ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከተማሪ ቅበላ ጀምሮ በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሠረት ስኬታማ አየሆኑ ነው

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከተማሪ ቅበላ ጀምሮ በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሠረት ስኬታማ አየሆኑ ነው

 

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስትር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀውን ሰላሳ ሁለተኛው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማዊ ለውጥ ምክር ቤት ጉባኤ ሲከፍቱ ያለፉት ዘጠኝ ወራት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመልካም አስተዳደር ዕቅዶች ስኬት የታየበት፣ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስርዓቱ ከሞላ ጎደል በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በተሻለ ሁኔታ የተካሄደበት፣ የመማር ማስተማር ሂደቱ ከተማሪ ቅበላ ጀምሮ በተቀመጠው ስታንዳርድ መሠረት የቀጠለበት ወቅት እንደነበር ገልጹ፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ ስኬቶቹ በዩኒቨርሲቲ ቦርድ፣በማኔጅመቱና በመላው ዩኒቨርሲቲዎቻችን ማህበረሰብ አመራር የተገኙ በመሆናቸው ተገቢው ዕውቅና ሊቸራቸው እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት የተጀመሩ ብቁና በቂ የሰለጠነ የሰው ሃይል ለልማታችን ፣ለዴሞክራሲያችንና ለሰላማችን የማቅረብ ስራ በሚመለከት በተደራጀ የትምህርትና የቴክኖሎጂ ሰራዊት ግንባታ ያለበትን ደረጃ መገምገም የመድረኩ ዋንኛ ዓላማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያለው የሠራዊት ግንባታ እንቅስቃሴያችን ባለፉት ዓመታት ሲያጋጥመን የነበረውን ተግዳሮት በወሳኝ መልኩ የተሻገርነው ቢሆንም አሁን ያለበት ቁመናና ጥራቱ መፈተሽ እንዳለበት ያሳሰቡት አቶ ሽፈራው በተለይም ፍሬ የሚያፈራ የተደራጀ የምርምር ስራ፣የተደራጀ የማስተማር ስራ፣የተደራጀ ማህበረሰብ የማገልገል እንዲሁም ብቁ ዜጋ የመገንባት ስራ ያለበት ደረጃ በመድረኩ እንደሚፈተሽ ተናግረዋል፡፡

በተጫማሪም ዩኒቨርሲቲዎቻችን ኪራይ ሰብሳቢነትን የሚፀየፉና የሚዋጉ ዜጎችን የሚያመርቱ የመልካም አስተዳደር የልቀት ማዕከላት ለማድረግ የተጀመረው ጉዞ የደረሰበት ደረጃ እንደሚገመገምም አቶ ሽፈራው አስታውቀዋል፡፡የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ለመምህራን አቅም ግንባታ ትኩረት ስጥቶ ለመስራት ዕቅድ ተይዞ ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው የተሰሩ ስራዎች በጥልቀት እንደሚፈተሹ ጠቁመው ከዚህ በተጨማሪም ሴት ምሁራንን ወደ ዩኒቨርሲቲ አመራርነት ከማምጣት አንጻር ስምንት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ምክትል ፕሬዚዳንቶች መመደባቸውን ጠቁመው ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እስካሁን ያልመደቡበትን ምክንያት ሊያቀርቡ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ንጉሴ ምትኩ በበኩላቸው እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው ባለፉት ዘጠኝ ወራት በመማር ማስተማር፣በምርምርና ማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ከፍተኛ ለውጥ ማስመዝገቡን ገልፀዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በሰብል ምርት፣በእንስሳት እና በአትክልትና ፍራፍሬ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ የምርምር ስራዎችን ከሀገር ውስጥና ከውጪ ተቋማት ጋር በጋራ እያካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

አካባቢው ለኢትዮጵያ ሥነፅሁፍ መጎልበት ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ሰዎች መፍለቂያ መሆኑን የገለጹት / ንጉሴ በደራሲ ሀዲስ አለማየሁ ስም የተሰየመ የባህል ጥናት ተቋም በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ተቋቁሞ በዘርፉ በርካታ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡ በምስራቅ ጎጃም ዞን ጥቂት ወረዳዎች በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የከብቶች ዋጋ ማሽቆልቆሉን የጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ ዩኒቨርሲቲው 300 በሬዎችን በመግዛት ወርዶ የነበረውን የከብት ዋጋ ማረጋጋት መቻሉንም ገልፀዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ አመታትም የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የመምህራን ልማት እና የቤተ ሙከራ ግብዓት ማሟላት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የጠቆሙት / ንጉሴ በተጨማሪም በተለያየ ስነ ምህዳር ላይ የሚቋቋሙ ሁለት የምርምር ጣቢያዎችን ለማቋቋም እየሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ ጉባኤው ዛሬና ነገ በሚኖረው ቆይታ የመቐለ፣ወሎ፣ቡሌሆራ፣ወልቂጤ፣ወላይታሶዶና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲዎች የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሱፐርቪዥን ሪፖርት አዳምጦ ውይይት ያካሂዳል፡፡


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