ዜናዎች ዜናዎች

ትምህርት ሚኒስቴር ጠንካራ ሥነ-ልቦና፣ ባህሪ፣ እና አመለካከትን ለመፍጠር የሚረዳ ትምህርትን "Mind Education" ለማስፋፋት ከዓለም አቀፍ የወጣቶች ህብረት ጋር የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ

የኢ.... ትምህርት ሚኒስቴር በሀገሪቱ ውስጥ በሥልጠና መልክም ሆነ በመደበኛ ትምህርት ሥርዓተ-ትምህርት ውስጥ አካቶ ጠንካራ ሥነ-ልቦና፣ ባህሪ፣ እና አመለካከትን ለመፍጠር የሚረዳ ትምህርትን "Mind Education" በዘርፉ ውስጥ በስፋትና ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ለመስጠት የሚረዳ የስምምነት ሰነድ  መቀመጫውን በደቡብ ኮሪያ ባደረገው የዓለም አቀፍ የወጣቶች ህብረት ጋር በትምህርት ሚኒስቴር መጋቢት 05 ቀን 2009 . ተፈራረመ።

 

በትምህርት ሚኒስቴር በኩል የስምምነት ሰነዱን የፈረሙት የትምህርት ሚኒስትር ክቡር / ሽፈራው ክለማሪያም ሲሆኑ በዓለም አቀፍ ወጣቶች ህብረት በኩል የህብረቱ መሥራችና መሪ የሆኑት የደቡብ ኮሪያ ተወላጅ / ኦክሱ ፓርክ ናቸው። ክቡር ሚኒስትሩ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ይህ በደቡብ ኮሪያ የተጀመረውና በዓለም አቀፍ የወጣቶች ህብረት እየተስፋፋ ያለው ጠንካራ ሥነ-ልቦና፣ ባህሪ፣ እና አመለካከትን ለመፍጠር የሚረዳ ትምህርትን በተመለከተ አጫጭር ገለፃዎች ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሠራተኞችና ለተወሰኑ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሠራተኞች ተሰጥቶ ጥሩ ግብረ-መልስ የተገኘበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ክቡር ሚኒስተሩ ይህንን ጅማሬ በውጤታማ መልኩ አደራጀቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ለሆኑ መምህራኖቻችንን በአሰልጣኞች ሥልጠና (TOT) መልክማድረስ ይህ ስምምነት እገዛ እንደሚያደርግ አስገንዝበዋል፡፡ በቀጣይም ከታችኛው የትምህርትና ሥልጠና እርከን ጀምሮ እስከ ከፍተኛው ድረስ ትምህርቱን በመደበኛነት በአገሪቱ ሥርዓተ-ትምህርት ውስጥ አካቶ ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመስጠት የሚስችል አሰራር ለመዘርጋት የስምምነት ሰነዱ ዋነኛ መሠረት መሆኑን ዶክተር ሽፈራው ገልጸዋል። ይህ ትምህርት በትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ የሀገርን አደራ የሚረከቡ ሁለንተናዊ ብቃትንና ሥነ-ምግባርን የተላበሱ ምክንያታዊ አስተሳሰብ ያላቸውን ዜጎችን ለመፍጠር እየተደረገ ያለውን ጥረት በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ እንዲሆን ከፍተኛ ፋይዳ ያለው መሆኑን ገልጸዋል። ዶክተር ሽፈራው ለዚህ ሥራ መሳካት ከሁሉም በላይ የመላው ህዛበችን ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው  ህብረቱም ሆነ የደቡብ ኮሪያ መንግሥት እገዛ እንደ ከዚህ በፊቱ እንደማይለየን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

 

