ዜናዎች ዜናዎች

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚካሄዱ የትምህርትና ሥልጠና ሥራዎች ውጤታማነት ተማሪዎች፣ መምህራን ፣ወላጆችና ህብረተሰቡ ኃላፊነታቸውን በላቀ ደረጃ ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ

 በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚካሄዱ የትምህርትና ሥልጠና ሥራዎች  ውጤታማነት ተማሪዎች፣ መምህራን ፣ወላጆችና ህብረተሰቡ ኃላፊነታቸውን በላቀ ደረጃ  ሊወጡ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ አስታወቁ፡፡

  • የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ህብረ-ብሔራዊነትና ኢትዮጵያዊነት የሚገነባባቸው ተቋማት እንጂ ተግባራቸው በጥቂት ችግር ፈጣሪዎች የሚስተጓጎል አለመሆኑንም ገለጹ
  • 141ሺህ አዲስ ተማሪዎችን ጨምሮ ከ700 ሺህ በላይ ተማሪዎች በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመማር ላይ

መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ክቡር የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ሥራ አጀማመርና መፈጸም ባለባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ተቋማቱ  የመማሪያ ፣ የምርምር፣የቴክኖሎጂና  የማህበረሰብ አገልግሎት ማዕከላት ናቸው፡፡

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከትምህርትና ስልጠና ባሻገር ህብረ ብሔራዊነትና ኢትዮጵያዊነት የሚገነባባቸው ተቋማት በመሆናቸው መደበኛው የመማር ማስተማር ሥራቸው ሰላምን በማይሹ በጥቂት ተማሪዎች መስተጓጎል እንደሌለበት ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

በመሆኑም መንግስት እንደ እናትና አባት ተረክቦ እያስተማረ፣ እየመገበ፣ ህክምና እና ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን እያቀረበ የሚያሰለጥናቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ትምህርታቸው እንዳይስተጓጎል ችግር ፈጣሪዎችን ተጠያቂ ሊያደርጓቸው እንደሚገባ አስታውቀዋል፡፡

ወላጆችም ልጆቻቸው በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ በጥብቅ በመከታተል መምከር እንዳለባቸው፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮችና መምህራንም የተቋማቱን ህግና ሥርዓት ማክበርና የማስከበር ኃላፊነት እንዳለባቸው ክቡር ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ጥያቄ  ቢኖራቸው እንኳን አደረጃጀቱን ተጠቅመው በሠላማዊና በህጋዊ መንገድ ሊያቀርቡ እንደሚገባ ጠቁመው ከዚህ ውጪ  ሠላምን ለማወክ የሚፈልጉ ችግር ፈጣሪዎች በዩኒቨርሲቲ እንዲቆዩ  እንደማይፈቀድላቸው አስታውቀዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቴክኖሎጂ መፍለቂያና የማህበረሰብ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በመሆናቸው የየአካባቢው ማህበረሰብም በባለቤትነት ችግር የሚፈጥሩ ውስን ተማሪዎችን አጋልጦ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል፡፡

በተያያዘ ግብዓት እየተሟላላቸው ያሉት አስራ አንዱ አዳዲስ ዩኒቨርስቲዎች በቅርቡ የተመደቡላቸውን ተማሪዎች ለመቀበል የመጨረሻ ዝግጅታቸውን በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኙ ዶክተር ጥላዬ  ጠቁመዋል፡፡

በትምህርት ዘመኑ በአጠቃላይ ከ700ሺህ የሚበልጡ ተማሪዎች በ36 የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በትምህርት ላይ እንደሚገኙ ከዚህ ውስጥ 141ሺህ ያህሉ አዲስ ገቢ ተማሪዎች መሆናቸውን፣ 43 በመቶ ያህሉ ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን ሚኒስትሩ ጨምረው መግለጻቸውን የትምህርት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዘግቧል፡፡


ዜናዎች

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚካሄዱ የትምህርትና ሥልጠና ሥራዎች ውጤታማነት ተማሪዎች፣ መምህራን ፣ወላጆችና ህብረተሰቡ ኃላፊነታቸውን በላቀ ደረጃ ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚካሄዱ የትምህርትና ሥልጠና ሥራዎች ውጤታማነት ተማሪዎች፣ መምህራን ፣ወላጆችና ህብረተሰቡ ኃላፊነታቸውን በላቀ ደረጃ ሊወጡ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ አስታወቁ፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ህብረ-ብሔራዊነትና ኢትዮጵያዊነት የሚገነባባቸው ተቋማት እንጂ ተግባራቸው በጥቂት ችግር ፈጣሪዎች የሚስተጓጎል አለመሆኑንም ገለጹ 141ሺህ አዲስ ተማሪዎችን ጨምሮ ከ700 ሺህ በላይ ተማሪዎች በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመማር ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ከ2011 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም የቅድመ ምረቃ ትምህርት መስኮች የብቃት መለኪያ አጠቃላይ ምዘና (የመውጫ ፈተና) ልተገበር ነው

