የ2010 ትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ

የ2010 ትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ


በመሆኑም በዘንድሮው የትምህርት ዘመን በመንግስትም ሆነ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመደበኛና መደበኛ ባልሆነ የትምህርት መርሃ ግብር መከታተል እንደሚችሉ የገለፁ ሲሆን፣ በግል በመደበኛው መርሃ ግብር ገብተው ትምህርታቸውን መከታተል የሚችሉ ተማሪዎች 295 እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚጠበቅባቸው ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
በዚህም መሠረት በመንግስት የትምህርት ተቋማት በመደበኛና በማታ በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ለወንዶች 352 እና ከዚያ በላይ ፣ለሴቶች 330 እና ከዚያ በላይ ሲሆን በአዎንታዊ ድጋፍ ለአርብቶ አደርና ታዳጊ ክልል እንዲሁም ከፊል አርብቶ አደር ተወላጅ ተማሪዎች ለወንዶች 320 እና ከዚያ በላይ፣ ለሴቶች 305 እና ከዚያ በላይ እና መስማት ለተሳናቸው ወንዶችም ሆኑ ሴቶች 275 እና ከዚያ በላይ መሆኑን በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ለማወቅ ተችሏል፡፡
በተያያዘ ዜና በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ለግል ተፈታኞች ለወንዶች 360 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች 355 እና ከዚያ በላይ እንዲሆን ተወስኗል፡፡
በተመሳሳይ በማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት በሁሉም መደበኛ እና የማታ መርሃ ግብር ለወንዶች 335 እና በላይ፣ ለሴቶች 320 እና በላይ፣ ለታዳጊ ክልሎች ተማሪዎችና ለአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢ ተማሪዎች ለወንዶች 315 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች 300 እና ከዚያ በላይ፣ ሁሉም መስማት የተሳናቸው ወንድም ሆነ ሴት ተማሪዎች 275 እና በላይ፣ ለሁሉም አይነ-ስውራን ተማሪዎች ወንዶችና ሴቶች 200 እና ከዚያ በላይ ውጤት እንዲሁም የግል ተፈታኞች ለወንዶች 360 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች 355 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመደበኛው መርሃ ግብር በውድድር ተመድበው እንዲማሩ ከሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡
ዘገባው እንደሚያመላክተው 2010 የትምህርት ዘመን በመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመደበኛ የትምህርት መርሃ ግብር የሚቀላቀሉ አዲስ ተማሪዎች 140,333(ወንድ 80,437 እና ሴት 59,896) ይሆናሉ፡፡

የዘንድሮው 12 ክፍል የፈተና ውጤት ሐምሌ 28/2009 . ይፋ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡

 

Image may contain: text


ዜናዎች

የቀጣይ 5 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ይፋ ሆነ

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር "የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ለፍትሃዊነት " በሚል መሪ ቃል ለቀጣዩ 5 ዓመታት የሚተገበር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

አካል ጉዳተኞች እንደየችሎታቸውና እንደየፍላጎታቸው መማር እንደሚገባችዉ ተገለጸ፤

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ከሰኔ 04 - 11/2010 ዓ.ም በአካል ጉዳተኞች ትምህርት ስታንዳርድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱም ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የአካቶ ትምህርትና የስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች፤ከትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሀመድ አህመዲን የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጅ፣ የሚዲያ አካላትና የፀጥታ ኃይል እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በአንዳንድ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ክፍል መግባትና ለሌላ ተማሪ ለመፈተን የመሞከር አዝማሚያዎች ቢከሰቱም በየደረጃው በተሰማሩ የፈተናው ግብረ ኃይል አማካይነት ችግሮቹ እልባት ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርሁን ዱሬሳ ገለጹ፡፡ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች የተፈተኑት እና ከ70ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞችና ተቆጣጣሪዎች የተሳተፉበት ፈተና፣ በአንዳንድ ፈተና ጣቢያዎች ላይ ሞባይል ይዘው ክፍል መግባት፣ ለመኮረጅ መሞከር፣ ለሌላ ተማሪ ለመፈተን መሞከር ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩ ቀላልና በፈተና ደንብ የሚታይ ይሆናል፣ በአጠቃላይ ግን ፈተናው በታቀደለት ጊዜ በሠላም ተጠናቋል ብለዋል ዶ/ር ዘርሁን፡፡

በአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሠጠ፤

በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠና ከግንቦት 23-ግንቦት 27/2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ነው ፡፡