የኢትዮጵያ ብሄራዊ ዩኔስኮ ኤጀንሲ

መግቢያ

የዓለም አቀፍ ዩኔስኮ አጠቃላይ ገጽታ፡ ዩኔስኮ በዓለማችን ታሪክ ውስጥ እጅግ አሰቃቂውና አውዳሚው የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ባበቃበት ማግስት ..16 ኖቨምበር 1946 ተመሠረተ፡፡ በወቅቱ የድርጅቱን ሕገደንብ /Constitution/ በፊርማቸው በማጽደቅ አባል የሆኑት ሀገራት ብዛት 37 ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት 195 ደርሷል፡፡

ኢትዮጵያም የድርጅቱ አባል የሆነችው ... 1955 /በአገራችን አቆጣጠር 1947 ./ ከአፍርካ አህጉር አራተኛ በመሆን ነው፡፡

በዩኔስኮ ሕገ ደንብ መግቢያ ላይ የሰፈረው ጥቅስ እንደ መርህ ተደርጎ የሚጠቀሰው የድርጅቱን አመሰራረት ይዘትና ግብ ያመላክታል፡፡ ይኸውም “Since wars begin in the minds of men, it is in the minds of men that the defenses of peace must be constructed.” 

በዚህ መርህ መሠረት ዩኔስኮ ሦስት ዋና ዋና ተልኮዎች አሉት፡፡ እነርሱም

 1. ዓለማ አቀፍ ምሁራን ትብብርን ማጠናከር  /International Intellectual Cooperation/
 2. የልማት ትብብር ማመቻቸት /Development Cooperation/
 3. በሥነ ምግባር ጉዳዮች ዙሪያ /Ethical Action) ናቸው፡፡

ዓለም አቀፍ ዩኔስኮ ዋና መሥሪያ ቤቱ ፈረንሳይ ዋና ከተማ ፖሪስ ነው፡፡ ይህ ድርጅት ኘሮግራሙን ለመተግበር ሦስት ዋና ዋና አካላት አሉት፡፡ እነሱም

 1. የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ /Executive Board/
 2. ጠቅላላ ጉባኤ /General Assembly/ እና
 3. ሴክሬታሪያት /Secretariat/ ሲሆኑ ዋነኛው ሥልጣን ግን የጠቅላላ ጉባኤው ነው፡፡ ምክንያቱም እያንዳንዱ የድርጅቱ አባል አገር የሚወከልበት አካል በመሆኑና የሉዓላዊነታቸውም መግለጫ በመሆኑ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዩኔስኮ 1961. በነጋሪት ጋዜጣ በወጣው ደንብ ቁጥር 55/61 በትምህርት ሚኒስቴር የሚደገፍ ሆኖም ራሱን ችሎ የተመሠረተ ኮሚሽን ነው፡፡

ዓላማ

 1. ከዩኔስኮ ጋር በቅርብ በመተባበር በኢትዮጵያ ውስጥ የትምህርት፤ የሣይንስ፤ የባህልና ኮሚኒኬሽን ሥራዎች ማበረታትና ማስፋፋት
 2. በኢትዮጵያ ሕዝብና በዓለም ሕዝብ መካከል  የትምህርት፤ የሣይንስ፤ የባህልና ኮሙኒኬሽን ተግባራትን እየተስፋፋ እንዲሄድ መርዳት፤ 

ተግባሮች

/ ከዓላማዎቹ ጋር በተያያዙ ጉዳዩች ጥናት ማድረግና የጥናቱን ውጤቶች አሳትሞ ማውጣት

/ ከዩኔስኮ ጋራ ግንኙነት ያላቸውን በኢትዮጵያ ውስጥ የትምህርት፤ የሣይንስ፤ የባህልና ኮሙዩኒኬሽን ሥራዎች ማስተባበርና ማስፋፋት፤

/ በሀገሪቱ ውስጥ ካሉ የመንግስትና የግል ድርጅቶች ጋር መተባበርና ከዩኔስኮ ጋር ስላላቸው የሥራ ግንኙነት  ለነዚህ ድርጅቶች ምክር መስጠት፤

/ የራሱን ዓላማዎች ለመፈጸም ከዩኔስኮ ጋራ ኘሮግራሞች የሚስፋፋበትን መንገድና ዘዴ ማጥናትና የዩኔስኮ ኘሮግራሞች በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገባ መፈጸማቸውን መከታተል፤

/ ለኢትዮጵያ የሚሰጠው የዩኔስኮ  የቴክኒክና የገንዘብ እርዳታና እንዲሁም በዩኔስኮ አማካይነት የሚሰጠው ማንኛውም ሌላ እርዳታ በሚገባ መገኘቱን ማረጋገጥ፤

 / ለዩኔስኮ ዋና መሪያ ቤት አባል አገሮች ብሔራዊ ኮሚሽኖችና እነዚህን ለመሰሉት ሌሎች ኢንተርናሽናል ድርጅቶች አስፈላጊውን መረጃ መስጠት፤

