥርዓት
 2. የአፍ መፍቻ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማት ዋና ዋና ተግባራት
  • ተጨባጭ ሁኔታዎችንና መረጃዎችን መሰረት ባደረገ መልኩ የአፍ መፍቻ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማት ግቦችን መንደፍ፣ ስትራቴጅክ እና ዓመታዊ እቅድ ማዘጋጀትና መተግበር
  • በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከናወኑ የአፍ መፍቻና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማት ተግባራት አፈጻጸም ከታለሙ አጠቃላይ ግቦች አንፃር እያስገኙ ያለውን የአጭርና የመካከለኛ ጊዜ ውጤት መከታተልና መገምገም
  • ስታንዳርድን መሰረት ያደረገ እና ሀገራዊ አቅጣጫን የሚከተል የቋንቋ ትምህርት ልማትን ለመተግበር የሚረዳ የመካከለኛ ጊዜ ሀገር አቀፍ የአፍ መፍቻ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማት ስትራቴጅ  ማዘጋጀት
  • በተማሪዎች የአፍ መፍቻ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት መሻሻል ላይ አዎንታዊ ለውጥ በሚያመጣ እና የስልጠና ፍላጎትን ባገናዘበ መልኩ በቅድመ-ሥራ እና በሥራ ላይ ለሚገኙ የአፍ መፍቻ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህራን የአፍ መፍቻ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትና የማስተማር ሥነ-ዘዴ ማሻሻያ  ስልጠና ሞጅዩሎችን ማዘጋጀትና ስልጠናዎችን መሰጠት
  • በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ሌሎች የትምህርት ዓይነቶችን በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚያስተምሩ መምህራን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ማሻሻያ ስልጠና ፍላጎትን መሰረት ያደረጉ የስልጠና ሞጅዩሎችን ማዘጋጀትና ስልጠና መስጠት፣ ስልጠናው የተማሪዎችን በእንግሊዝኛ ቋንቋ ሌሎች የትምህርት ዓይነቶች የመማር ሂደት ማሻሻሉን መከታተል
  • የቋንቋ ትምህርት ልማት ሥርዓትን እንደየክልሎቹ ተጨባጭ ሁኔታ ለመዘርጋት የሚረዱ  ስታንዳርዶችን፣  ማንዋሎችንና  መመሪያዎችን ከክልሎች ጋር በጋራ ማዘጋጀት
  • በቋንቋ ትምህርት ልማት አተገባበር ላይ የታዩ ጠንካራና ደካማ አፈጻጸሞችን፣ልዩ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችንና የወደፊት አቅጣጫዎችን በመጠቆም የቋንቋ ትምህርት ልማትን በዘላቂነት ለማሳለጥ የሚያግዙ ጥናቶችና ምርምሮችን ማካሄድ
  • በቋንቋ ትምህርት ልማት አተገባበር ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ወቅታዊ የጋራ ምክክር መድረኮች፣ የልምድና የተሞክሮ ልውውጦች፣ ድጋፎች፣ ክትትሎች፣ ግምገማዎች ማካሄድና ግብረ-መልስ መስጠት
  • ከልማት አጋሮችና ከመንግስት የቋንቋ ትምህርት ልማት እቅድ ማስተግበሪያ የፋይናንስ ሀብት ማፈላለግ፣መመደብና አፈጻጸሙን መከታተል
  • ትምህርት ቤት ተኮር የአፍ መፍቻ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህራን የቋንቋ ክህሎት ማሻሻያ  የድጋፍ መርሀ ግብር የተከታታይ የሙያ ማሻሻያ መርሀ ግብር አካል ሆኖ የሚተገበርበትን ማዕቀፍና ማንዋል በማዘጋጀት በመተግበርና ውጤታማነቱን መከታተል  
  • የአፍ መፍቻ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማትን ከትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም ትግበራ ጋር በማስተሳሰር በየደረጃው የሚገኙ ተማሪዎች በየትምህርት ቤቶቻቸው በአፍ መፍቻ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማት ክበባት እንዲደራጁና የቋንቋ ክህሎታቸውን እንዲያሻሽሉ ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣
  • የተማሪዎችን የአፍ መፍቻ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት እና የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት በንቃት መሳተፍ፣
