የ2010ዓ.ም ትምህርት ዘመን መቀበያ ውይይት

የ2010ዓ.ም ትምህርት ዘመን መቀበያ ውይይት

2010 . የትምህርትና ስልጠና ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ ከመስከረም 08-15/2010 . የሚቆይ የመምህራን ፣አስተዳደርና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች እንዲሁም የትምህርትና ስልጠና አመራር አካላት ውይይት እንደሚካሄድ ተገለፀ፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር / ሳሙኤል ክፍሌ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት የስልጠናው ዋና ዓላማ መምህራን የትምህርት ጥራት በማረጋገጥ ለሀገራዊ ህዳሴ የሚኖራቸው ሚና፣የትምህርትና ስልጠና ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ የውጤታማ አሰራር ስርዓት /Deliverology/ በተመለከተ እንዲሁም የስነዜጋና ስነምግባር ትምህርትን እንዴት መሻሻል እንደሚገባውና የባለድርሻ አካላት ሚና ላይ እንደሚያተኩር እና በመጨረሻም ሁሉም የዘርፉ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት 2009 . የእቅድ አፈፃፀም በመገምገም 2010. እቅድ ላይ በመወያየት ለቀጣይ የተሸለ መነሳሳት የሚፈጥሩበት ይሆናል በማለት ገልፀዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም የክፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቅበላ አቅምን አስመልክተው ከጋዜጠኞች የቀረበላቸው ጥያቄ 2010 . በመደበኛ ትምህርት መርሃ ግብር 140,000 የሚጠጉ አዲስ ተማሪዎች ወደ ክፍተኛ የመንግስት ትምህርት ተቋማት እንደሚቀላቀሉና አዲሶችንም ሆነ ነባር ተማሪዎችን ለማስተናገድ የቅድመ ዝግጅት ስራ መጠናቀቁን ጠቁመዋል፡፡
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ሚኒስቴር ደኤታ ክቡር አቶ ተሾመ ለማ የውይይቱ ርዕሰ ጉዳዮችን ከሌላው ጊዜ ለየት የሚያደርገቸው ሙሉ በሙሉ በዘርፉ ጉዳይ ላይ እንዲያተኩር ተደርጎ መዘጋጀታቸው ነው ብለዋል፡፡
እንደ ሚኒስቴር ደኤታው ገለፃ ይህ ውይይት እንደ ዘርፍ ከፌዴራል ትምህርት ሚኒስቴር ጀምሮ እስከታችኛው ትምህርት መዋቅር ድረስ የሚሰጥ መሆኑን ገልፀው በውይይቱ የሌሎች ሀገሮች ልምድ የሚቀርብበት፣መምህራንና አሰልጣኞች በጥልቀት የሚወያዩበትና ለውጤት የሚዘጋጁበት መሆኑን አመላክተው የዚህ አይነቱ ውይይት በቀጣይም ከወላጆች፣ከተማሪዎችና ከሌሎችም የትምህርትና ስልጠና ዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚካሄድ አመላክተዋል፡፡
በኢ..ዴሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ተወካይ አቶ ብርሃኑ ሞረዳ በበኩላቸው በትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ስራ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት፣ ትምህርት ቤቶች ያሉበትን ደረጃ መዝኖ ለመደገፍ፣ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት ስራዎች በስፋት እየተሰሩ መሆናቸውን የትምህርት ጥራቱንም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሻጋገር ለቅድመ መደበኛ ትምህርት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም ከተለያዩ የሚድያ ተቋማት የመጡ የሚድያ ባለሙያዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ምላሽ ተሰጥቷል፡፡


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