Web Content Display Web Content Display

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት የአስተዳደር ጉዳዮች ጄኔራል ዳይሬከቶሬት

መግቢ

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በሀገራችን እየተስፋፋ የመጣውን የከፍተኛ ትምህርት ጥራት፣ ተደራሽነት፣ ፍትሀዊነትና አግባብነት የስራ እንቅስቃሴና ሌሎች ጉዳዮች በተገቢው ሁኔታ በሚደግፍና በሚመራ መልኩ እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡ ተቋሞቻችን መልካም አስተዳዳር የሰፈነባቸው፣ ሰላማዊ መማር ማስተማር የሚካሄድባቸው፣ ጥራቱን የጠበቀ የማህበረሰብ አገልግሎት  የሚሰጥባቸው፣ የዘርፉ ማስፋፊያና ተሳትፎ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እንዲፈፀም ለማድረግ፣ የከፍተኛ ትምህርት  ወጪ  ፍትሃዊና አዋጪ በሆነ ስልት እንዲሸፈን ለማስቻል አገራዊ ሥርዓት፣ የህግ ማዕቀፍ፣ ደንብና መመሪያ እንዲዘረጋ በዘርፉ የተዋቀረዉ የአስተዳደር ጉዳዮች ጀነራል ዳይሬክቶሬት ሃላፊነት ተጥሎበታል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት የአስተዳደር ጉዳዮች የጄኔራል ዳይሬክቶሬቱ ተልዕኮ

የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የዕቅድ ግቦች ይሳኩ ዘንድ በከፍተኛ ትምህርት ተቋሞቻችን አዳዲስ አሰራሮች ተጠንተው ስራ ላይ እንዲውሉ በማድረግ ብሎም የተጀመሩት የለውጥ ኘሮግራሞች ሙሉ በሙሉ ስራ ላይ መዋላቸውን በመከታተልና በመደገፍ መልካም አስተዳደር የሰፈነባቸው፤ ተጠያቂነትና ግልጽነት ያለበት የሀብት አጠቃቀምና አያያዝ ሥርዓት የሚከተሉና የላቀ የማህበረሰብ አገልግሎት የሚያበረክቱ ከፍተኛ ትምርት ተቋማት መፍጠር ነው፡፡

 ዋና ዋና ግቦች

 1. በከፍተኛ ትምህርት የአመራርና ፈጻሚዎች አቅምን መገንባት፤
 2. በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መልካም አስተዳደር ማስፈንና መስጠበቅ፤
 3. የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር መዋጋትና ልማታዊ አስተሳሰብ በሁሉም ዘንድ እንዲሰፍን ማድረግ፤
 4. በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህበረሰባዊ አገልግሎቶችን አሰጣጥ መደገፍና ማጠናከር፤
 5. መመሪያዎች ደንቦችና አዳዲስ አሰራሮች እንዲሰርፁ ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸው እንዲሻሻሉ ለተቋሞቻችን ድጋፍና ክትትል ማድረግ፤
 6. የሀብት አጠቃቀማችን እና የግዥ ስርዓታችን የመንግስትን መመሪያና ደንብ ተከትሎ እንዲፈፀም ትኩረት ሰጥቶ መስራት፤
 7. ጥራትና ወቅታዊ መረጃዎችን መቀመርና ለባለድርሻ አካላት ተደራሽ ማድረግ ናቸዉ፡፡

አደረጃጀት፡-

ዳይሬክቶሬቱ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ተደራጀ ሲሆን ፡- የከፍተኛ ትምህርት ምርምር ስርጸት እና ማህበረሰብ አገልግሎት ማጠናከሪያ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወጪ መጋራት፣ የእቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ እና የአስተዳደራዊ ጉዳዮች ክፍሎች አሉት፡፡ በዚህ መሠረት 1 ጄኔራል ዳይሬክተር፣ 8 ባለሙያዎች፤ 1 ሁኔታ አመቻች እና 1 የመልዕክት ሰራተኛ በመያዝ ተልዕኮን እየተወጣ ይገኛል፡፡