የዓለም አቀፍ የወጠቶች ህብረት መሥራችና መሪ የሆኑት የደቡብ ኮሪያው ተወላጅ የሆኑት / ኦክሱ ፓርክ ከፍርማ ሥነ-ሥርዓቱ በኃላ ኢትዮጵያ የዚህን ትምህርት ፋይዳ ተገንዝባ ለነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶቿ ለመስጠት ወስና በይፋ ወደ ሥራ መግባቷን አስመልክቶ ባደረጉት የእንኳን ደስ አላችሁ ንግግራቸው ውስጥ ትምህርቱ 10 ዓመታት ውስጥ በሀገሪቷ ሁለንተናዊ ልማት ላይ በግልጽ የሚታይ ተጽዕኖ እንደሚያሳይ ያለውን እምነት ጠቅሰው ትምህርቱ የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ የሚጠበቅባቸውን ትብብርና ድጋፍ  እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። ማህበሩ በተወሰኑ የአፍሪካ ሀገራት ዋና ከተሞች ላይ ቢሮዎችን ከፍቶ ሀለ-ገብ አገልግሎት የሚሰጥ የወጣቶች ማዕከል ለመገንባት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ጠቅሰው በቅርቡ በአዲስ አበባ ቢሮዎችን ለመክፈት እየተንቀሳቀሳ መሆኑንና የአዲስ አበባን የአፍሪካ መዲናነት ከግንዛቤ ባስገባ ሁኔታ በሌሎች አፍሪካ ሀገራት ከሚገነቡት ይበልጥ ጉዙፍ የሆነ ሀለ-ገብ የወጣቶች ማዕከል ለመገንበት ለኢትዮጵያ መንግሥት የመሬት ጥያቄ ማቅረቡንም ተናግረዋል። እንደሚያበረክት ተናግረዋል። / ኦክሱ  በማከል ትምህርቱ ከእድገት ጋር ተያይዞ በደቡብ ኮሪያ የመጠውን ማህበራዊ ችግር ማለትም የግለሰቦች ራስን ወይም ፍላጎትን ያለመግዘት (ያለመቆጣጠር) ችግር እንዲሁም በተስፋና በራዕይ መኖር ያለመቻልን፤በሌላ አገለለጽ  የዳካማ አእምሮ ባለቤት የሆኑ ዜጎች መበራከትን፤ይህ ችግር ኮሪያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ዜጎች በብዛት ራሳቸውን የሚያጠፉባት ዋነኛ ሀገር እንዲትሆን ያደረጋት ስለመሆኑ፣ለዚህም ችግር በደቡብ ኮሪያም ሆነ በአሁኑ ወቅት ለሌሎች ሀገራት እንደ መፍትሔ ሆኖ እያገለገለ ያለው  ይህ ”Mind Education” ወይም ”Mind seting Education” (ራስን ወይም ፍላጎትን ወይም ምኞትን በራስ" በቤተሰብና በሀገር አቅም ልክ የመግዛት ወይም የመቆጣጠር ትምህርት እና  ጠንካራ ሥነ-ልቦናና አእምሮን የመፍጠር) ትምህርት እንደሆነ ገልጸዋል።No comments yet. Be the first.
ዜናዎች

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚካሄዱ የትምህርትና ሥልጠና ሥራዎች ውጤታማነት ተማሪዎች፣ መምህራን ፣ወላጆችና ህብረተሰቡ ኃላፊነታቸውን በላቀ ደረጃ ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚካሄዱ የትምህርትና ሥልጠና ሥራዎች ውጤታማነት ተማሪዎች፣ መምህራን ፣ወላጆችና ህብረተሰቡ ኃላፊነታቸውን በላቀ ደረጃ ሊወጡ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ አስታወቁ፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ህብረ-ብሔራዊነትና ኢትዮጵያዊነት የሚገነባባቸው ተቋማት እንጂ ተግባራቸው በጥቂት ችግር ፈጣሪዎች የሚስተጓጎል አለመሆኑንም ገለጹ 141ሺህ አዲስ ተማሪዎችን ጨምሮ ከ700 ሺህ በላይ ተማሪዎች በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመማር ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ከ2011 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም የቅድመ ምረቃ ትምህርት መስኮች የብቃት መለኪያ አጠቃላይ ምዘና (የመውጫ ፈተና) ልተገበር ነው

