የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዳይሬክቶሬት

ዳራ

አዲሱ የትምህርት ስልጠና ፖሊሲ ተግባራዊ ከሆነ 1986 . ወዲህ በሀገራችን የትምህርት ሽፋን ተገቢነትና ፍትሐዊነት ከጊዜ ወዲ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱ ግልጽ ነው፡፡ የትምህርት ተገቢነትንም በተመለከተ የት/ አሰጣጡ ችግር ፈቺ እንዲሆን ያስችላል ተብሎ  በታሰበ ስልት የተቃኘ ስለሆነ ሀገሪቱ የሰለጠነ የሰው ሀይል ከማፍራትና የምእት ዓመቱን ግቦች ከማሳካት አንፃር ቁጥራቸው የማይናቅ የተለያዩ ባለሙያዎች በዘርፉ ለማሰልጠን ተችሏል፡፡

በሁሉም የትምህርት ደረጃዎች የሴቶች ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተ እድገት እያሳየ መምጣቱ በአርብቶ አደሩና በታዳጊ ክልሎች የትምህርት ሽፋን ቀላል የማይባል የመሻሻል ለውጥ ማሳየቱ ፍትሀዊነቱ ምን ያህል በትክክለኛው መሥመር እየተጓዘ እንዳለ የሚያሳይ ነው፡፡ እነዚህ ስኬቶች የሚያበረታቱና ተስፋ ሰጪ ቢሆኑም በትምህር ዘርፍ አሁንም ያልተሻገርነውና ትልቅ ጥረት የሚጠይቅ የትምህርት ጥራት ችግር ቅድሚያ ትኩረት የሚሻና መሻሻል የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡ መንግስትም ይህንኑ እውን ለማድረግ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፖኬጅ ነድፎ የተጠናከረ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ነው፡፡

ለዚህም ለትምህርት ጥራት ታሳቢ የሚደረጉ ግብዓቶች ብዙ ቢሆኑም የመምህራንና የት/ አመራር ብቃት ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡ በመሆኑም የመምህራንና የትምህርት አመራሮች አሰለጣጠን ከማሻሻልና ክህሎታቸውን ከማሳደግ ባሻገር ወደ ሥራው ሲሰማሩም ሆነ በስራው በሚቆዩበት ጊዜ ደረጃውን በጠበቀ የምዘናና  ግምገማ ሥርዓት እየፈተሹ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ እንዲኖራቸው ማድረግና በየወቅቱ ውጤትን መሠረት ባደረገ መልኩ የሚታደስበትን ሥርዓት በመዘርጋት ለትምህርት ጥራት መሻሻል አስፈላጊውን አስተዋጽኦ የሚያደርግ ራሱን የቻለ አካል በማስፈለጉ የመምህራንና የት/ አመራር የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዳይሬክቶሬት በሚል ስያሜ 2003 . በትምህርት ሚኒስቴር እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡

የሙያ ፈቃድ  ምንነት

የመምህራንና የትምህርት አመራር ሙያ ፈቃድ  (Licensure) በመምህራንና አመራር ልማት መርሀ-ግብር ስር የሚገኝ ሲሆን፤ ዋና ትኩረቱም መምህራንና ርዕሳነ መምህራን ያሉበትን የብቃት ደረጃ በጽሁፍና በፖርትፎሊዮ ምዘና እየፈተሸ ጠንካራና ደካማ ጎናቸውን በመለየት ብቃታቸውን ላረጋገጡት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሲሰጥ ክፍተት ያለባቸውን ደግሞ የተለየውን ክፍተት ለሚመለከታቸው ክፍሎች ግብረ-መልስ በመስጠት ድጋፍ ተደርጎላቸው ክፍተቶቻቸው እንዲሞሉ የሚያደርግ ሲሆን በአጠቃላይ በትምህርት ዘርፉ ያሉትን የትምህርት ተቋማት ጥራት ያለው ትምህርት ከመስጠት አንፃር ለመገምገም ያስችላል ተብሎ በተዘጋጀ የእውቅና መስጫ ስታንዳርድ መሠረት እውቅና የሚሰጥ አካል ሲሆን የሙያ ፈቃድ መርሀ ግብር የትምህርት ጥራቱ በመምህራን የማስተማር አተገባበር በትምህርት አመራሩም የአመራር ውጤታማነት ብቃት የተማሪዎችን ውጤታማነት በማሳደግ ላይ ትኩረት ያደረገ ጽንሰ ሀሳብ ነው፡፡

