የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት

መግቢያ

በትምህርት ዘርፍ በሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ እና በአምስተኛው የትምህርት ዘርፍ ልማት መርሃ ግብር  በተጣለው ግብ መሰረት የመምህርነትን ሙያ  ሳቢ፣ ተመራጭ እና  በፍላጎት የሚገባበት በማድረግ ሙያዊ ብቃት ያላቸው፣  ስነምግባሩንም የተላበሡ እና ብቁ ዜጋ የሚያፈሩ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ለማፍራት በየደረጃው የሚሰጠውን ስልጠና ጥራቱን ለማስጠበቅ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡

ዓላማ

የመምህራንን፣ ርዕሳነ መምህራንንና ሱፐርቫይዘሮችን በረዥምና አጫጭር ስልጠናዎች በማብቃት በመማር ማስተማር ስራው ላይ አወንታዊ ለውጥ እንዲያመጡ ማስቻል ነው፡፡

አደረጃጀት

የተጀመረውን  የትምህርት ልማት ሰራዊት ግንባታ እውን ለማድረግ ዳይሬክቶሬቱ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ሲሆን፣ በዳይሬክቶሬቱ  የሚመራ አንድ የልማት  ቡድን እና ሶስት የ1 ለ 5 አደረጃጀቶች ማለትም የቅድመ ስራ ስልጠና ኬዝ ቲም (8 ባለሙያዎች የያዘ)፣የስራ ላይ ስልጠና ኬዝ ቲም (6 ባለሙያዎችን የያዘ) እና የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች (4  ሰራተኞችን የያዘ) በጠቅላላው 19 የሰው ሃይል ይዞ ግቡን ለማሳክት እየሰራ ያለ ነው፡፡

መርሃ ግብሮች

ከአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ  ፓኬጅ ውስጥ በሁለቱ መርሃ ግብሮች ላይ እየሰራ ያለ ነው፡፡

እነሱም፡ የትምህርት ቤት አመራር፣ አሰራርና አደረጃጀት እና የመምህራን ልማት መርሃ ግብር  ናቸው፡፡

ዳይሬክቶሬቱ በቅድመ ስራ ስልጠና እና በስራ ላይ ስልጠና ኬዝ ቲሞች የተከፈለ  ሆኖ በርካታ ተግባራትን ያከናውናል፡፡

 1. የቅድመ ስራ  ስልጠና ዋና ዋና ተግባራት
 • ለቅድመ መደበኛ  ት/ቤት፣ ለመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት እና ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን ትምህርትና ስልጠና ማእቀፍ፣ ስርዓተ ትምህርት( Curriculum)፣ መርሃ ትምህርት (Syllabus)፣ ሞጁሎች፣ መመሪያዎች ወዘተ ማዘጋጀት፣
 • የሁለተኛ  ደረጃ ት/ቤትመምህራን የመግቢያ ፈተና ማዘጋጀት፣
 • ለቅድመ ስራ ስልጠና የክልሎችን  የስልጠናፍላጎትና የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ  አቅምመረጃ ማሰባሰብ፣
 • የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እጩ መምህራን ለአሰልጣኝ ዩኒቨርሲቲዎች መመደብ፡፡
 1. የስራ  ላይ ስልጠና ዋና ዋና ተግባራት