/ ከዩኔስኮና ከሌሎች አባል አገሮች ጋራ ግንኙነት ስላላቸው በጽ/ቤቱ የትምህርት፤ የሳይንስ፤ የባህልና ኮሙዩኒኬሽን ሥራዎች በተገቢው መገናኛ አማካይነት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማስረዳትና እንዲሁም ስለትምህርት፤ ስለሳይንስ፤ ስለባህልና ኮሙዪኒኬሽን ጉዳዮች መረጃዎችን ለዩኔስኮና አባል አገሮች ማሰራጨት፤

/ ለዩኔስኮ ጉባኤዎችና ዩኔስኮ ጠቀስ ወደሆኑት ሌሎች ስብሰባዎች የሚላኩት የኢትዮጵያ መልእክተኞች ስለጉዳዩ ተገቢው መረጃና ምክር መስጠት፤

/ ከዩኔስኮ ዋና መሠሪያ ቤት ጋር በመተባበር የዩኔስኮ ኘሮግራሞች በሥራ ላይ በሚውሉበት ጉዳይ ተካፋይ መሆን፤

/ ከግል ምንጮች ስጦታና እርዳታ ለመቀበል የሚቻልበትን መመሪያ መወሰን፤

በኢትዩጵያ ብሔራዊ ዩኔስኮ ሴክሬታሪያት አማካኝነት ከዓለም አቀፍ ዩኔስኮ /ቤት የተለያዩ የትብብር ኘሮግራሞች የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህም ዋና ዋናዎቹ፤

 1. ፌሎሽኘ ኘሮግራም
 2. የፓርትስፔሽን ኘሮግራም
 3. የፋይናንስ፤ ማቴሪያልና ቴክኒካል እርዳታ
 4. የእውቀት ሽግግር፤ የልምድ ልውውጥ /ወርክሾኘ፤ ኮንፈረንስ ወዘተ.../ ተሳትፎ፤
 5. የቤተ መጽሀፍት፤ የዶክመንቴሽንና የተለያዩ የመረጃ አገልግሎቶች፤
 6. ለምርምር ሥራዎች የሚሰጥ የገንዘብ ድጋፍ / research grant/
 7. የተለያዩ አለም አቀፍ ሽልማቶች
 8. ለድንገተኛ  አደጋ የሚሰጥ የገንዘብ ድጋፍ ናቸው፡፡

በኤጀንሲው ዶክመንተሽን ማእከል የሚገኙ የመረጃ ዓይነቶች፤

 • በትምርት፤ በሳይንስ፤በማህበራዊ ሳይንስና በኮሙዩኒኬሽን ዙሪያ ጥናታዊ ሰነዶች፤
 • በዩኔስኮ ልዩ ልዩ ስብሰባዎች የተላለፉ ወሳኔዎችና የስምምነት ማእቀፎች፤
 • ከዩኔስኮ ጋር የተያያዙ ሪፖርቶች፤
 • በሳይንስና በባህል ላይ ያተኩሩ መጽሐፍቶች
 • ጋዜጦችና መጽሄቶች ይገኛሉ

አገልግሎት የሚሰጥበት ጊዜ፡- ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ በመደበኛ የሥራ ሰዓት

የኢትዮጵያ ቅርሶች እስካሁን በዮኔስኮ በዓለም አቀፍ ቅርስነት የተመዘገቡት 10 ናቸው፡፡ እነሱም

 1. የሰሜን ብሄራዊ የተፈጥሮ ፓርክ
 2. የላልበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን
 3. የፋሲል ግቢ
 4. የታችኛው  አዋሽ ሸለቆ
 5. የጢያ ትክል ድንጋይ
 6. የአክሱም ሐውልት
 7. የታችኛው ኦሞ ሸለቆ  
 8. የሐረር ጀጐል ግንብ
 9. የኮንሶ መልካአምድር
 10. የሸካ ጥብቅ ደን  ሲሆኑ፤

ሌሎች በዓለም ቅርስነት ሊመዘገቡ የተመረጡ ቅርሶች፡-

/ የመስቀል በዓል አከባበር ስረዓት፤

/ ድሬ ሼክ ሁሴን የአምልኮ ስፍራ

/ የሶፍ ኡመር ዋሻ

/ የይምራሃነ ክርስቶስ ሥልጣኔ

/ የጌድዎ አገር በቀል የእርሻ ደን አሰራር ዘዴ

    የመሳሰሉ ናቸው፡፡

አድራሻ አድራሻ

ለበለጠ መረጃ:

የብሄራዊ የዩኔስኮ ኤጀንሲ

ትምህርት ሚኒስቴር

ስልክ +251(0) 111552519

ፖሳቁ 2996, አዲስ አበባ

ኢሜይል: naueth@gmail.com

ዳይሬክቶሬቶች እና የስራ ክፍሎች ዳይሬክቶሬቶች እና የስራ ክፍሎች