ዋና ግብ

በዕውቀት፤በክህሎትና በአመለካከት የተሻለ አቅም ያላቸውንና በሥነ ምግባር  የታነፁ ባለሙያዎችን ወደ ማስተማር ሙያ በመሳብ ሙያቸውን የበለጠ እያሳደጉና ተወዳዳሪ እየሆኑ በሄዱ ቁጥር በሚያስመዘግቡት መልካም ውጤት እና በሂደቱም  ጥራቱ የተጠበቀ ትምህርት በሀገሪቱ እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡

አበይት ርዕሰ ጉዳዮች

 • የመምህራንና የ ትምህርት ቤት አመራሮችን ብቃት ማረጋገጥ
 • የመምህራንና የትምህርት አመራሮችን ትምህርት ተቋማት ብቃት ማረጋገጥ ናቸው
 • የመምህራንና የትምህርት አመራሮች የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዳይሬክቶሬት ፈጻሚ አካላት ደረጃጀት

የመምህራንና የትምህርት አመራሮች የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት  ፈፃሚ አካላት አደረጃጀቶች መጠነ ሰፊ የሆነውን የሙያ ፈቃድና ዕድሳት ተግባራት ለመምራት የሚያስችል ተቋማዊ ብቃት እንዲኖረው ለማድረግ ታስቦ በፌደራል ደረጃ በሚዋቀር ኤጀንሲ የሚመራና  ለጊዜው በዳይሬክቶሬት ደረጃ በማደራጀት ተግባራትን ለመምራትና ለማከናወን የሚያስችል ቁመና እንዲይዝ ተደርጓል፡፡

አደረጃጀት፡ በፌደራል ደረጃ በአንድ ዳይሬክቶሬት የሚመራ ተጠሪነቱ ለት/ ሚኒስቴር የሆነ ዳይሬክቶሬት ሲሆን በስሩ ሶስት ቡድኖች አሉት እነሱም የስታንዳርድ ዝግጅት፤ የምዘናና ግምገማ ሠርተፊኬሽንና ስታስቲክስ ቡድኖች ሲሆኑ  በእያንዳንዱ ቡድንም ሁለት ሁለት ኬዝ ቲሞች የተዋቀረ ነው፡፡ ይኸውም

በስታንዳርድ ዝግጅት ቡድን ሥር

 • የመምህራን የሙያ ብቃት ስታንዳርድ ዝግጅት ኬዝ ቲምና
 • የርዕሳነ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የሙያ ብቃት ስታንዳርድ ዝግጅት ኬዝ ቲም ናቸው

በምዘና ግምገማና ሰርተፊኬሽን ቡድን ሥር

 • የቅድመ መደበኛ፣ የአንደኛ ደረጃ፣የሁለተኛ ደረጃ፣የመሰናዶና የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ መምህራን የሙያ ፈቃድና እድሳት ማረጋገጫ ምዘና፣ ግምገማና ሠርተፊኬሽን ኬዝ ቲም
 • የቅድመ መደበኛ የአንደኛ፤የሁለተኛ ደረጃ የመሰናዶ ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ሙያ ፈቃድና እድሳት ብቃት ማረጋገጫ ምዘና፣ግምገማና ሠርተፊኬሽን ኬዝ ቲም ናቸው

