የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት

 

ዳራ

በሀገራችን በተቀረፀው የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ በየደረጃው የትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትሀዊነት፣ አግባብነትና ጥራትን ለማረጋገጥ ፖሊሲውን መሰረት ያደረጉ የትምህርት ዘርፍ ልማት ፕሮግራሞች እና የማስተግበሪያ መርሀ ግብሮች ተቀርፀው አበረታች ውጤት የተመዘገበ ቢሆንም ፤ የትምህርት ጥራትን ከማረጋገጥ አንፃር የተጀመሩ ጥረቶችን በማጠናከር  ተጨማሪ ስራዎች መሰራት ይኖርባቸዋል፡፡

 

ትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራትን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጅ በ1999 ዓ.ም. በመቅረፅ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡በመሆኑም በሀገራችን የሚገኙ የመጀመሪያ፣ሁለተኛ እና መሰናዶ ት/ቤቶች ፓኬጁን ከመፈፀም አኳያ ከግብዐት፣ ትና ውጤት ያሉበትን ደረጃ በመለየትና ያለባቸውን  ክፍተት በመሙላት የተማሪዎችን ውጤትና ባህርይ ለማሻሻል የሚደረገውን ጥረት አጠናክሮ ለመቀጠል የኢንስፔክሸን ስርአት በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ተግባራዊ ለማድረግ በ2004 ዓ.ም. የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ተቋቁሞ እየሰራ ይገኛል፡፡

 

ዳይሬክቶሬቱ የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅ ረገድ ኃላፊነትና የስራ ድርሻ ከተሰጣቸው የስራ ክፍሎች ውስጥ አንዱ ሲሆን የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ማስፈጸሚያ ሰነዶችን /መመሪያ፣ ማዕቀፍና የት/ቤቶች ደረጃ ምደባ/በማዘጋጀትና በየደረጃው ላሉ የትምህርት ኢንስፔክሽን ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠትክልሎች እገዛ እያደረገ ነው፡፡

 

መርሆዎች

የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን መርሆዎች

 • ነጻ ወይም የት/ቤቱ አካል ባልሆኑ የትምህርት ኢንስፔክተሮች ይካሄዳል፣
 • የአንድን ትምህርት ቤት አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ለመገምገም ተጨባጭ፣     ወጥነትና ቀጣይነት ባላቸው መረጃዎች ላይ ተመስርቶ ይካሄዳል፣
 • ግምገማው ሁሉንም ት/ቤቶች ባካተተ መልኩ በተቀመጡት ግልጽ ስታንዳርዶችና  መስፈርቶች መሠረት የሚካሄድ እንጂ  የኢንስፔክተሮች ግላዊ አመለካከት ፈጽሞ አይንጸባረቅበትም ፣
 • ገንቢ እና ለጉዳዮች ትኩረት የሚሰጥ ፤  የተከናወኑ መልካም ተግባራትን የሚያበረታታና እጥረቶችን ለይቶ በማውጣት የማሻሻያ ሃሳብ የሚሰጥበት ተግባር ነው፡፡
 • የትምህርት ቤቱን ማህበረሰብ ስብእና በማክበር ይከናወናል፣
 • የግምገማ ተግባራት ት/ቤቶች እንደ ተቋም ባስመዘገቡት ውጤት ላይ ያተኮረ እንጂ  በግለሰቦች የሥራ አፈጻጻም ላይ መሆን አይገባውም፣

አጠቃላይ ዓላማ

 • የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ዋና ዓላማ የትምህርት ጥራትንና  ውጤታማነትን በማረጋገጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተማሪዎችን ውጤትና ሥነ-ምግባር ማሻሻል ነው፡፡

