የትምህርት ሚኒስቴር አካል ጉዳተኛና ልዩ ፍላጎት ያላቸው ዜጎችን የትምህርት ተሳትፎ ወደ 75 በመቶ ሽፋን ለማድረስ እየሰራ ነው

የትምህርት ሚኒስቴር አካል ጉዳተኛና ልዩ ፍላጎት ያላቸው ዜጎችን የትምህርት ተሳትፎ ወደ 75 በመቶ ሽፋን ለማድረስ እየሰራ ነው

የትምህርት ሚኒስቴር አካል ጉዳተኛና ልዩ ፍላጎት ያላቸው ዜጎችን የትምህርት ተሳትፎ አሁን ካለበት 4 በመቶ ወደ 75 በመቶ ለማድረስ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በአካል ጉዳተኛ ዜጎች የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ዙሪያ ከመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች፣ የአካል ጉዳተኛ ማህበራትና የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በአዲስ አበባ ካሌብ ሆቴል የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የልዩ ድጋፍና አካቶ ትምህርት ዳይሬክተር አቶ መሐመድ አቡበከር የምክክር መድረኩ በተካሄደበት ወቅት እንዳስታወቁት በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ትኩረት ተሰጥቷቸው ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል የአካል ጉዳተኛና ልዩ ፍላጎት ያላቸው ዜጎችን የትምህርት ተደራሽነት ማሳደግ አንዱ ሲሆን በአምስት አመቱ እቅድ ዘመን አካል ጉዳተኛና ልዩ ፍላጎት ያላቸው ዜጎችን የትምህርት ተሳትፎ አሁን ካለበት 4 በመቶ ወደ 75 በመቶ ለማድረስ ተጠናክሮ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

የአካል ጉዳተኛና ልዩ ፍላጎት ያላቸው ዜጎችን በሁሉም የትምህርት ዘርፎች ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል የአስር አመት ስትራቴጂክ ፕላን ተዘጋጅቶ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡ እስካሁን ሲሰሩ የነበሩ የትምህርት ቤት ግንባታዎች አካል ጉዳተኛ ዜጎችን ተደራሽ ያደረጉ አለመሆናቸውን የጠቆሙት አቶ መሐመድ በቀጣይ የህንፃ ግንባታ አዋጅን መሠረት በማድረግ የመማሪያ ክፍሎችና አስፈላጊ መገልገያዎች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ በማድረግ ይሰራሉ ብለዋል፡፡

በተያዘው በጀት አመትም የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን የትምህርት ተጠቃሚነት ለማሳደግ የንቅናቄ ሰነድ በማዘጋጀት፣ ትምህርት ቤቶችን ለአካል ጉዳተኞች ምቹ በማድረግ፣ መምህራን መስማት ለተሳናቸውና ለአይነ ስውራን ተማሪዎች ተገቢ ትምህርት እንዲሰጡ ለማስቻል አቅም የማጎልበት ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ እንዲሁም 1 እስከ 8 ክፍሎች ለሚማሩ መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች የመማሪያና ማስተማሪያ መፃህፍት ተዘጋጅተው መሰራጨታቸው፣ 1 ደረጃ ትምህርት መፃህፍትን በብሬል በመተርጎም ለአይነ ስውራን ተማሪዎች ተደራሽ የማድረግ፣ 2 ደረጃ ትምህርት መፃህፍትን በብሬል በማዘጋጀት ለአይነ ስውራን ተማሪዎች ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲሁም ለትምህርት ቤቶች አስፈላጊ የመማሪያ ማስተማሪያ ግብዓቶችን የማሟላት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

የምክክር መድረኩ በትምህርት ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት በአግባቡ በመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት ለህብረተሱ ተደራሽ ከማድረግ አንፃር ውስንነት በመኖሩ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ መረጃዎችን በምን መልኩ ለህብረተሰቡ ማስተላለፍ እንዳለባቸው የሚያስችል መሆኑን አቶ መሐመድ አስረድተዋል፡፡  ከተሳታፊዎች መካከል አንዳንዶች በሰጡት አስተያየት መድረኩ አካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ህጎችና መመሪያዎች ተፈፃሚነትና ፋይዳቸውን እንዲያውቁ ያደረገ መሆኑ፣ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችም ከመድረኩ ባገኙት ግንዛቤ በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ በሚፈለገው መልኩ ለመስራትና ለህብረተሰቡ መረጃዎችን በአግባቡ ለማድረስ እገዛ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡10 - Special needs ed Pic 2

በሌላ በኩል አካል ጉዳተኞች በትምህርትና በሌሎችም ዘርፎች በአግባቡ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተከታታይነት ያለው የተጠናከረ ስራ መሰራት እንዳለበት፣ እንዲሁም መስማት የተሳናቸው መምህራን በመምህርነት የስራ ቅጥር ቢወዳደሩም አድልኦ እየተፈፀመባቸው እንደሚገኝ ገልፀው የሚመለከታው አካላት መፍትሄ እንዲሰጡ ጠይቀዋል፡፡

በመድረኩ ትምህርት እንደ ሰብዓዊ መብት፣ የልዩ ፍላጎት/አካቶ ትምህርት ስትራቴጂና የአፈፃፀም መመሪያ፣ የስራ ስምሪት መብት አዋጅ፣ የአካል ጉዳተኞች የህንፃዎች፣ መንገዶችና መረጃ ተደራሽነት እንዲሁም በሰው ሰራሽና አካል ድጋፍ ምንነት


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