(Deliverology) በላቀ ደረጃ አጠናክሮ ማስቀጠል

(Deliverology) በላቀ ደረጃ አጠናክሮ ማስቀጠል

ባለፉት ዓመታት በትምህርትና ስልጠና ዘርፉ የተመዘገቡ ስኬቶችን በውጤታማ የትግበራ ስኬት ሥርዓት (Deliverology) በላቀ ደረጃ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሀገር አቀፉ 2010 የትምህርት ሳምንት የትምህርት ሚኒስቴርና በስሩ የሚገኙ ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች ውይይት አድርገዋል፡፡
2010 የትምህርት ሳምንትን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴርትር ሠራተኞች ውይይት ባደረጉበት ወቅት የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር / ጥላዬ ጌቴ እንደገለፁት Deliverology ወይም የውጤታማ ትግበራ ስኬት ስርዓት የትምህርት ጥራትና ተገቢነትን በላቀ ደረጃ ለማስፈጸም ያስችላል፡፡
የውጤታማ ትግበራ ስኬት ስርዓት ቁርጠኝነትን ፣የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች መለየት፣ወሳኝ የሆኑ የተለጠጡና መፈጸም የሚችሉ ኢላማዎችን ማስቀመጥ፣አሳታፊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ጠንካራ ድጋፍና ክትትልን የሚጠይቅ መሆኑንም ክቡር ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም መላው የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞችና የዘርፉ ባለድርሻዎች በትምህርት ዘመኑ በውጤታማ ትግበራ ስኬት ስርዓትን በመጠቀም የትምህርት ጥራትና ተገቢነትን ለማረጋገጥና የትምህርቱን ሥራ ስኬታማ ለማድረግ ለተቀመጡ ግቦች ተፈጻሚነት በቁርጠኝነት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባቸው ክቡር / ጥላዬ አስገንዝበዋል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ክቡር / ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው በውጤታማ የትግበራ ስኬት ሥርዓት (Deliverology) 2010 ጀምሮ ተፈጻሚ በማድረግ 2012 መጨረሻ ከከፍተኛ ትምህርት ምሩቃን መካከል 80 በመቶ ያህሉን በተመረቁ 12 ወራት ውስጥ በሥራ ፈጠራና በቅጥር የስራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ግብ መቀመጡን ተናግረዋል፡፡
በቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ስልጠና ደግሞ 90 በመቶ ያህሉ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የራሳቸውን ሥራ በመፍጠርና ተቀጥረው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግና በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍም በየትምህርት እርከኑ ተማሪዎች 50 በበመቶና ከዚያም በላይ ሁለ-ገብ ብቃት ወይም ውጤት እንዲያስመዘግቡ ግብ መጣሉን ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል፡፡
በውይይቱ የውጤታማ ትግበራ ስኬት ሥርዓት (Deliverology) ጨምሮ በስነ ዜጋና ስነ ምግባር ትምህርት፣በ2009 አፈጻጸምና 2010 ዕቅድና በሌሎችም ውይይት የተደረገ ሲሆን በመድረኩም ከሠራተኞች የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው ውይይት የተደረገባቸውና በከፍተኛ አመራሩ ምላሽ የተሰጠባቸው መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዘገባ ያስረዳል፡፡


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