11ኛው ሃገራዊ የሴቶች ትምህርትና ስልጠና ፎረም ተካሄደ

11ኛው ሃገራዊ የሴቶች ትምህርትና ስልጠና ፎረም ተካሄደ

ሴቶችን በሃገራዊ ጉዳይ ላይ እንዲሳተፉና ብሎም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ያለመ አገር አቀፍ የሴቶች ትምህርት ፎረም ጉባኤ  በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ "የሴቶች ትምህርትና ተሳትፎ፣ተጠቃሚነትና ውጤታማነት ለሃገር እድገት ወሳኝ ነው"በሚል መሪ ቃል ጥር 22 ቀን 2009 ተካሄደ ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር /  ሽፈራው ተክለማርያም እንደተናገሩት በቁጥርና በአቅም ከፍተኛውን ድርሻ የያዙትን ሴቶች ያላካተተ የሃገር እድገት ጉዞ ሙሉ አይሆንም ያሉት ሚኒስትሩ የአንድ ሃገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዞ የሴቶች ተሳትፎ ወሳኝ ብቻ ሳይሆን ሌላ አማራጭም እንደሌለው ገልፀዋል። ሴቶች በኢትዮዽያ ልማት ላይ ያላቸውን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማስጠበቅና ለማሳደግ በፖሊሲ የታገዘ ስራ እየተሰራ መሆኑን እና ሴቶችን በለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ ከወንድሞቻቸው ጋር በመሰለፍ የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ላይ መንግስት ሰፊ ቁርጠኝነትን ያሳየ ሲሆን ይህም በተጨባጭ በፖሊሲዎችና  በህጎች ከህገመንግስታችን ጀምሮ ተደንግገዋል ብለዋል።

ይህ ሃገራዊ የሴቶች ትምህርትና ስልጠና ፎረም ጉባኤ ዋና አላማው ሴቶች በሃገራዊ ጉዳይ ላይ እንዲሳተፉና ብሎም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ነው ያሉት ደግሞ የህዝብተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤና የፎረሙ የበላይ ጠባቂ የተከበሩ / ሽታዬ ምንአለ ናቸው። / ሽታዬ አያይዘውም የትምህርትና ስልጠና ፎረሙ የተመሰረተው የህብረተሰቡ ግማሽ አካል የሆኑት ሴቶች በተለይም ደግሞ ወጣት ሴቶች በየደረጃው ባለው የትምህርት እርከን በተሟላ መንገድ ተሳታፊ እንዲሆኑና ከተሳትፎ ባሻገርም ውጤታማ በመሆን ለሃገራቸው ልማትና ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ  የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱና እራሳቸው እንዲጠቀሙ ለማስቻል መሆኑን ተናግረዋል።

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት / አባተ ጌታሁን በበኩላቸው ሴቶች በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ያላቸው ተሳትፎና የአመራርነት ሚና ለውጥ እያሳየ መሆኑን ተናግረው እስከ 2007 ድረስ 67 የነበሩትን ሴት መምህራን በአሁኑ ሰዓት 3እጥፍ በማሳደግ 226 ሴት መምህራን አድርሰናል ብለዋል።ፕሬዚዳንቱ ጨምረውም የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚሰሩት ስራዎቸ በሚያስገኙት ውጤት መሰረት ሊመዘኑ ይገባልም ብለዋል።

በእለቱ ለውይይት የሚሆን የመነሻ ሃሳብ  ፅሁፍ ያቀረቡት በትምህርት ሚኒስቴር የስርዓተ ፆታ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት / ኤልሳቤጥ ገሰሰ በሶስቱም የትምህርት ዘርፎቸ በስርዓተ ፆታ የልማት ፕሮግራሞችን ለመተግበር የሚያስችል የአደረጃጀት፣ አሰራርና አመራር ስርዓትን (በሰው ሃይል፣ በማቴሪያልና በበጀት)ማጠናከር፣በህዝብ ንቅናቄ እቅድ ውስጥ ስርዓተ ፆታን የተመለከቱ ችግሮችን በመለየት በህብረተሰብ ተሳትፎ እንዲፈቱ በጋራ መስራት እንዲሁም በታዳጊ ክልሎች በተለየ መልኩ የሴት ተማሪዎችን የትምህርትና ስልጠና ተሳትፎና ውጤታማነት ለማጎልበት ተቀናጅቶ መንቀሳቀስ እንደሚገባና በሴቶች ትምህርት ዙሪያ መልካም ተሞክሮዎችን በመቀመርና በማስፋት ለውጥ ማምጣት ይቻላል ብለዋል። በተጨማሪም በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጾታዊ ትንኮሳና ጥቃትንም በዘላቂነት ከትምህርትና ስልጠና ተቋማት መከላከልና ሙሉ በሙሉ እንዲወገዱ ማድረግና ተፈጽሞ ሲገኝም በመመሪያው መሰረት ሌሎችን የሚያስተምር እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ  ገልጸዋል።

በፎረሙ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና አመራሮች፣ከሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር፣ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ፣ከሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችና የስርዓተ ፆታ ጉዳይ ሃላፊዎች፣ከሁሉም ክልሎች የትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች፣የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ሃላፊዎችና የስርዓተ ፆታ ጉዳይ ሃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

በመጨረሻም ፎረሙ ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።


ዜናዎች

የቀጣይ 5 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ይፋ ሆነ

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር "የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ለፍትሃዊነት " በሚል መሪ ቃል ለቀጣዩ 5 ዓመታት የሚተገበር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

አካል ጉዳተኞች እንደየችሎታቸውና እንደየፍላጎታቸው መማር እንደሚገባችዉ ተገለጸ፤

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ከሰኔ 04 - 11/2010 ዓ.ም በአካል ጉዳተኞች ትምህርት ስታንዳርድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱም ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የአካቶ ትምህርትና የስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች፤ከትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሀመድ አህመዲን የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጅ፣ የሚዲያ አካላትና የፀጥታ ኃይል እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በአንዳንድ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ክፍል መግባትና ለሌላ ተማሪ ለመፈተን የመሞከር አዝማሚያዎች ቢከሰቱም በየደረጃው በተሰማሩ የፈተናው ግብረ ኃይል አማካይነት ችግሮቹ እልባት ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርሁን ዱሬሳ ገለጹ፡፡ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች የተፈተኑት እና ከ70ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞችና ተቆጣጣሪዎች የተሳተፉበት ፈተና፣ በአንዳንድ ፈተና ጣቢያዎች ላይ ሞባይል ይዘው ክፍል መግባት፣ ለመኮረጅ መሞከር፣ ለሌላ ተማሪ ለመፈተን መሞከር ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩ ቀላልና በፈተና ደንብ የሚታይ ይሆናል፣ በአጠቃላይ ግን ፈተናው በታቀደለት ጊዜ በሠላም ተጠናቋል ብለዋል ዶ/ር ዘርሁን፡፡

በአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሠጠ፤

በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠና ከግንቦት 23-ግንቦት 27/2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ነው ፡፡