26ኛው ሀገር አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ አመታዊ ጉባኤ ተካሄደ

26ኛው ሀገር አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ አመታዊ ጉባኤ ተካሄደ

በሀገራችን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መሰጠት ከተጀመረ ረጅም አመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም እሰከ 1980ዎቹ አጋማሽ ድረስ ይሰጥ የነበረው የስልጠና ስርዓት የመንግስት የልማት ስትራቴጂዎች መሰረት ያላደረገ፣ኢንዱስትረውን ደንበኛ አደርጎ ያልወሰደና ዜጎችን እኩል ተጠቃሚ ያላደረገ ስልጠና ባልተሟላና በተቆራረጠ መልኩ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

 

ይህንኑ ለመቅረፍና የዘርፉን ውጤታማነት ለማሳደግ  መንግስት 1992 . የተዘጋጀውን ውጤት  ተኮር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ስትራቴጂ ተከትሎ የስርዓት ለውጥ  በማድረግ ውጤትን መሰረት ያደረገ  የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቀርፆ እየተገበረ ይገኛል፡፡ 

 

በሀገራችን እየተመዘገቡ ያሉት ፈጣን ተከታታይና ዘላቂ የኢክኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት  ዕድገት ውስጥ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ማስፋፋት ትልቅ አስታዋጾ እያበረከተ ነው፡፡

 

በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ተሾመ ለማ 26ኛው ሀገር አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና  ዘርፍ አመታዊ ጉባኤ በንግግር በከፈቱበት ወቅት እንደተናገሩት ጉባኤው የተዘጋጀበት አላማ  በፌዴራልና በክልሎች የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲዎች፣ ኮሌጆችና ተቋማት 2009 . የመጀመሪያ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም የተገኙ ውጤቶች  ለመገምገምና በተለያዩ ተግዳሮቶች ሳቢያ በተያዘው ዕቅድ መሰረት ያልተከናወኑ ተግባራት በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫ ለመጠቆም ታስቦ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

 ሚኒስትሩ እንዳሉት መንግስት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የሚመራበትን ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ ፕሮግራሞችና ዕቅዶች ሳይቆራረጡ በማስተግበር በዘርፉ የሰው ሃይል በብቃትና በጥራት እንዲሁም በተደራጀ መልኩ በማፍራት ላይ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

 

እንደ አቶ ተሸመ  ገለጻ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ስራዎች በየጊዜው ለማሻሻል ዘላቂና ተከታታይነት ያለው  የህዝብ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥና   ረገድ ባለፉት ሁለት አስር ዓመታት  የታቀዱና በእቅድ አፈጻጸም የተገኙ ውጤቶች በርካታ ቢሆንም  የሰው ሃይል በጥራት በሚፈለገው ከማፍራት  አንፃር የትብብር ስልጠና በስትራቴጂው በተቀመጠው አገባብ ከኢንዱስትሪው ጋር አቅዶ መስራት ላይ፣ መረጃን በአግባቡ አደራጅቶ ከመያዝ የመረጃ ስርዓቱን ታዓማንና ወቅታዊ ከማድረግ አንፃር  አሁንም ክፍተቶች እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡

 

ዘርፉ በዋነኛነት ሰፊ የሰው ሃይል በመካከለኛና በዝቅተኛ ባለሙያነት በማብቃት ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ያለውን  የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና የሚመራበት ውጤት ተኮር ስትራቴጂና የህግ ማዕቀፍ  በመቅረፅና ስራ ላይ በማዋል ረገድ  ባለፉት አስር አመታት መጠነ ሰፊ  የህዝብ ተጠቃሚነት  ሊያረጋገጥ የሚችል ውጤት  እያተመዘገበ መምጣቱን ክቡር አቶ ተሸመ   ተናግረዋል፡፡

 

