የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ማስተባበሪያ  

 1. ዳራ

የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት በሀገራችን  ረጅም ታሪክ ያለው መሆኑ ይታወቃል፡፡ሆኖም ግን ማስተባበሪያው አሁን ባለበት ደረጃ ራሱን ችሎ  በ2003 ዓ.ም ተቋቋመ፡፡   ማስተባበሪያው የተቋቋመበት ዋነኛ  አላማ በመደበኛው የትምህርት አቅርቦት የመማር እድል ያላገኙ እድሜያቸው 15 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ወጣቶችና ጎልማሶች መደበኛ ባልሆነ የትምህርት አቅርቦት ስልቶች የትምህርት ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡ ፋይዳውም፡-

 • የተቀናጀ ተግባር ተኮር የጐልማሶች ትምህርት የሰው ሀብት ልማትን በማሳደግ የአገር እድገትና ልማትን ያፋጥናል፣

 • ምርታማነትን በማሳደግ የነፍስ ወከፍና አገራዊ ገቢን ያሳድጋል፣

 • የተቀናጀ ተግባር ተኮር የጐልማሶች ትምህርት ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ ለመፍጠር ያስችላል፣

 • የተቀናጀ ተግባር ተኮር የጐልማሶች ትምህርት የመልካም አስተዳደር ሥርዓትን በማጎልበት የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታን ያፋጥናል፣

 • የልማት መርኀ ግብሮቻችንን በማቀናጀት ጊዜንና ሀብትን በኣግባቡ ለመጠቀም ያስችላል፣

 1. መርሃ-ግብርሮች ዋና ዋና ግብ/ቦችና አላማዎች

ሁለት ዋና ዋና መርሀ ግብሮች አሉ፡ እነዚህም፡-

አንደኛው የተቀናጀ ተግባር ተኮር የጐልማሶች ትምህርት በጐልማሶች ባህርይና ስነልቦና ላይ ያተኮረ፣ የጐልማሶችን ልምድ፣ እውቀትና ክህሎት መነሻ በማድረግና ይህንኑ በማጐልበት ወደ ተሻለ ደረጃ የሚያሸጋግር አዲስ ዓይነት የቴክኖሎጂ ግብዓትና አሠራርን በማስተዋወቅ ራስን፣ አካባቢን፣ ማህበረሰብን ብሎም አገርን የማልማት ሂደት ነው፡፡ የመማማሪያ ይዘቶችም ጐልማሶች በሕይወታቸው በዕለት ተዕለት ኑሮአቸው ማንበብን፣ መጻፍንና ማስላትን እንዲያውቁ እና እንዲተገብሩ ለማስቻል የተዘጋጀ ኘሮግራም ነው፡፡

ሁለተኛው ድህረ የተቀናጀ ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት ፕሮግራም፡- ማለት የሁለት ዓመቱን የተቀናጀ ተግባር   ተኮር የጎልማሶች ትምህርት ፕሮግራም ያጠናቀቁ፤  በተወሰነ  ደረጃ   ማንበብ፣ መጻፍና ማስላት የሚችሉ  መደበኛ  የአንደኛ ደረጃ  የመጀመሪያ ሣይክል  ትምህርታቸው  ሳያጠናቅቁ  ያቋረጡ  ወጣቶችና  ጎልማሶች የሚሳተፉበት ፕሮግራም ማለት ነው፡፡

 

ዓላማ፡-

ዘላቂ የሕይወት ዘመን የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ የትምህርትና ሥልጠና ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል እንደፍላጎቱ በመስጠት ለራሱ፣ ለኅብረተሰቡና ለሀገሩ የምጣኔ ሀብት እድገት የሚተጋ የተማረ ኅብረተሰብ መፍጠር ሲሆን