ከ2011 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም የቅድመ ምርቃ ትምህርት መስኮች ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት የብቃት መለኪያ አጠቃላይ ምዘና (የመውጫ ፈተና) ወስደው አጥጋቢና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚጠበቅባቸው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የከፍተኛ ትምህርት ጥራትን በተለይም የምሩቃንን ብቃትና ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ አጠቃላይ ምዘና ወይም የመውጫ ፈተና መስጠት የምሩቃንን ዕውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ለመመዘን የላቀ ሚና ከመጫወቱም በተጨማሪ የተመራቂ ተማሪዎች በራስ መተማመን ያጎለብታል፡፡

የምርምርና የፈጠራ ስራ ውድድር ኤግዚቪሽን ተካሄደ

የሂሳብና ሣይንስ ትምህርቶች ማሻሻያ ማዕከል ከስቴምስ ሲነርጂ ፣ከዩኔስኮ እና ከኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ ጋር በመተባበር "በሣይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ የበለፀገ ህብረተሰብ ለዘላቂ ሠላምና ልማት "በሚል መሪ ቃል አገር አቀፍ የምርምርና ፈጠራ ስራ ውድድር ኤግዚቪሽን በኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ ተካሄደ፡፡ የምርምርና የፈጠራ ስራ አውደ- ርዕይ መከፈቱን አስመልክቶ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ የኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር ሲሆኑ የኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ የኢትዮጵያን ሣይንስ ለማበልፀግ የተቋቋመ መሆኑን አስታውሰው ይህ ማዕከል የህብረተሰቡን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ እንዲሁም ቴክኖሎጂን የመጠቀም አቅሙን ለማጎልበት ለማስተማርና የሣይንስ ፖርሽን ለመፍጠር የተሰራ ሲሆን ቋሚ የሳይንስ ማዕከል ለመፍጠር ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፡፡ በመሆኑም በቅርቡም የሳይንስ ማዕከሉ ወደ ስራ ይገባል በዚህም ወጣቱ ወደ ሣይንስ በሄደ ቁጥር የሀገራችን ተስፋ እየለመለመ ይሄዳል ብለዋል፡፡

የሥርዓተ-ፆታ ማካተትና ተቋማዊ ማድረግ መከታተያ፣ መመዘኛና በደረጃ የመለያ ማዕቀፍ ላይ ስልጠና ተሰጠ

የትምህርት ሚኒስቴር ሥርዓተ ፆታ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሁሉም የሥራ ክፍሎች እና ከተጠሪ ተቋማት ለተውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች እየተሰጠ ባለው ስልጠና የሁለተኛ ቀን ውሎ በሥርዓተ-ፆታ ማካተትና ተቋማዊ ማድረግ መከታተያ፣ መመዘኛና በደረጃ የመለያ ማዕቀፍ ላይ ስልጠና ሰጠ ፡፡ ስልጠናውን የሰጡት በዳይሬክቶሬቱ የስርዓተ ፆታ ክትትልና ድጋፍ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ብርሃኑ አረጋ ሲሆኑ የዚህ ስልጠና ዋና አላማ በሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ያሉ የስራ ክፍሎች የሥርዓተ ፆታ እኩልነትና ሴቶችን ማብቃት ተቋማዊ ለማድረግ የሚያከናውኑትን ተግባራት በመመዘንና ተከታታይ ድጋፍ በመስጠት የሥርዓተ ፆታ እኩልነት በሁሉም ዘርፍ ለማረጋገጥ ብሎም የሀገራችንን የልማት ራዕይ ለማሳካት ነው ብለዋል፡፡

የመንግስታዊና ግብረሰናይ ድርጅቶች የጋራ ፎረም ውይይት ተካሄደ፡፡

ዛሬ ጥቅምት 20/2010 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር አዳራሽ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በትምህርት ስልጠና ዘርፍ የ2010 ዓ.ም ዋና ዋና ዕቅዶች ላይ ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል፡፡ በምክክር መድረኩ ተገኝተው የመድረኩን አላማ የገለጹት በትምህርት ሚኒስቴር የእቅድ ዝግጅትና ሃብት ማፈላለግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ ግርማ የመድረኩ ዋና አላማ የትምህርት ሴክተሩ እቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት ማድረግ ነው ብለዋል፡፡