ሚኒስትሩ አክለው ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ስራችን ከግብሪና መሪ ወደ ኢንዱስትሪ መሪ ኢኮኖሚ የሚደረገው ጉዞ በጥራትና በተቀመጠለት ጊዜ አገባብ ለማሳካት ኢንዱስትሪው የሚፈለገውን ማለትም ገበያን መሰረት ያደረገ ዝቅተኛና መካከለኛ ደረጃ  ብቁና በቂ  የሰው ሃይል በማቅረብ  ሰዎች በራስ ስራ ዕድል ፈጠራ አንፃር በማዘጋጀት በተጨማሪ የስራ አጥነት ችግር ለመፍታት  የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንደሚሻ አቶ ተሸመ አስገንዝበዋል፡፡

 

የስልጠነውን የሰው ሃይል በጥራት በሚፈለገው ከማፍራት  አንፃር የትብብር ስልጠና በስትራቴጂው በተቀመጠው አገባብ ከኢንዱስትሪው ጋር አቅዶ መስራት፣ እንዲሁም የመረጃ ስርዓት  ታዓማንና ወቅታዊ ከማድረግ ላይ ውስንነቶች እንዳሉም  ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

 

እንደ አቶ ተሸመ ገለፃ የቴ//// ተቋማት የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከላት ለማድረግ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች መፈልፈያና የቴከተኖሎጂ አቅም ግንባት ሽግግር ማዕከል የበለጠ ማስፋትና ማሳደግ እንደሚገባም ሚኒስትሩ አስገነዝበዋል ፡፡

 

በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የቴክኒክና ሙያ ትመህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሃመድ ያሲን እንኋን ደህና መጣቸው መልዕክት ባስተላለፉበት  ወቅት እንደተናገሩት መንግስት የአርብቶ አደሩን የሙያ ፍላጎት ለሟሟላት /// በኤጀንሲ ደረጃ 2005 . እንዲቋቋም ከማድረጉም በተጨማሪ ለኤጀንሲው ልዩ ድጋፍና ክትትል  እያደረገ መሆኑን  ጠቁመዋል፡፡

 

አንዳንድ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና  ተቋማት የሚሰጡ ስልጠናዎች በከተማና ከተማ አካባቢዎች የሚካሄዱትን  ጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ስራ ዘርፎች ምርታማነታቸውን ለመጨመር ፣የምርትና የአገልግሎት ጥራታቸውን በማሻሻል የቴክኖሎጂ ሽግግሩን በሚገባ መተግበር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

 

በጉባኤው 2009 ሩብ  ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን በአፈጻጸም የታዩ ዕጥረቶችን ለመሙላት በሚያስችሉ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ተለይቷል።


ዜናዎች

የቀጣይ 5 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ይፋ ሆነ

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር "የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ለፍትሃዊነት " በሚል መሪ ቃል ለቀጣዩ 5 ዓመታት የሚተገበር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

አካል ጉዳተኞች እንደየችሎታቸውና እንደየፍላጎታቸው መማር እንደሚገባችዉ ተገለጸ፤

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ከሰኔ 04 - 11/2010 ዓ.ም በአካል ጉዳተኞች ትምህርት ስታንዳርድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱም ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የአካቶ ትምህርትና የስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች፤ከትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሀመድ አህመዲን የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጅ፣ የሚዲያ አካላትና የፀጥታ ኃይል እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በአንዳንድ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ክፍል መግባትና ለሌላ ተማሪ ለመፈተን የመሞከር አዝማሚያዎች ቢከሰቱም በየደረጃው በተሰማሩ የፈተናው ግብረ ኃይል አማካይነት ችግሮቹ እልባት ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርሁን ዱሬሳ ገለጹ፡፡ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች የተፈተኑት እና ከ70ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞችና ተቆጣጣሪዎች የተሳተፉበት ፈተና፣ በአንዳንድ ፈተና ጣቢያዎች ላይ ሞባይል ይዘው ክፍል መግባት፣ ለመኮረጅ መሞከር፣ ለሌላ ተማሪ ለመፈተን መሞከር ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩ ቀላልና በፈተና ደንብ የሚታይ ይሆናል፣ በአጠቃላይ ግን ፈተናው በታቀደለት ጊዜ በሠላም ተጠናቋል ብለዋል ዶ/ር ዘርሁን፡፡

በአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሠጠ፤

በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠና ከግንቦት 23-ግንቦት 27/2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ነው ፡፡