የአጠቃላይ ትምህርት ተከታታይ የክፍል ውስጥ ምዘና ስትራቴጂ (CCA) ተዘጋጀ:

የአጠቃላይ ትምህርት ተከታታይ የክፍል ውስጥ ምዘና ስትራቴጂ (CCA) ተዘጋጀ:

በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የተከታታይ ክፍል ውስጥ ምዘና (CCA – Classroom Continuous Assessment) በአድስ መልክ ተዘጋጀ፡፡

ቀደም ተብሎ ይሰራበት የነበረው የተከታታይ ምዘና የተማሪዎችንና የመምህራንን ክህሎትና ዕውቀት በመዳሰስ ሁለቱን በማቀራረብ የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅ አንጻር ክፍተት የታዩበት በመሆኑ የክፍል ውስጥ ተከታታይ ምዘና ስትራቴጂ በአዲስ መልክ ማዘጋጀት እንዳስፈለገ ተገልጿል፡፡ በአዲሱ ተከታታይ የክፍል ውስጥ ምዘና ስትራቴጂ እንደተለመደው መምህሩ በሳምንት ወይም በወራት የተማሪዎችን ውጤት መዝኖ በወረቀት የሚያሰፍር ሳይሆን በተዘጋጀው የስትራቴጂው ማስተግበሪያ መመሪያና ማኑዋል መሠረት በየቀኑ በዕቅድ ተማሪዎችን እንዲሁም እራሱን በመፈተሽ የሚያበቃበት መሁኑን የገለጹት የስትራቴጂው ዝግጅት ግብረ ሃይል ሰብሳቢና የአፍ መፍቻ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር / እመቤት አበራ ናቸው፡፡

የስትራቴጂው ዝግጅት ዋና ዓላማ በአገር አቀፈፍ ደረጃ ወጥ በሆነ መልኩ የክፍል ውስጥ ተከታታይ ምዘናን ለማስኬድ ሲሆን ስትራቴጂውን በገንዘብ ከደገፈው USAID/GEQIP-E ፕሮጀክት ፕሮግራም ጋር የሚጣጣም በመሆኑ 2018 . ጀምሮ የሚተገበርና በፕሮጀክቱ ፕሮግራም መጨረሻ ዓመት ላይ አመርቂ ውጤት እንደሚጠበቅ ዳይሬክተሯ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከክልል ትምህርት ቢሮዎች፣ ከመምህራን ትምህርት ኮሌጆች፣ ከትምህርት ልማት አጋር ድርጅቶች በተውጣጡ ባለሙያዎች የስትራጂው ሰነዶች ከግንቦት 17-19/2010. በአዳማ ከተማ ተገምግመዋል፡፡ በቀጣይም በተዋረድ ለአሰልጣኞች፣ ለርዕሠ መምህራንና ለመምህራን ስልጠና እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

 


ዜናዎች

የቀጣይ 5 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ይፋ ሆነ

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር "የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ለፍትሃዊነት " በሚል መሪ ቃል ለቀጣዩ 5 ዓመታት የሚተገበር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

አካል ጉዳተኞች እንደየችሎታቸውና እንደየፍላጎታቸው መማር እንደሚገባችዉ ተገለጸ፤

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ከሰኔ 04 - 11/2010 ዓ.ም በአካል ጉዳተኞች ትምህርት ስታንዳርድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱም ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የአካቶ ትምህርትና የስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች፤ከትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሀመድ አህመዲን የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጅ፣ የሚዲያ አካላትና የፀጥታ ኃይል እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በአንዳንድ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ክፍል መግባትና ለሌላ ተማሪ ለመፈተን የመሞከር አዝማሚያዎች ቢከሰቱም በየደረጃው በተሰማሩ የፈተናው ግብረ ኃይል አማካይነት ችግሮቹ እልባት ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርሁን ዱሬሳ ገለጹ፡፡ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች የተፈተኑት እና ከ70ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞችና ተቆጣጣሪዎች የተሳተፉበት ፈተና፣ በአንዳንድ ፈተና ጣቢያዎች ላይ ሞባይል ይዘው ክፍል መግባት፣ ለመኮረጅ መሞከር፣ ለሌላ ተማሪ ለመፈተን መሞከር ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩ ቀላልና በፈተና ደንብ የሚታይ ይሆናል፣ በአጠቃላይ ግን ፈተናው በታቀደለት ጊዜ በሠላም ተጠናቋል ብለዋል ዶ/ር ዘርሁን፡፡

በአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሠጠ፤

በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠና ከግንቦት 23-ግንቦት 27/2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ነው ፡፡