ከ2011 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም የቅድመ ምርቃ ትምህርት መስኮች ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት የብቃት መለኪያ አጠቃላይ ምዘና (የመውጫ ፈተና) ወስደው አጥጋቢና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚጠበቅባቸው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የከፍተኛ ትምህርት ጥራትን በተለይም የምሩቃንን ብቃትና ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ አጠቃላይ ምዘና ወይም የመውጫ ፈተና መስጠት የምሩቃንን ዕውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ለመመዘን የላቀ ሚና ከመጫወቱም በተጨማሪ የተመራቂ ተማሪዎች በራስ መተማመን ያጎለብታል፡፡

የምርምርና የፈጠራ ስራ ውድድር ኤግዚቪሽን ተካሄደ

የሂሳብና ሣይንስ ትምህርቶች ማሻሻያ ማዕከል ከስቴምስ ሲነርጂ ፣ከዩኔስኮ እና ከኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ ጋር በመተባበር "በሣይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ የበለፀገ ህብረተሰብ ለዘላቂ ሠላምና ልማት "በሚል መሪ ቃል አገር አቀፍ የምርምርና ፈጠራ ስራ ውድድር ኤግዚቪሽን በኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ ተካሄደ፡፡ የምርምርና የፈጠራ ስራ አውደ- ርዕይ መከፈቱን አስመልክቶ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ የኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር ሲሆኑ የኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ የኢትዮጵያን ሣይንስ ለማበልፀግ የተቋቋመ መሆኑን አስታውሰው ይህ ማዕከል የህብረተሰቡን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ እንዲሁም ቴክኖሎጂን የመጠቀም አቅሙን ለማጎልበት ለማስተማርና የሣይንስ ፖርሽን ለመፍጠር የተሰራ ሲሆን ቋሚ የሳይንስ ማዕከል ለመፍጠር ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፡፡ በመሆኑም በቅርቡም የሳይንስ ማዕከሉ ወደ ስራ ይገባል በዚህም ወጣቱ ወደ ሣይንስ በሄደ ቁጥር የሀገራችን ተስፋ እየለመለመ ይሄዳል ብለዋል፡፡

የሥርዓተ-ፆታ ማካተትና ተቋማዊ ማድረግ መከታተያ፣ መመዘኛና በደረጃ የመለያ ማዕቀፍ ላይ ስልጠና ተሰጠ

የትምህርት ሚኒስቴር ሥርዓተ ፆታ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሁሉም የሥራ ክፍሎች እና ከተጠሪ ተቋማት ለተውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች እየተሰጠ ባለው ስልጠና የሁለተኛ ቀን ውሎ በሥርዓተ-ፆታ ማካተትና ተቋማዊ ማድረግ መከታተያ፣ መመዘኛና በደረጃ የመለያ ማዕቀፍ ላይ ስልጠና ሰጠ ፡፡ ስልጠናውን የሰጡት በዳይሬክቶሬቱ የስርዓተ ፆታ ክትትልና ድጋፍ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ብርሃኑ አረጋ ሲሆኑ የዚህ ስልጠና ዋና አላማ በሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ያሉ የስራ ክፍሎች የሥርዓተ ፆታ እኩልነትና ሴቶችን ማብቃት ተቋማዊ ለማድረግ የሚያከናውኑትን ተግባራት በመመዘንና ተከታታይ ድጋፍ በመስጠት የሥርዓተ ፆታ እኩልነት በሁሉም ዘርፍ ለማረጋገጥ ብሎም የሀገራችንን የልማት ራዕይ ለማሳካት ነው ብለዋል፡፡

የመንግስታዊና ግብረሰናይ ድርጅቶች የጋራ ፎረም ውይይት ተካሄደ፡፡

ዛሬ ጥቅምት 20/2010 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር አዳራሽ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በትምህርት ስልጠና ዘርፍ የ2010 ዓ.ም ዋና ዋና ዕቅዶች ላይ ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል፡፡ በምክክር መድረኩ ተገኝተው የመድረኩን አላማ የገለጹት በትምህርት ሚኒስቴር የእቅድ ዝግጅትና ሃብት ማፈላለግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ ግርማ የመድረኩ ዋና አላማ የትምህርት ሴክተሩ እቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት ማድረግ ነው ብለዋል፡፡

ኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ ኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ

Communication Address:

Tel: +251-11-156-14-94

Fax: