የ2010 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አዲስ ገቢ ተማሪዎች ምደባ ድልድል ይፋ ሆነ፡፡

የ2010 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አዲስ ገቢ ተማሪዎች ምደባ ድልድል ይፋ ሆነ፡፡

2009 . የመሰናዶ ትምህርታቸውን በመከታተል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች ምደባ ድልድል ይፋ ሆነ፡፡ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ ዛሬ ከቀኑ 800 ሠዓት ላይ በኤጀንሲው ድረ ገፅ እንደሚለቀቅ ገልጿል፡፡
ምደባው የተማሪዎችን የትምህርት መስክ ምርጫ፣ የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች የክልል ስብጥር ባመላከተ መልኩ የተከናወነ ከመሆኑም በተጨማሪ ተማሪዎች ባስመዘገቡት ውጤት መሰረት እንደተደለደለ አቶ አርአያ ገልፀዋል፡፡ አቶ አርአያ አያይዘውም የጤና ችግር ኖሮባቸው የጤና ማስረጃ ያቀረቡ 137 የእንቅስቃሴ ችግር ያለባቸው 34 የሚያጠቡ እናቶች 25 መስማት የተሳናቸው 63 ተመሳሳይ ፆታ ያላቸው መንትዮች 37 እንዲሁም የአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር 40 መሰናዶ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ ድልድል መደረጉን ገልፀዋል፡፡
በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ከሚገቡት መካከል 94,195 ወንዶች፣ 42,941 ሴቶች በድምሩ 137,136 18 የትምህርት መስኮች መመደባቸውን አቶ አርአያ ገልፀዋል፡፡ 56.77/43.23 የወንድ ሴት ጥምርታ፣ 68.69 / 31.31 የተፈጥሮ ሳይንስ እና የህብረተሰብ ሳይንስ ጥምርታ እንዲሁም ኢንጂነሪንግ ከሌሎች ትምህርቶች ጋር ሲመዘን 30.48 ጥምርታ እንዳለው ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም አቶ አርአያ አያይዘውም የተማሪዎች የምደባ ውጤት በድህረ ገፅ www.app.neaea.gov.et እንዲሁም የየዩኒቨርሲቲዎች የምዝገባ ፕሮግራም በትምህርት ሚኒስቴር ቴሌቪዥን Frequency 11512 – Symbol rate 27500 – Polarization Vertical የሚገነውን እንዲከታተሉ አስገንዝበው ተማሪዎች ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ በተመደቡበት ዩኒቨርሲቲዎች በወቅቱ እንዲገኙ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

የኤጀንሲው ዳይሬክተር አቶ አርአያ /እግዚአብሄር የተማሪዎች ውጤት አወሳሰን፣ ሁለተኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድና አምስተኛውን የትምህርት ዘርፍ ልማት ፕሮግራም፣ የመንግስትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመቀበል አቅም፣ በትምህርትና ስልጠና መስክ የግል ሴክተሩ የሚጫወተውን ሚናና የዜጎች የመማር ዕድል መስፋት፣ የሴቶች ተማሪዎችን ቁጥር በማበራከት የትምህርት ፍትሃዊነትን ማረጋገጥ፣ የታዳጊ ክልልና የአርብቶ አደር ተወላጅ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተሳትፎ ማጠናከር እንዲሁም የአገራችንን ፈጣን ዕድገት ቀጣይ ለማድረግና ተፈላጊውን የሰው ኃይል ግንባታ ለማስቀጠል መሰረት ያደረገ እንደነበር አብራርተዋል፡፡


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