የትምህርት ዘርፍ ኤችአይቪ/ኤድስና ተዛማጅ በሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ማስተባበሪያ

መግቢያ

የትምህርት ዘርፍ ኤችአይቪ/ኤድስና ተዛማጅ በሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ማስተባበሪያ እስከ መጋቢት 2006 ዓ.ም ድረስ እንደ ሥራ ክፍል ከመቋቋሙ በፊት በ 1 ፎካል እና በ2 የኮንትራት ቅጥር ባለሙያዎች ይመራ ነበረ፡፡ አብዛኛው የሀገሪቱ ወጣቶች የሚገኙት በትምህርት ሴክተሩ በመሆኑና እነዚህ ወጣቶች በእድሜአቸው አፍላነት ምክንያት ለኤችአይቪ/ኤድስና ስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች የመጋለጥ እድላቸውን ከግምት በማስገባት፤ ጤናማ እና አምራች ዜጋ እንዲሆኑ ለማስቻል አዲስ መዋቅር በማዘጋጀት እና እንዲፀድቅ በማድረግ ከመጋቢት 2006 ዓ.ም ጀምሮ በሙሉ አቅም ወደ ሥራ ገብቷል፡፡ የቫይረሱን ስርጭት እና በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያግዙ የትምህርት ሴክተሩ፡-

 • የፖሊሲው ማስተግበሪያ ጋይድ ላይን፣
 • ኤችአይቪ/ኤድስ ፖሊሲና ስትራቴጂ፣
 • በሁሉም የትምህርት እርከኖች የሚተገበር ፓኬጅ፣
 • የሥራ ቦታ ፖሊሲና የኤድስ ፈንድ ማስተግበሪያ ማንዋል፣
 • የአቻ ለአቻ ትምህርት ማንዋል፣
 • በ2ኛ ደረጃ በ3 የትምህርት አይነቶች የማጣጣም (እንግሊዝኛ፣ ባዮሎጂ እና ሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር ትምህርቶች) የህይወት ክህሎት ማንዋሎች ተዘጋጅው ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡

የማስተባበሪያው ዋና ዋና ግቦች

 • በትምህርት ሰክተሩ ያሉትን ተማሪዎች፣ ሰልጣኞች፣ መምህራን፣ አመቻቾችና የትምህርት ማህበረሰቡ ከኤችአይቪ/ኤድስ  እና ሥነ-ተዋልዶ ጤና ችግሮች በመከላከል  አምራችና ጤናማ ዘጋ ማፍራት፣
 • ማግለልና አድልኦን በማስወገድ ምቹ የመማሪያና ማስተማሪያ አከባቢ እና የትምህርት ማኅበረሰብ በመፍጠር የኤችአይቪ/ኤድስን ተጽእኖ መግታት፤
 • በሁሉም የትምህርት ዘርፍ መዋቅሮች፣ ስትራቴጂክ ሰነዶች፣ ዕቅዶችና ፕሮገራሞች ውስጥ ኤችአይቪ/ኤድስን የመከላከል ዋና ዋና ተግባራት ተካተው (Mainstream) በሁሉም ኣካላት ተግባራዊ እንዲሆኑ ማድረግ፤
 • የኤች አይቪ/ኤድስ እና የሥነ-ታዋልዶ ጤና ጉዳዮች በከፍተኛ ትምህርት ተቋቋማት በሚከናወኑ የምርምር እና የማህበረሰብ ሥራዎች ውስጥ በማካተት የትኩረት መስክ እንዲሆኑ ማድረግ፡፡

ኤችአይቪ/ኤድስና የሥነ-ተዋልዶ ጤና ርዕሰ ጉዳዮች በትምህርት ሴክተሩ (Approaches)