ግቦች/

 • በጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ፕሮግራሞች የጎልማሶችን ተሳትፎ አድጎል፤ የማይምነት ግርሻ መከላክያ አማራጮችም ቀርበዋል፡፡
 • በጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ፕሮግራሞች የሴቶች ተሳትፎ ጨምሯል።
 • ፖሊሲና የሕግ ማዕቀፍ የተዘጋጀለት ጠናከረና ውጤታማ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ተቋማዊ አመራርና አደረጃጀት ተፈጥሮ ወደ ትግበራ ገብቷል፡፡
 • ለታዳጊ ክልሎች ከአካባቢያቸው ጋር የተጣጣመና የተገናዘበ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች ቀርበዋል።
 • የአመቻቾች የሥልጠና ደረጃ፣ ለትምህርት ግባቶችና ለትምህርት አሰጣጡ አጥጋቢ የብቃት መለኪያ ሰነድ ተዘጋጅቶ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ተጠብቋል።
 • በጎልማሶችና መደበኛ ባልሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች ልዩ ፍላጎት ያላቸው ጎልማሶች ተሳትፎ አድጓል።
 1. አደረጃጀት

የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ማስተባበሪያ በቀጥታ ተጠሪነቱ ለአጠቃለይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሲሆን በስሩም አንድ ሀላፊ፣ 8 ባለሙዎች እና 2 ድጋፍ ሰጪ በድምሩ 10 ሰራተኞች ይገኛሉ፡፡

 1. ዋና ዋና ተግባራት

የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ  ትማህርት ማስተባበሪያ በስሩ ባሉ ሰራተኞች እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ተግባራት ያከናውናል፡፡ እነሱም፤-

 • መርሀግብሩ የሚመራበትን የተለያዩ እስትራተጂክ ሰነዶችን ያዘጋጃል ለአፈፃፀም ወደ ክልሎች እንዲሰራጩ ያደርጋል  በአፈፃፀም ላይም ድጋፍና ከትትል ያደርጋል፡፡ይህንንም መሰረት አድርጎ ግብረ መልስ ይሰጣል፡፡
 • ከመርሀ ግብሩ ጋር የተያያዙና ፍላጎትን መሰረት ባደረገ መልኩ  የተለያዩ የስልጠና ሰነዶችን ያዘጋጅል ፤ለክልል አስፈፃሚዎችና ፈፃሚዎች ያሰልጣኞች ስልጠና ይሰጣል፡ስልጠናውም በሚፈለገው መልኩ ወደታች ስለመውረዱ ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ያደረጋል
 • በየደረጃው ላለው አመራር፤ፈፃሚ አስፈፃሚ እንዲሁም ለመላው ሕብረተሰብ የተለያዩ አግባቦችን በመጠቀም በመርሀ ግብሩ ዙሪያ ተገቢውን ግንዛቤ ማስጨበጥ እንዲሁም  መድረኮችን በመፍጠር ንቅናቄ መፍጠር
 • ለመርሀ ግብሩ ማስፈፀሚያ የሚሆን በጀት ለማፈላለግ የሚያስችል ፕሮጀክት ፕሮፖዛል ያዘጋጃል ለሚመለከተው ክፍል/አካል መላኩን እንዲሁም ያለበትን ደረጃ ይከታተላል፡፡በጀት ሲገኝም ስራ ላይ ያውላል፡፡
 • በየደረጃው ስለፕሮግራሙ አፈፃፀም ሂደት በተመለከተ ከክልሎችና ከህዝብ ክንፎች ጋር በመሆን በየሶስት ወሩ ግምገማ ያካሂዳል ለሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን ሪፖርትና ግብረ መልስ ይሰጣል፡፤ በአፈፃፀሙም ሂደት ተገቢውን ክትትል ያደርጋል
 • በፕሮግራሙ ትግበራ ሂደት  ምርጥ  ተሞክሮዎችን በመለየት በመቀመር በተለያዩ አግባቦች ለክልሎች እንዲሰራጩ ያደርጋል
 • መርሀግብሩ በአገር ፤ በቤተሰብ፤ በግለሰብ እንዲሁም በማህበረሰብ ደረጃ ያስገኘውን ፋይዳ እንዲሁም የተሻለ አደረጃጀት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ያጠናል/ያስጠናል የጥናቱን ውጤት ለሚመለከተው አካል በማቅረብ ተቀባይነት ሲያገኝ ለመርሀ ግብሩ መሻሻል ተግባራዊ ያደርጋል
 • ፕሮግራሙ የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ተሳትፎ የሚሻ በመኆኑ ተቀናጅተው መርሀግብሩን የሚደግፉበትን ስልት በመንደፍ ተግባራዊ ያደርጋል
 1.  የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ማስተባበሪያ ከተቁአቁመበት ጀምሮ እስከ 2008 የተገኙ ዋና ዋና ውጤቶች