በስታስቲክስ ቡድን  ሥር

 • ስታስቲክስ  ኬዝ ቲም ነው፡፡

የመምህራንና የት/ አመራሮች ሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዳይሬክቶሬት ዋና ዋና ተግባራት

 • መመሪያዎችንና ደንቦችን ያወጣል ለባለድርሻ አካላት ያሳውቃል
 • ሙያዊ ብቃትን፣የይዘትና የማስተማር ስልቶችን የተመለከቱ ስታንዳርዶችን ያዘጋጃል በነሱም ላይ የግንዛቤ መፍጠሪያ ስልጠና ይሰጣል፡፡
 • በተዘጋጁት ስታንዳርዶች መሠረት የጽሁፍ ምዘናዎች ይዘጋጃሉ ለተመዛኞችም ይሰጣሉ፡፡
 • የምዘና ውጤቶችን በመተንተን ክፍተቶችን ይለያል ድጋፍ ለሚያደርጉ ዳይሬክቶሬቶችም ክፍተቱን ያሳውቃል
 • ስለ ሙያ ፈቃድ መድረኮችን ማመቻቸትና የግንዛቤ መፍጠር ሥራ ማከናወን
 • በክልሎችና በከተማ አስተዳደር የድጋፍና ክትትል ሥራ መሥራት
 • ከውጭና ከሀገር ውስጥ ተሞክሮዎች ቀምሮ ማስፋት
 • በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች ጥናቶችን ለማካሄድ መረጃዎችን ያሰባስባል በመረጃዎቹ ላይ ተመሥርቶም ጥናቶችን ያካሂዳል የጥናቱን ውጤትም ለሚመለከታቸው ያሳውቃል፡፡
 • ልዩ ፍላጎት ላላቸው መምህራንና የት/ ተቋማት አመራሮች እና ለሴቶች በሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ላይ ምቹ ሁኔታዎች  እንዲኖሩ ለክልሎችና ለከተማ አስተዳደር የሙያ ፈቃድ /ቤቶች ሙያዊና ቴክኒካዊ ድጋፍ ያደርጋል አፈፃፀምንም ይከታተላል ያረጋግጣል፡፡
 • የሙያዊ ፈቃድን በተመለከተ ዘመናዊ የመረጃ ሥርዓቶችን በመዘርጋትና በመጠቀም ሰነዶችን ያደራጃል መዝግቦ ይይዛል
 • የሙያ ብቃት ስታንዳርዶችን ከወቅቱ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር እያገናዘበ አሻሽሎ ያወጣል ያሰራጫል
 • ለሁሉም ደረጃዎች የሚያገለግሉ ሠርተፊኬሽን አዘጋጅቶ ያሰራጫል የብቃት ምዘናውን ላለፉ የሙያ ፈቃድ
 • እንዲያገኙ ያደርጋል ለሚታደስላቸውም የእድሳት አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡
 • ደረጃውን ጠብቀው የሚቀርቡ ቅሬታዎችንም ይቀበላል ይመረምራል ውሳኔም ይሰጣል፡፡
 • የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳትን አስመልክቶ መረጃ ያጠናቅራል ለሚመለከታቸው ክፍሎችም በዓመቱ መጨረሻ
 • የትግበራ ሪፖርት ለሚመለከታቸው ያቀርባል፡፡