  • ለክልሎች በቋንቋ ትምህርት ልማት ላይ የአቅም ግንባታና የግንዛቤ  ማስጨበጫ ስልጠናዎች መስጠት ፣ ወቅታዊ ድጋፍና ክትትል ማድረግ፤
 3. ከዳይሬክቶሬቱ ምስረታ ጀምሮ የተገኙ ውጤቶች
  • የአፍ መፍቻ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማት መርሀ ግብርን በባለቤትነት የሚመራ አደረጃጀት በፌዴራል ደረጃ ተፈጥሯል።ዳይሬክቶሬቱ የሚመራበት የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ተዘጋጅቷል።
  • በ2008 ዓ.ም ብቻ ለ66,144 (ወንድ 35,771 ሴት 30,373)  የ1-4ኛ ክፍል የአፍ መፍቻ ቋንቋ መምህራን በተከለሰው የአፍ መፍቻ ቋንቋ ሥርዓተ-ትምህርት መሰረት የቋንቋ ክህሎትና  የማስተማር ሥነ-ዘዴ ማሻሻያ ስልጠና ተሰጥቷል። ስልጠናው ያስገኘው የአጭር ጊዜ ውጤታማነትም በመስክ ጉብኝት ተገምግሟል
  • በ2008 ዓ.ም በተካሄደው ክትትልና በተሰበሰበው መረጃ መሰረት በሀገሪቱ ውስጥ በትምህርት ዓይነትና በትምህርት መስጫነት እያገለገሉ የሚገኙ የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች ብዛት 51 መሆናቸው የታወቀ ሲሆን 11ዱ የግእዝ፣ 40ዎቹ ደግሞ የላቲን ስክሪፕት እንደሚጠቀሙ ተለይቷል
  • በመምህራን ትምህርት ኮሌጆች የአፍ መፍቻ ቋንቋ ማሻሻያ ማዕከላት ረቂቅ መመሪያ ተዘጋጅቷል  
  • በ2008 ዓ.ም ብቻ ለ3,556 የመጀመሪያ  እና ለ1,143 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህራን  በድምሩ ለ4,699 የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህራን የክህሎት  እና የማስተማር ሥነ-ዘዴ ማሻሻያ የስራ ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
  • በመምህራን ትምህርት ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ማዕከላት ድጋፍና ክትትል ተደርጓል። የማዕከላቱ ዓመታዊ ጉባኤ ሁለት ጊዜ ተካሂዷል። የማዕከላቱ መመሪያም ተከልሷል።
  • እንግሊዝኛን በማስተማሪያ ቋንቋነት ተጠቅመው ሌሎች የትምህርት ዓይነቶችን (ሂሳብ፣ሣይንስ፣ወዘተ) የሚያስተምሩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሻሻል የሚረዱ የቋንቋ ክህሎት ማሻሻያ ስልጠና ሞጅዩሎችን ለማዘጋጀት የስልጠና ፍላጎት የመስክ ጥናት ተካሂዷል።በጥናቱ መሰረትም ሦስት ዓይነት ሞጅዩሎች ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግ ታውቋል።
  • የአፍ መፍቻ  እና  የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማት ሀገር አቀፍ ስትራቴጅ ለማዘጋጀት የሚረዳ ሀብት ለማፈላለግ ፕሮፖዛል ተዘጋጅቷል። በዚህ መሰረት ከ Quality Education Strategic Support Project/QESSP የቴክኒክና የፋይናንስ ድጋፍ ተገኝቷል።  
  • ከREAD-TA ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ከቅድመ-መደበኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ሥርዓተ-ትምህርት ለመከለስ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ የስራ ክፍሉ ንቁ ተሳትፎ አድርጓል 
  • ከህዝብ ክንፍ፣ ከክልሎች፣ ከልማት አጋሮችና ከትምህርት ሚኒስቴር  ልዩ ልዩ የስራ ክፍሎች ጋር የጋራ እና የትስስር እቅድ በማቀድና ወደ ትግበራ በመግባት የአፈጻጸም ግምገማዎችን በጋራ ለማካሄድ ተችሏል።  በአፍ መፍቻና በእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህራን ስልጠና ላይ ለክልሎች ድጋፍ ተሰጥቷል።
 4. የዳይሬክቶሬቱ  ቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች
  • የአፍ መፍቻ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማት ሀገር አቀፍ ስትራቴጅ፣ ስታንዳርዶች፣ ማንዋሎችና መመሪያዎች ማዘጋጀት  
  • በተማሪዎች የንባብና የጽሁፍ ክህሎት መሻሻል ላይ አዎንታዊ ድርሻ ሊኖረው በሚችል መልክ  የአፍ መፍቻ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትና የማስተማር ሥነ-ዘዴ ማሻሻያ ስልጠና ለመምህራን በተከታታይ መስጠትና የአጭርና የመካከለኛ ጊዜ ውጤቱን መፈተሽ