ዝርዝር ዓላማዎች

 • ትምህርት ቤቶች የሚጠበቅባቸውን ተፈላጊ (Minimum)የአፈጻጸም ደረጃ ማሟላታቸውን ማረጋገጥ፣
 • ት/ቤቶችን በደረጃ በመመደብና ሞዴል ት/ቤቶችን በመለየት የጉድኝት ማዕከላት  ሆነው ሌሎችን እንዲያበቁ ማስቻል፣
 • የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ ግብር በተለይም  የትምህርት ቤት መሻሻል መርሀ ግብር አተገባበርና ውጤታማነትን በመፈተሽ ለፖሊሲ አውጭዎችና ለትምህርት ባለሙያዎች መረጃ ለመስጠት፣
 • በትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ስራ ወላጆች፣ መምህራንና  ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ትምህርት ቤታቸው ስላለበት ደረጃ መረጃ ለመስጠትና መሻሻል በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ተሳትፏቸውን ለማጎልበት፣
 • ትምህርት ቤቶች ሶስቱን የልማት ሰራዊት አቅሞች/ የድርጅት፣ የመንግስትና የህዝብ ክንፎች/ በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ ተጣምረው በትምህርት ተደራሽነት፣  ፍትሃዊነት፣ ብቃት፣ አግባብነትና ጥራት ላይ መረጃ   በመስጠት ተሳትፏቸውን በማጎልበት የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር እንዲያሻሽሉ ለማድረግ፣
 • የትምህርት ቤቶች መሻሻልና አፈጻጸምን አስመልክቶ  በየደረጃው የተጠያቂነት ስርአት ለማስፈን ነው፡፡

አደረጃጀት

የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለትምህርት ሚኒስቴር አጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሲሆን በአንድ ዳይሬክተር  ይመራል ዳይሬክቶሬቱ  በሶስት ንዑሳን ቡድኖች ማለትም በኢንስፔከሽን ክትትልና ግምገማ፣ በኢንስፔክሽን ልማት እና በመረጃ አሰባሰብና ማጠናቀር የተዋቀረ ነው፡፡ ዳይሬክቶሬቱክልል የትምህርት ቢሮ  ኢንስፔክሽን ዘርፍየዞን/ የክፍለ ከተማ ትምህርት መምሪያ ኢንስፔክሽን  ዘርፍየወረዳ ትምህርት /ቤት ኢንስፔክሽን ዘርፍ ጋር በቅርበት ይሰራል፡፡ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በአፋርና በጋምቤላ ክልሎችና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን መዋቅር በየደረጃው ዘርግተውና ባለሙያ መድበው ወደ ስራ ገብተዋል። የሐረሪ፣ የትግራይ፣ የቤኒሻንጉልና የኢትዮጰያ ሶማሌ ክልሎችና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር መዋቅሩን አስጠንተው በክልሉ ሲቪል ሰርቪስ እስኪፀድቅ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።

 

የአፈፃፀም ወሰን

የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ የአጠቃላይ ትምህርት ተቋማት ማለትም በቅድመ መደበኛ ፣ በመጀመሪያ ደረጃ፣ በአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃና በመሰናዶ  የመንግስት ፣ የህዝብ ፣ የግልና የሌሎች ትምህርት ተቋማት እንዲሁም በአማራጭ መሰረታዊ የትምህርት ማዕከላት ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ የተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት መስጫ ጣቢያዎችና የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች ወደፊት ስታንዳርድና መመሪያ ተዘጋጅቶ የሚታቀፉ ይሆናል፡፡

 

ስርዐት ዝርጋታ

የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ስርዐትን በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ማዕቀፍ ፣ መመሪያ እና ትምህርት ቤቶች የራሳቸውን ግለ ግምገማ የሚያደርጉበት  የትምህርት ቤት ደረጃ ምደባ ማዕቀፍ  እንዲሁም የመረጃ መሰባሰቢያ  መሳሪያዎች  /Checklist/ ለመጀመሪያ እና ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተዘጋጅቷል፡፡

 

የኢንስፔክሽን ባለሙያዎች አቅም ግንባታ ስልጠና በተመለከተ

በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ የአጠቃላይ ትምህርት የኢንስፔክሽን  ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ሲሆን ለታዳጊ ክልሎች የወረዳ ኢንስፔክሽን ባለሙያዎች በአይነቱ በርከት ያለ ስልጠናዎችን ሰጥቷል።  በየሩብ ዓመቱም በሁሉም ክልሎች የክተትልና ግምገማ ስራዎችን የሚሰራ ሲሆን  በተመረጡ ዞኖች፣ ወረዳዎች፣ የከተማና የገጠር  የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የናሙና ኢንስፔክሽን ስራ  ያከናውናል።