 • የባህሪ ለውጥ አምጪ (Behavioural) ስራዎች
 • የህይወት ክህሎት ትምህርት (Life Skill Education) በሥርዓተ-ትምህርቱ ውስጥ በማካት
 • አቻ ለአቻ ትምህርት (Peer Education)
 • ይንሰተሪም (Mainstreaming)
 • በትምህርት ተቋማት ልዩ ልዩ ጉዳዮችን ማዘጋጀት (Events such as Red Card, Pijama, SISTA, Self Risk Assessments…)
 • መዋቅራዊ (Structural) ሥራዎች
 • የልዩ ልዩ ሰነዶች ዝግጅት
 • ትምህርት ሴክተሩ እስከታችኛው እርክን ድረስ መዋቅር መዘርጋት፤ ባለሙያ ንዲመደብ ማድረግ
 • ተጓዳኝ ትምህርት የሚተገበሩ ልዩ ልዩ መዋቅሮችን ማቋቋም ወይም ማጠናከር (የፀረ-ኤድስ ክበብ፣ የኤድስ ማዕከል)
 • የሥነ-ህይወታዊ ህክምና (Bio-medical) ሥራዎች ናቸው
 • የክሊኒክ ሥራዎች (Clinical works)
 • ከጤና ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠር መሥራት (Referal Linkages)
 • ኮንዶምን በሥራ ቦታና በከፍተኛ ጥምህር ተቋማት መስተዋወቅና ማሰራጨት (Condom Promotion & Distribution at the work Place and Higher Education Institutions)

የትምህርት ዘርፍ ኤ አይቪ/ኤድስና ተዛማጅ በሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ማስተባበሪያ አደረጃጀት

የሥራ ክፍሉ መጠሪያ፡- የትምህርት ዘርፍ ኤችአይቪ/ኤድስና ተዛማጅ በሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ማስተባበሪያ

 • ተጠሪነቱ ለሥራ አመራርና አስተዳደር ዘርፍ ሆኖ የሚከተሉት የሥራ መደቦችና ሠራተኞች ተመድበው በሥራ ላይ ይገኛሉ፡፡
 • የማስተባበሪያ ኃላፊ = 1
 • ባለሙያዎች = 7
 • ፀሀፊ = 1
 • መልዕክት ሠራተኛ = 1
 • በአጠቃላይ 10 ሰራተኞችን ይዞ የተሰጠውን ተልዕኮ በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡

የማስተባበሪያው ዋና ዋና ተግባራት

 • የትምህርት ዘርፍ ልማት ዕቅድ ግቦች መሳካት ወሳኝ የሆኑት መምህራን፣ ሠራተኞች፣ ሰልጣኞችና ተማሪዎች ከኤችአይቪ/ኤድስና ተዛማጅ በሽታዎች እንዲጠበቁ የፖሊሲ ጥናትና ትንተና በማድረግ ለከፍተኛ አመራሩ የውሳኔ ኃሳብ በማቅረብ ሲወሰን ስልት ነድፎ ሥራ ላይ ማዋል፣
 • መምህራን፣ ሠራተኞች፣ ሰልጣኞችና ተማሪዎች ከኤችአይቪ/ኤድስና ተዛማጅ በሽታዎች እንዲጠበቁ የአቻ ለአቻና የህይወት ክህሎት ትምህርቶች የስልጠና ማኑዋል  በማዘጋጅት ተከታታይ የሆነ የአሰልጣኞች ሥልጠና መስጠት፣
 • በትምህርት ሴክተሩ የኤችአይቪ/ኤድስን ስርጭት፣ ተፅዕኖ፣ እና እየተሰጡ ያሉ ምላሾችን ሊያሳዩ የሚችሉ ጠቋሚዎችን (Indicators) በትምህርት ሴክተሩ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ (EMIS) መረጃዎችን መሰብሰብ፣ መተንተን በዓመታዊ የትምህርት መፅሄት(Educational Abstract) እንዲወጣ ማድረግ፡፡
 • በፕላዝማ፣ በሬድዮና በበራሪ ወረቀቶች ሊሰራጩ የሚችሉ የባህሪ ለውጥ ተግባቦትና ኮሙኒኬሽን (IEC/BCC) ጹሁፎችን በማዘጋጀት ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ሠራተኞች፣ ለተጠሪ ተቋማት፣ ለመጀመሪያና ለ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ ለቴ/ሙ/ት/ሥ/ተቋማትና ለዩኒቨርሲቲዎች እንዲሰራጩ ማድረግ፣
 • ኤችአይቪ/ኤድስ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ የሚገኝባቸውን የመ/ቤቱ ሠራተኞችንም ሆነ ወላጆቻቸውን በኤድስ ምክንያት ያጡ ልጆችን በመ/ቤቱ የኤድስ ፈንድ እና ደጋፊዎችን በማፈላለግ የትምህርት፣ የቁሳቀቁስና የማህበራዊ ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ፤ ከምርመራ በፊትና ከምርመራ በኋላ የምክር አገልግሎት መስጠት፡፡
 • የኤችአይቪ/ኤድስንና ስነ-ተዋልዶ ጤና ጉዳዮችን ስትራተጂዎችና ፕሮግራሞችን ሜይንስትሪም ማድረግ፣ በካሪኩለም ማካተትና አውደ ጥናቶችን ማካሄድ፣
 • የትምህርት ዘርፉን የኤችአይቪ/ኤድስና ተዛማጅ በሽታዎች መረጃ የመሰብሰብ፣ የማጠናቀርና መተንተን ለፖሊሲ  አውጪዎችና ውሳኔ ሰጪዎች ማቅረብ። እንዲሁም ለአጭር፣ ለመካከለኛና ለረጅም ጊዜ እቅድ ዝግጅት በግብዓትነት መጠቀምና ለሌሎች ተጠቃሚዎች ተደራሽ ማድረግ፤
 • ኤችአይቪ/ኤድስንና ስነ-ተዋልዶ ጤና ጉዳዮችን ከመከላከል አንፃር በሴክተሩ የተሰሩ የምርምርና የማህበረሰብ ሥራዎችን ውጤታማነት መፈተሽ፣ በአዲስ እንዲሰሩ ድጋፍ ማድረግ፣ ምርጥ ተሞክሮችን በመቀመር ማስፋት፣
 • በትምህርት ሴክተሩ በልማት አጋሮች የሚከናወኑ የኤችአይቪ/ኤድስና ስነ-ተዋልዶ ጤና ጉዳዮችና ሥራዎችን መደገፍና መከታተል፡፡
 • የተጋላጭነት(Risk assessment)፣ የተፅዕኖ(Impact Assessment) እና የሴክተሩን ምላሽ (Intervention/Response Assessement) ዳሰሳ ጥናቶችን ማካሄድ፤
 • ተከታታይና ቋሚ የሆነ የጋራ የክትትልና ግምገማ ስርዓት በመዘርጋት እስከ ታችኛው የትምህርት ተቋም ድረስ ክትትልና ግምገማ ማድረግ፤ ግብረ-መልስ መስጠት የማስተባበሪያው ዓበይት ተግባራት ናቸው።