  • ትምህርት ቤት ተኮር የአፍ መፍቻ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህራን የቋንቋ ክህሎትና የማስተማር ሥነ-ዘዴ ማሻሻያ ድጋፍ አገልግሎት ሥርዓትን መዘርጋትና ማጠናከር 
  • በየክልሎች ከአፍ መፍቻ ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ ማስተማሪያነት በሚደረገው የሽግግር ሂደት ላይ ጥናት ማካሄድና የአተገባበር ጥንካሬዎች፣እጥረቶችና ልዩ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በመለየት ለውሳኔና ለእቅድ ጥቅም ላይ ማዋል
  • ለአፍ መፍቻ እና ለእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማት የሚያስፈልግ ሀብት ማፈላለግ፣ መመደብና ጥቅም ላይ ማዋል 
  • ጠንካራ የአፍ መፍቻ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማት መርሀ ግብር የድጋፍ፣ የክትትል፣ የግምገማና የግብረ-መልስ ሥርዓት በመዘርጋት የአፍ መፍቻና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማት መርሀ ግብርን የአተገባበር ጥንካሬ እና   እጥረት  በየጊዜው መፈተሽ፣ ልዩ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን መለየትና አቅጣጫ ማስቀመጥ
  • የአፍ መፍቻ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማትን በአህዝቦት ስራ ማጀብ
 5. የአፍ መፍቻና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማት ማስተግበሪያ ሰነዶችና የህትመት ውጤቶች
  • ከ1ኛ- 4ኛ ክፍል የተሻሻለው የአማርኛ እንደ አፍ መፍቻ ቋንቋ ማንበብና መፃፍ ስርዓተ ትምህርት የአሰልጣኞች ስልጠና ማንዋል፤
  • ከ1ኛ- 8ኛ ክፍል በሰባቱ  ቋንቋዎች በተሻሻለው አፍ መፍቻ ቋንቋ ስርዓተ ትምህርት   ማሰልጠኛ  ማንዋል ፤
  • በሰባቱ  አፍ መፍቻ ቋንቋዎች የመምህራን ማማከሪያ ፍሬም ወርክ፤
  • ከ1ኛ -8ኛ ክፍል በሰባቱ  አፍመፍቻ ቋንቋዎች የመምህራን ማማከሪያ ማንዋል፤
  • Framework for implementing English language teacher improvement program (eltip)
  • School Based English Mentoring(SBEM)
  • Refresh your  English Teaching, Learning and Language (TKT)
  • Refresh your  English Listening and Speaking
  • Refresh your  English Reading
  • Refresh your  English Writing
  • Trainers Manual

Address Address

ተራ ቁ. የኃላፊ/የባለሙያ ስም የሥራ ኃላፊነት ስልክ ኢሜል
1 አቶ ታያቸው አያሌው ዳይሬክተር 0111565600 Mteldddirectorate@gmail.com
2 አቶ አበራ ላቀው የእንግሊዝኛ ትምህርት ማሻሻያ ኬዝ ቲም አስተባባሪ 0111565600  
3 አቶ ሲሳይ በዛብህ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ት/ት ባለሙያ 0111565600  
4 አቶ ሰለሞን ወርቁ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ት/ት ባለሙያ 0111565600  
5 አቶ ብርቃየሁ ደመቀ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ት/ት ባለሙያ ረዳት ፀሀፊ 0111565600  
6 አቶ ሙስጠፋ አየለ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ት/ት ባለሙያ 0111565600  
7 ወ/ሮ እመቤት አበራ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርት ማሻሻያ ኬዝ ቲም አስተባባሪ 0111565600  
8 ወ/ሮ የወይንሀረግ ሽታ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ት/ት ባለሙያ 0111565600  
9 ወ/ሮ ሙላቷ አዘነ ፀሀፊ 0111565600  
10 ወ/ት ራሔል አለምሰገድ የመልዕክት ሰራተኛ 0111565600  

Directorates and Departments Directorates and Departments