የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ

የከፍተኛ ትምህርት ግብ በተለያዩ መስኮች ተገቢው ዕውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ያላቸው ተወዳዳሪ፣ ተመራቂዎችን ማፍራት፣ በማህበረሰብ ፍላጎትና በሀገር ዕድገት ተመስርቶ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማምጣት የሚችል ጥናትና ምርምር ማካሄድ፣ በትምህርትና ጥናትና ምርምር በምክንያት፣ በዲሞክራሲ፣ በብዙሃን ባህልና እሴቶች በመመስረት የነጻነት መርሆችን ማለትም የአመለካከትና የሀሳብ ልውውጥን ማሳደግ ነው፡፡

 

የከፍተኛ ትምህርት ዓላማና ተግባራት፡ የፖሊሲው ዓላማ የከፍተኛ ትምህርትን መጠንና ጥራት ማሳደግ ነው፡፡ ዩኒቭርስቲዎችን በማስፋፋትና በማጠናከር ተማሪዎችን የመቀበል አቅማቸውን ማሳደግ፡፡ አዳዲስ ዩኒቭርስቲዎች ይገነባሉ፡፤ ነባሮች ይጠናከራሉ፡፡ በተጎጂዎችና በሌሎች መካከል ላለው የተሳትፎ ልዩነት ምላሽ ይሰጣል፡፡ በዩኒቭርስቲዎች የሴት ተማሪዎችን ተሳትፎ ማሳደግ፣ ሴት መምህራንን በማስተማር፣ በጥናትና ምርምር፣ በአመራርና በአስተዳደር፣ በከፍተኛ ትምህርት ማሳደግ ዋና የፖሊሲ ዓላማዎች ናቸው፡፡ የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎ በዩኒቭርስቲዎች እንዲያድግ ትኩረት ይሰጣል፡፡

 

የመንግስት ወጭን ለመቀነስና ፍትሐዊ የሀብት ክፍልን በሴክተሩ ለማስፈን አዲስ የወጭ መመለስ ፖሊሲዎች ይፈተሻሉ፣ በዩኒቭርስቲዎችና በቀጣሪዎች ያለውን የግንኙነት አግባብ በማሻሻል በተመራቂዎችና በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ባለው የቅጥር ገበያ መመጣጠንን ይበልጥ ለማረጋገጥ፣ የዩኒቭርስቲዎች መምህራን የትምህርት ደረጃ ይሻሻላል፡፡ (ወደ ሁለተኛ ዲግሪና ሶስተኛ ዲግሪ)

 

የዩኒቭርስቲዎች የጥናትና ምርምር አቅም በውጤት ተኮር ሥርዓት የማህበረሰብና የሀገር ዕድገት የሚያጎለብቱ ጥናትና ምርምሮችና ተመራማሪዎችን ዕውቅና በመስጠት፣ በመሸለም ይጎለብታል፡፡ በፖሊሲዎች በተቋማት መካከል የሚደረግ የጥራት ማረጋገጫ ሥርዓት የመሰረታል፣ የመርሃ ግብሮች የግምገማ ሥርዓትና ክለሳ ይቀጥላል፡፡ በየኒዓለም አቀፍ ተቋማት መካከል ሚኖረው ትብብር ይቀጥላል፡፡