ዋና ዋና ስኬቶች

 • የሙያ ፈቃድ መመሪያዎች፣ደንቦችና ተያያዥነት ያላቸው ሰነዶች ተዘጋጅተው ተሰራጭተዋል በአሁኑ ጊዜም
 • ወቅታዊ ለማድረግ ማሻሻያ እየተደረገላቸው ይገኛል
 • ለጽሁፍ ምዘና የሚያገለግሉ ሙያዊ ስታንዳርድ የይዘትና የማስተማር ሥልት ስታንዳርዶች ተዘጋጅተው የግንዛቤ
 • መፍጠሪያ ስልጠና ተሰጥቷባቸዋል በከፊል የተሰራጩ ሲሆን በከፊልም በድረ-ገጽ እንዲጫኑ ተደርጓል፡፡
 • 170 ሺህ ለሚሆኑ መምህራንና የት/ቤት አመራሮች የብቃት ምዘና ተሰጥቶ ውጤታቸው ተተንትኖ የተቀመጠ ሲሆን የፖርትፎሊዮ ምዘናውን ወስደው መስፈርቱን ለሚያሟሉ የሙያ ፈቃድ ለመስጠት ዝግጅቱ ተጠናቅቋል
 • ባለድርሻ አካላትን መድረኮችን እየፈጠሩ በማሰባሰብ ሙያ ፈቃድን አስመልክቶ የግንዛቤ ማሳደጊያ ሥራ በማከናወን ወደ ተጠቃሚው ማድረስ ተችሏል፡፡
 • በሙያ ፈቃድ መርሐ-ግብሮች አተገባበር ላይ በታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በምክክር መድረኮች ችግሮችን መፍታትና ጠንካራ ጎኖች እንዲበረታቱ የተደረገበት ሁኔታ መኖሩ
 • ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የመዋቅር አደረጃጀቶቻቸውን ራሳቸውን አስችለው እንዲያዋቅሩ የተደረገው ጥረት 90% በላይ በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ መሆኑ፡፡
 • ሙያ ፈቃድን አስመልክቶ ከውጭም ሆነ በሀገር ውስጥ የልምድ ልውውጥ ተደርጎ ለዳይሬክቶሬቱ ሥራ ምቹ ሁኔታዎችን የሚፈጥሩ ተሞክሮዎችን መገኘታቸው የመሳሰሉት ከብዙ በጥቂቱ የተገኙ ውጤቶች ናቸው፡፡

በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ የተቀመጡ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች

 • የትምህርት ጥራት ማሻሻያውን ለማስጠበቅ የጥራት ማሻሻያ ፖኬጁን ሙሉ በሙሉ መተግበር
 • ለዚህ የሚረዱ ግብዓቶችን ማቅረብና ደረጃዎችን ማውጣትና መከታተል
 • የልዩ ፍላጎት ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች በት/ ሥርዓቱ ውስጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተቀመጠውን ስትራቴጂ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ
 • በትምህርት ዘርፉ ቀጣይነት ያለው ወቅታዊ ክትትልና ጥናት በማድረግ ውጤቱን የእንቅስቃሴ ግብዓት በማድረግ የት/ ጥራት የሚረጋገጥበት ሁኔታ መፍጠር

የሙያ ፈቃድ ማስተግበሪያ ሰነዶችና የህትመት ጤቶች

 • የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ሥርዓትን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመተግበር የሚያስችሉ መመሪያዎች፣
 • የፈፃሚ አካላት አደረጃጀትና ተግባራት ሰነድ
 • የመምህራን የሙያ ብቃት ስታንዳርድ
 • የርዕሰ መምህራን ሙያዊ ብቃት ስታንዳርድ
 • የሱፐርቫይዘሮች ሙያዊ ብቃት ስታንዳርድ
 • የመመሪያዎች ማስተግበሪያ ማንዋሎች የየት/ ዓይነቱ / ከቴክኒካል ድሮዊንግ በቀርየኮንቴንትና የማስተማር ሥነ ዘዴ ስታንዳርዶች ተዘጋጅተው በትግበራ ላይ የዋሉ ሲሆኑ የሙያዊ ብቃት ስታንዳርዶቹ ታትመው ለክልሎችና ለከተማ መስተዳድሮች እንዲሰራጩ ተደርገዋል፡፡ የተቀሩት ግን በሚኒስትር /ቤቱ ድረ-ገጽ ላይ በመጫን ለተጠቃሚው ተደራሽ እንዲሆኑ እየተደረገ ይገኛል፡፡

Directorates and Departments Directorates and Departments