የውጤታማነት አሰራር/DELIVEROLOGY ስልጠና

የውጤታማነት አሰራር/DELIVEROLOGY ስልጠና

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ለከፍተኛ አመራሮች በውጤታማ አሰራር/ ደሊቨሮሎጂ/ ዙሪያ በተዘጋጀ መድረክ ላይ ተገኝተው መመሪያ በሰጡበት ወቅት እንዳስታወቁት የትምህርት ጥራትን በተቀመጡ የትምህርት ጥራት መመዘኛዎች ለማረጋገጥ /DELIVEROLOGY /የውጤታማነት አሰራር ዘዴን ተግባራዊ ማድረግ ወሳኝ ነው፡፡
ውጤታማ አሰራር/DELIVEROLOGY/ የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ ፕሮግራሞችን በማስጠበቅ፣ የትምህርት ሥርዓቱን በአመለካከት ቅኝት በማስተሳሰርና በቁርጠኝነት በመስራት ሊረጋገጥ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም አስገንዝበዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ሽፈራው ተክለ ማርያም በበኩላቸው የትምህርትና ስልጠና ዘርፉ ባለፉት 25 ዓመታት የተመዘገቡ ውጤቶችን በአመለካከት ጥራት ፣በሳይንሳዊ የአሰራር ሥርዓት መናበብ እየጎለበቱ መሄድ እንደሚገባቸው አስታውቀዋል፡፡
በጥራት የተካነ የውጤታማነት ሂደትና ውጤት የእቅዶቻችን ሁሉ ማጠንጠኛ በማድረግ አገራዊ ብልጽግናን ለማፋጠን፣የህዝብ እርካታን ለማረጋገጥና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ዕውን ለማድረግ የውጤታማነት አሰራር አማራጭ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ውጤታማ አሰራር/DELIVEROLOGY/በትምህርት መስኩ የምናስመዘግባቸውን ውጤቶች ጥራት፣ፍጥነትና ዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚያስችል በመሆኑ ሁሉም የትምህርት ሥራ አመራሮችና ባለድርሻዎች ለውጤታማነቱ መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው ሚኒስትሩ ዶክተር ሽፈራው አስገንዝበዋል፡፡
በውይይቱ ላይ በውጤታማነት አሰራር/DELIVEROLOGY / ዙሪያ ሰፊ ጥናትና ምርምር ያደረጉት ሰር ማይክል ባርበር የውጤታማ አሰራር ዙሪያ ያሉ ተሞክሮዎችንና መልካም ልምዶችን አስመልክተው ጽሁፍ አቅርበው በከፍተኛ አመራሮቹ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በመድረጉኩ ላይ ሚኒስትሮች፣የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ከንቲባዎች፣ የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶችና ሌሎችም በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና ባለድርሻዎች ተሳታፊ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዘግቧል፡፡


ዜናዎች

የቀጣይ 5 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ይፋ ሆነ

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር "የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ለፍትሃዊነት " በሚል መሪ ቃል ለቀጣዩ 5 ዓመታት የሚተገበር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

አካል ጉዳተኞች እንደየችሎታቸውና እንደየፍላጎታቸው መማር እንደሚገባችዉ ተገለጸ፤

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ከሰኔ 04 - 11/2010 ዓ.ም በአካል ጉዳተኞች ትምህርት ስታንዳርድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱም ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የአካቶ ትምህርትና የስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች፤ከትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሀመድ አህመዲን የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጅ፣ የሚዲያ አካላትና የፀጥታ ኃይል እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በአንዳንድ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ክፍል መግባትና ለሌላ ተማሪ ለመፈተን የመሞከር አዝማሚያዎች ቢከሰቱም በየደረጃው በተሰማሩ የፈተናው ግብረ ኃይል አማካይነት ችግሮቹ እልባት ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርሁን ዱሬሳ ገለጹ፡፡ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች የተፈተኑት እና ከ70ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞችና ተቆጣጣሪዎች የተሳተፉበት ፈተና፣ በአንዳንድ ፈተና ጣቢያዎች ላይ ሞባይል ይዘው ክፍል መግባት፣ ለመኮረጅ መሞከር፣ ለሌላ ተማሪ ለመፈተን መሞከር ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩ ቀላልና በፈተና ደንብ የሚታይ ይሆናል፣ በአጠቃላይ ግን ፈተናው በታቀደለት ጊዜ በሠላም ተጠናቋል ብለዋል ዶ/ር ዘርሁን፡፡

በአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሠጠ፤

በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠና ከግንቦት 23-ግንቦት 27/2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ነው ፡፡