በአጠቃላይ ከማስተባበሪያው ምስረታ ጀምሮ እስከ 2008 ዓ.ም የተገኙ ዋና ዋና ውጤቶች

 • በሴክተሩ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያግዙ የትምህርት ዘርፍ ኤችአይቪ/ኤድስ እና ስነ-ተዋልዶ ጤና ፖሊሲና ስትራቴጂ እንዲሁም የፖሊሲው ማስተግበሪያ ጋይድላይን ተዘጋጅቶ ወደ ስራ ተገብቷል፤
 • በሁሉም የትምህርት እርከኖች የሚተገበሩ የመከላከልና የመቆጣጠር ዋና ዋና ስራዎችን የሚያመላክት ፓኬጅ (Minimum Intervention Package) ተዘጋጅቶ በትግበራ ላይ ይገኛል፤ 
 • የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዎችን ሜይንስትሪም ከማድረግ አንጻር በካሪኩለም ውስጥ የማካተትና በአተገባበሩ ላይም ስልጠና ተሰጥቶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፤
 • በትምህርት ሴክተሩ የኤችአይቪ/ኤድስን ስርጭት፣ ተፅዕኖ፣ እና እየተሰጡ ያሉ ምላሾችን ሊያሳዩ የሚችሉ ጠቋሚዎችን (Indicators) በትምህርት ሴክተሩ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያና ቋት (EMIS) ውስጥ እንዲካተት ተደርጓል፡፡ በየጊዜውም መረጃዎች እየተሰበሰቡ እና እየተተነተኑ ይገኛሉ፡፡
 • በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ በክልል ትምህርት ቢሮዎችና ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኤጀንሲዎች ውስጥ የኤች አይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ መዋቅሮች እንዲኖሩ የሚኒስቴር መሥራያ ቤቱን መወቅር በመስጠት ከየተቋማቱ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማጣጣም አፀድቀው ተግባራዊ እንዲያደርጉ እገዛ ተደርጓል፤
 • የኤችአይቪ/ኤድስና ሥነ-ተዋልዶ ሥራዎችን የመደገፍና የመከታተል ሥራ በአካል መልከታ፣ በድጋፋዊ ሱፐርቪዥን፣ በጋራ በማቀድና በመገምገም፣ በየሩብ ዓመቱ ሪፖርቱን የመጠመርና ለሚመለከታቸው አካላት የማቅረብ እና የታዩ ክፍተቶችም እንዲታረሙ በከፍተኛ አመራሩ አቅጣጫ እንዲሰጥባቸው የማድረግ ሥራ ተካሂዷል፡፡
 • የሚኒስቴር መ/ቤቱ የሥራ ቦታ የተጋላጭነት (Risk assessment) ጥናት 2 ጊዜ ተሠርቷል፡፡ ጥናቱን መሰረት በማድረግ ሰራተኛውን ከኤችአይቪ/ኤድስ ለመከላከል ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ተሰርቷል፤ በቀጣይነትም ዕየተሠራ ይገኛል፡፡
 • ከተለያዩ ተቋማት ምርጥ ተሞክሮዎችን በማምጣጥ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡
 • በሰራተኛው በጎ ፈቃድ ላይ በመመስረት የኤድስ ፈንድ ተቋቁሟል፤ በዚህም ወላጆቻቸውን ላጡ ወይም ድጋፍ ለሚሹ 5 ሕፃናት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡

የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያግዙ በትምህርት ሴክተሩ እና በአጋሮች የተዘጋጁ ሰነዶች፡-

 • የፖሊሲው ማስተግበሪያ ጋይድ ላይን፣
 • ኤችአይቪ/ኤድስ ፖሊሲና ስትራቴጂ፣
 • በሁሉም የትምህርት እርከኖች የሚተገበር ፓኬጅ፣
 • የሥራ ቦታ ፖሊሲና የኤድስ ፈንድ ማስተግበሪያ ማንዋል፣
 • የአቻ ለአቻ ትምህርት ማንዋል፣
 • በ2ኛ ደረጃ በ3 የትምህርት አይነቶች የማጣጣም (እንግሊዝኛ፣ ባዮሎጂ እና ሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር ትምህርቶች) የህይወት ክህሎት ማንዋሎች ተዘጋጅው ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡

በሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የተቀመጡ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች

 • በህይወት ክህሎትና በአቻ ለአቻ ትምህርቶች 12,000,000 የሚሆኑ ተማሪዎችን መድረስ፣
 • የኤችአይቪ/ኤድስና ስነ-ተዋልዶ ጤና ፕሮግራሞች ሜይንስትሪሜንግ፣ ዕቅድ፣ ክትትልና ግምገማ ላይ በሁሉም ደረጃ ለሚገኙ አስተባባሪዎች የአቅም ግንባታ ሥራ መሥራት ለተማሪዎች ተደራሽ ማድረግ፣
 • መልካም ተሞክሮዎችን ለማምጣትና ለማስፋት የልምድ ልውውጥ ማካሄድ፣
 • የሥራ ቦታ ኤችአይቪ/ኤድስና ስነ-ተዋልዶ ጤና ፕሮግራሞችን በተጠናከረ ሁኔታ መተግበር፣
 • የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን በተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫሎች፣ በዓለም ኤድስ ቀንና በአዲስ ተማሪዎች ቅበላ ወቅት መሥራት፣
 • ቀደም ብለው የተዘጋጁ የማስፈፀሚያ ማኑዋሎችን ከወቅቱ ጋር እንዲሄዱ አድርጎ ማሻሻልና ስራ ላይ ማዋል፣
 • የህይወት ክህሎት ትምህርት በሁለተኛ ደረጃ ስርዓተ-ትምህርት ውስጥ በ3 የትምህርት ዓይነቶች የተካተተውን ማስፋት፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥም ትግበራውን መከታተልና ድጋፍ ማድረግ፣
 • የህይወት ክሎቶችን በአንደኛ ደረጃ ትምህርት በሁለተኛ ሳይክል በ3 የትምህርት ዓይነቶች ውስጥ ማካተት እንዲቻል ጥናት ማድረግና በጥናቱ ውጤት መሠረት ስርዓተ-ትምህርት ውስጥ የማካተት ስራ መስራት
 • በሥራ ቦታና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኮንዶምን የማስተዋወቅና የማሰራጨት ስራ መስራትና መከታተል
 • የፀረ-ኤድስ እና ስነ-ተዋልዶ ጤና ክበባት በትምህርት እና ሥልጠና ተቋማት እንዲቋቋሙና ያሉትንም ማጠናከር፣
 • የፀረ-ኤድስና ስነ-ተዋልዶ ጤና ክበባት በሁሉም ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ማቋቋምና  ማጠናከር፣
 • በሁሉም የትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ሚኒ ሚዲያዎችን ማቋቋምና  ማጠናከር፣
 • የኤድስና ስነ-ተዋልዶ ጤና መረጃ ማዕከል በሁሉም ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ማቋቋም ወይም ማጠናከር፣
 • ለድሀና ተጋላጭ ለሆኑ ተማሪዎች ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣

ተግዳሮቶች ወይም በቀጣይ የከፍተኛ አመራሩን ድጋፍ የሚፈልጉ ጉዳዮች

 • የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሁሉም የሥራ ክፍሎች የዘርፈ-ብዙ ጉዳዮችን (የኤችአይቪ/ኤድስ እና ስነ-ተዋልዶ ጤና ጉዳዮችን ሜይንስትሪም) በዕቅዳቸው ውስጥ አካተው እንዲተገብሩ እና እንዲገመግሙ ማድረግ፤
 • ለሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሲዘጋጅ የሥራ ክፍሎች ሰልጣኞችን እንዲልኩ እና ስልጠናውን እንዲከታተሉ ማድረግ
 • አንዳንድ ዝግጅቶችና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች ሲዘጋጁ የሥራ ክፍል ላፊዎችና ሠራተኛው በመድረኮች ላይ እንዲገኝ አመረር መሥጠት ከፍተኛ አመራሩም እንዲገኝና በጥብቅ ዲሲፕሊን መምራት፡፡
 • የኤችአይቪ/ኤድስና ስነ-ተዋልዶ ጤና ፕሮግራሞችን በGEQIP II ወይም በ UNICEF ፋይናንስ ድጋፍ እንዲታቀፍ ማድረግ፡፡
 • በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኤድስ ፈንድ መዋጮ ላይ ሁሉም ሠራተኛ ድጋፍ እንዲያደርግ ማገዝ፤
 • የከፍተኛ ትምህርት ፀረ-ኤድስ ንዑስ ፎረም ከት/ሚ ጋር በጋራ ለመስራት ፈቃደኛ አለመሆን፤ (የሥራ ሪፖርት ለት/ሚ አለማቅረብ፣ ወቅታዊ የኦዲት ሪፖርት አለማቅረብ ግልፅ አሰራር አለመከተል፣ ዩኒቨርሲቲዎች ለት/ሚ ሪፖርት እዳያደርጉ ማከላከል፣ በት/ሚ የተዘጋጀ ሰነድ እያለ ድጋሚ ማዘጋጀት…) እንዲሁም ህግን መሠረት አድርጎ አለመሥራት
 • በአጠቃላይና በከፍተኛ ትምህርት ዘርፎች በሚደረጉ የሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማዎች የኤችአይቪ/ኤድስ ጉዳይ በአጀንዳ ተይዞ አለመገምገሙ፤ ማስተባበሪያውም በግምገማው ላይ ተገኝቶ ሪፖርት እንዲያቀርብ እድል አለማግኘቱ
 • ከአንዳንድ የክልል ትምህርት ቢሮዎች የሩብ ዓመት የሥራ ክንውን ሪፖርት አለማግኘት፣
 • በአብዛኛው የክልል ት/ቢሮዎችና በአንዳንድ ከፍተኛ ትምህርት ተማት ስትራክቸር/የሥራ ክፍል/ አለመኖር፤ ወይም በፎካል ፐርሰን ለማሰራት መሞከር፣
 • በአንዳንድ ከፍተኛ ትምህርት ተማት ስትራክቸር/የሥራ ክፍል/ የማጠፍ ችግር መታየቱ፣
 • በክልል ትምህርት ቢሮዎችና በከፍተኛ ትምህርት ተማት የተመደቡ የሰለጠኑ ባለሙያዎች ፍልሰት በየጊዜው ማጋጠሙ
 • በየደረጃው ያለው አመራርም ሆነ የትምህርት ማህበረሰብ ኤችአይቪ እንደጠፋ በመቁጠር በመከላከሉ ሥራ ላይ ከፍተኛ መዘናጋት መከሰቱ

አንድም ሰው በኤችአይቪ/ኤድስ እንዳይያዝ ሁላችንም ኃላፊነታችንን እንወጣ !!!

Directorates and Departments Directorates and Departments