 

ጊዜ

ስልጠናው የተሰጣቸው

ይዘት

ፆታ

ወንድ

ሴት

ድምር

2005

ሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደር

ኢንፔክሽን ማስተግበሪያ ሰነዶች

52

6

58

2005

4 ታዳጊ ክልሎች

ኢንፔክሽን ማስተግበሪያ ሰነዶች

56

4

60

2006

ክልሎችና ከተማ አስተዳደር

ኢንፔክሽን ማስተግበሪያ ሰነዶችና አለምዓቀፍ ልምዶች

36

6

42

2006

4 ታዳጊ ክልሎች

ኢንፔክሽን ማስተግበሪያ ሰነዶች

75

12

84

2007

4 ታዳጊ ክልሎች

ኢንፔክሽን ማስተግበሪያ ሰነዶች

83

13

96

2007

4 ታዳጊ ክልሎች

ቅድመ መደበኛና አማራጭ መሰረታዊ ትምህርት ኢንፔክሽን ሰነዶች

47

2

49

2007

ለሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደር

ቅድመ መደበኛና አማራጭ መሰረታዊ ትምህርት ኢንፔክሽን ሰነዶች

17

4

21

 

 

ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚደረግ ግንኙነት

ዳይሬክቶሬቱ ከተለዩት የህዝብ ክንፍና የክልል ኢንስፔክሽን ስራ ሂደት ጋር በመሆን በየሩብ ዓመቱ የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ያደርጋል። በአፈፃፀማቸው መሰረትም ለክልሎች የማወዳደሪያ መስፈርት በማዘጋጀት ለክልሎች ደረጃ የማውጣት ስራና የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ኢንስፔክሽን ቼክሊስት በማዘጋጀትና ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ድጋፍና ክትትል የማድረግ ስራዎች ይከናወናሉ።

 

የትምህርት ቤቶች ግለ-ግምገማና ደረጃ ምደባ

የትምህርት ቤቶች ደረጃ ምደባና ግለ-ግምገማ በየዓመቱ መጨረሻ ትምህርት ቤቶች እንዲያከናውኑና ጠንካራና ደካማ ጎናቸውን በመለየት በገመገሟቸውና መሻሻል ባለባቸው ጉዳዮችን የቀጣይ ዓመት ዕቅድ ይዘው ለለውጥ እንዲሰሩ የሚያስችላቸው መሆኑን የትምህርት ቤቶች ደረጃ ምደባና  ማዕቀፍ ይጠቁማል።

 

የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን አተገባበር

የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ማስተግበሪያ መመሪያ ሰነድ ከ2006ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የኢንስፔክሽን ስራው እንደሚጀመርና በ2006ዓ.ም  20% ፣ በ2007 ዓ.ም 40% እና በ2008ዓ.ም 40% በድምሩ በሶስቱ ዓመት ጊዜ ውስጥ 100% እንደሚሰራ ያስቀምጣል። በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች   በ2006 ዓ.ም 20% ታቅዶ 27% ታይተዋል። በ2007 ዓ.ም 40% የኢንስፔክሽን ስራው በዕቅዱ መሰረት እየተከናወነ ሲሆን በቅርቡ መረጃው ከክለሎችና ከተማ አስተዳደሮች ተሰብስቦ ይፋ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ይገኛል።

 

በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ስር የሚገኙ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግለ ግምገማ ውጤት  ከታች ባለው ሰንጠረዥ የቀረበ ሱሆን  የአፈጻጸም ደረጃ መግለጫ እንደሚከተለው ይሆናል።

 

ደረጃውን ያላሟላ

ደረጃ 1

 

 

ደረጃውን በማሻሻል ላይ ያለ-       

ደረጃ 2  

 

 

ደረጃውን ያሟላ -             

ደረጃ 3      

 

 

ደረጃውን በከፍተኛ ደረጃ ያሟላ    

ደረጃ 4

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Address Address

የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት

ኢ ሜይል— inspectiondirectorate@yohoo.com

ስልክ—0111-11-05-34  /0111-11-05-67

Directorates and Departments Directorates and Departments