2.1  የደረጃ ማሻሻያ

 • የመምህራንና የትምህርት ቤት የስራ ላይ ስልጠና  ስርዓተ ትምህርት፣ መርሃ ትምህርት እና ሞጁሎች ማዘጋጀት፣
 • የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅምና የክልሎችን የስልጠና ፍላጎት መረጃ ማሰባሰብ፣ ኮታ መደልደልና መመደብ፣
 • መምህራን፣ ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች (ከሰርተፍኬት ወደ ድፕሎማ፣ ከድፕሎማ ወደ መጀመሪያ ድግሪ፤ ከመጀመሪያ ድግሪ ወደ ሁለተኛ ድግሪ) የትምህርት ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ ማድረግ፣
 • የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና መርሃ ግብሮች ማዘጋጀት፡- በአሁኑ ወቅት ያሉት፡-
 • የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ድህረ ምረቃ ድፕሎማ በትምህርት ቤት አመራር ስልጠና (Post Graduate Diploma in school leadership (PGDSL))፣
 • የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት  ሱፐርቫይዘርነት ስልጠና (Post Graduate Certificate in Primary School Supervision (PGCPSS))፣
 • የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት  የሁለተኛ ድግሪ የትምህርት ቤት አመራርነት ስልጠና (MA in School Leadership)፣
 • የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት  ሱፐርቫይዘርነት ስልጠና (Post Graduate Certificate in Secondary school Supervision (PGCSSS)) ናቸው፡፡
 • የመምህራንና የትምህርት አመራሮችን የውጤት ተኮር አፈጻጸም እና የደረጃ እድገት መመሪያ ማዘጋጀት፣

2.2  ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ መርሃ ግብር (CPD)

•  የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ( ተሙማ) መርሃ ግብር በመከታተል፣ በመገምገምና ግብረ መልስ በመስጠት ማጠናከር፣

•  የተሙማ አፈጻጸምን በመገምገም ማሻሻል፣

•  በተሙማ አፈጻጸም ላይ  ምርጥ ተሞክሮዎችን መቀመርና ማስፋት፣

•  ለመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች አጫጭር የአቅም ግንባታ ስልጠና  መስጠት፣

•  በመምህራን ትምህርት አሰልጣኝ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠውን የከፍተኛ ዲፕሎማ መርሃ ግብር (HDP) በመከታተል ማጠናከር፡፡

ዋና ዋና ስኬቶች

በሀገር አቀፍ ደረጃ በጠቅላላው 497,737(ወ 311,852፣ ሴ 185,885 ) ቅድመ መደበኛ ት/ቤት፣ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት እና  የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን አሉ፡፡ (ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ስታትሲቲክስ፣ 2007 ዓ.ም):: በአምስተኛው የትምህርት ዘርፍ ልማት መርሃ ግብር እቅድ አንዱ ትኩረት የተሰጠው  ጉዳይ የመምህርነትን ሙያ ተመራጭ ማድረግ ሲሆን፣ በ2008 ዓ.ም አፈጻጸም ሁለት ዋና ዋና ተጠቃሽ ስኬቶች ተገኝተዋል፡፡ እነሱም፡ የመምህራንንና የትምህርት ቤት አመራሮችን የደመወዝ ስኬል እንዲሻሻል እና የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል መመሪያ በማዘጋጀት ወደ ትግበራ እንዲገባ ማድረግ መቻሉ ናቸው፡፡

በተጨማሪም ለመምህራንና ለትምህርት ቤት አመራሮች በረዥም ጊዜ ስልጠና የእየተደረገ ያለውን የደረጃ እና የብቃት ማሻሻያ ስልጠና ውጤቶች ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ ማየት ይቻላል፡፡

በአምስተኛው የትምህርት ዘርፍ ልማት መርሃ ግብር እቅድ ዋና ዋና የትኩረት ጉዳዮች

አላማው በሁሉም የትምህርት ተቋማት ያለውን የመምህራንና የአመራር ሀይል የስራ ፍቅርና እርካታ እንዲሁም የሙያ ክህሎት ማሻሻል ሆኖ፡-

 • የመምህርነትን ሙያ ተመራጭ ማድረግ፣
 • የመምህራንን ሙያዊ ክህሎት ማሻሻል እና፣ 
 • የትምህርት ቤት አመራሮችን   የአመራር ክህሎት ማሻሻል ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ሲሆኑ  በእነዚህ አቅጣጫዎች ስር በርካታ ዋና ዋና ተግባራትን የያዙ ስምንት የማስፈሚያ  ስልቶች ተቀርጸው  ተግባራዊ እየተደረጉ ናቸው፡፡

Directorates and Departments Directorates and Departments