የተከናወኑ ተግባራት

 • የከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁ.650/2001 እና ከፍተኛ ትምህርት ወጪ መጋራት ደንብ ቁጥር 154/2000 ማሻሻል ስራ ማካሄድ፤
 • የከፍተኛ ትምህርት ማህበረሰብ አገልግሎት ተልዕኮ ማጠናከሪያ ማዕቀፍ መዘጋጀቱ፤
 • ልዩ ፍላጎት ያላቸዉ ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ጀምሮ ልዩ ድጋፍ ዕነዲያገኙ ማድረገ፤ 
 • ከተቋማት የዉጥ ጽ/ቤቶች ጋር በመሆን ለዉጥ ትግበራና የመልካም አስተዳደር ማስፈን ማጠናከር፤
 • የመምህራን እና የቴክኒክ ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች የደሞዝ ደረጃ ማሻሻያ እነዲደረግላቸዉ ከባለድርሻ አካላት ጋር መስራት፤
 • ከመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመረቁ የወጪ መጋራት እንዲፈጽሙ ማድረግ፤
 • የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራር ምልመላና ምደባ ማዕቀፍ ማዘጋጀት፤
 • በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሴቶችን ወደ አመራር የማምጣት ሥራ ማካሄድ፤
 • በየሩብ ዓመቱ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከተለያዩ አደረጃጀቶች ጋር የጋራ የውይይት መድረክ በመፍጠር ድጋፍ ማድረግና ልምዶችን እንዲለዋወጡ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፤
 • ዩኒቨርሲቲዎች የምርምርና የልህቀት ማዕከል ለማደራጀት የሚያደርጓቸዉን ተግባራት መደገፍ፤
 • የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተናጠል ከተለያዩ  ሀገራዊና  አለም አቀፋዊ ድርጅቶች ጋር በመስራት የገቢ አቅማቸውን ማሳደግ እንዲችሉ መደገፍ፤
 • በስራ ክፍሉ የኪራይ ሰብሳቢነት  ምንጮችን የመለየትና በየጊዜው በአደረጃጀት አማካኝነት ስራዎችን  እየገመገሙና  የመፍትሔ  አቅጣጫ  በማስቀመጥ መተግበር፤
 • የመልካም  አስተዳደር ፓኬጅ እቅድ ለዘርፉና ለዩኒቨርሲቲዎች መነሻ እንዲሆን አዘጋጅቶ መላክና  አተገባበሩን መከታተልና መደገፍ የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡

የተገኙ ዋና ዋና ውጤቶች

 1. በለውጥ ሠራዊት ግንባታ፣ በመልካም አስተዳደርን ለማስፈን እና ኪራይ ሰብሳቢነትን ለመታገል ተገቢውን የአመለካከት ለውጥና ግንዛቤ ተይዟል፤
 2. በክፍሉ በተደራጀ የተገልጋዮች አስተያየት መዝገብ በ2008 ዓ.ም አስተያየት ከሰጡ 137 ደንበኞች 135 (98.5%) በተሰጣቸዉ አገልግሎት የረኩ መሆኑ፤
 3. ሰራተኞች በለዉጥ መሳሪያዎች አስፈላጊነትና አጠቃቀም ላይ ያላቸዉ ግንዛቤና ክህሎት ተሻሽሏል፤
 4. በከፍተኛ ትምህርት የአመራርና ፈጻሚን አቅም መገንባት ተችሏል፤
 5. ያልተመዘገበ እንዳልተሰራ  ስለሚቆጠር ሥራዎችን  እየገመገሙ መመዝገብ ባህል እየሆነ መጥቷል፤
 6. ለተቋማት የልምድ መለዋወጫ መድረክ በማዘጋጀት ተቋማት ወደ ተቀራረበ አሰራር እንዲመጡ አስችሏል፡፡

ዋና ዋና የቀጣይ ትኩረት  አቅጣጫዎች
በሥራ ክፍሉ እና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (በሰራተኛዉና ማህበረሰቡ ዘንድ) የሚታየዉን  የአመለካከት፤ ክህሎትና ግብአት እጥረት ከሥር ከሥሩ እየለዩ ማብቃት፤

መልካም አስተዳደር የስራዎች ሁሉ አስኳል(yoke) መሆኑን ተገንዝቦ በየደረጃዉ ለማረጋገጥ መሥራት፤

የኪራይ  ሰብሳቢነት  አመለካከትና  ተግባር  በአደረጃጀት  በተጀመረው  አግባብ  እየፈቱ መሄድ፤

 በስራ ክፍሉና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያሉ አደረጃጀቶችን ሳያቆራርጡ በተቀመጠው ፕሮግራም መሰረት አጠናክሮ በማስቀጠል የከፍተኛ ትምህርት ፍትሃዊነትና ጥራት ማሻሻል፤

በስራ ላይ ያሉ ደንቦችና መመሪያዎች ላይ በአተገባበር የሚታዩትን ክፍተቶች በማጥናት ማሻሻልና በአዲስ መዘጋጀት ያለባቸውን የአፈጻጸም መመሪያዎች ማዘጋጀት   

በከፍተኛ ትምህርት አስ/ጉ/ጄ/ዳይሬክቶሬት ያሉ የህትመት ውጤቶች

 • ከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁ.650/2001
 • ከፍተኛ ትምህርት ወጪ መጋራት ደንብ ቁጥር 154/2000
 • ከፍተኛ ትምህርት ወጪ መጋራት አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 001/2004

Address Address

አድራሻ

በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ

የአስተዳደር ጉዳዮች ጀነራል ዳይሬክቶሬት

ስልክ፡- 251 011 156 5566

ፋክስ፡- 251 0111 56 55 65

Directorates and Departments Directorates and Departments