ዕድሜያቸው ከ15-60 ዓመት ያሉ መጻፍና ማንበብና ማስላት ከማይችሉ 20.5 ሚሊየን ጎልማሶች ውስጥ 3.9 ሚሊየን ሴቶችና 3.9 ሚሊየን ወንዶች በድምሩ 7.3 ሚሊየን ጎልማሶች የሁለት አመት ትምህርት በማጠናቀቅ ማንበብ መፃፍ ዕና ማስላት በመቻል በኑሮአቸው የተሻለ ለውጥ አሳይተዋል፡፡ ለምሳሌም አዳዲስ የአስተራረስ ዘዴዎችንና ግብአቶችን በመጠቀም ምርታማነታቸው ማሳደግ፣ የግልና የአካባቢ ንጽህና አጠባበቃቸው ማሻሻል፣ የእናቶችና የህጻናትን ሞት ለመቀነስ በሚደረገው  ጥረት አስተዋጽኦ ማበርከት ችለዋል፡፡

 1. በጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ማስተባበሪያ በሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ የተቀመጡ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች
 • የጎልማሶች ትምህርት አመራርና አደረጃጀት፣ የፖሊሲና የሕግ ማዕቀፍ፣ ፍትሐዊነት ተደራሽነት፣ ጥራትና ተገቢነት፣ እንዲሁም የድህረ የተቀናጀ ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት ፕሮግራም ናቸው፡፡
 1. የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ማስተባበሪያ ማስተግበሪያ ሰነዶችና የህትመት ውጤቶች
 • ሀገር አቀፍ የጎልማሶች ትምህርት ስትራተጂ 2000 ዓ/ም
 • የተግባር ተኮር የጎልማሶች መሰረተ ትምህርት የአመቻቾች ማኑዋል 2001 ዓ/ም
 • ተግባር ተኮር የጎልማሶች መሰረተ ትምህርት/FAL/ አፈፃፀም መመሪያ 2002 ዓ/ም
 • የተቀናጀ የተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት ስርአተ ትምህርት ማእቀፍ፡2003 ዓ/ም
 • የተቀናጀ የተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት አጥጋቢ የመማር ብቃት መለኪያ፣2004 ዓ/ም
 • የተቀናጀ የተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት መማማሪያ ፅሁፍ አዘገጃጀት ማእቀፍ፡2006 ዓ/ም
 • የተቀናጀ የተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት የሱፐርቪዥን ማኑዋል፡2006 ዓ/ም

የተለያዩ መረጃዎች የተለያዩ መረጃዎች

አድራሻ አድራሻ

የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ማስተባበሪያ

አዳነ ማሞ ተገኔ፣ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ማስተባበሪያ ክፍል ሃላፊ

 

ስልክ 0911468106

ስልክ ቁጥር 0111550733  ኢማይል adultedumoe@gmail.com

ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1367

ኢ-ሜይል adane.mamo@yahoo.com

ዳይሬክቶሬቶች እና የስራ ክፍሎች ዳይሬክቶሬቶች እና የስራ ክፍሎች